.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዬው የህዝብ ቁጣ ገንፍሎ ለመውጣት መቃረቡን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ገለጡ

ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ መንግስት አኬል ዳማ በሚል ስም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስም ያሰራጨው የፈጠራ ድራማም፣ ጭንቀት የወለደው መሆኑን ዶክተሩ ተናግረዋል። የህዝቡ ምሬት ከሚገባው በላይ ጨምሩአል የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር መፈንዳቱ አይቀሬ ነው ብለዋል። ዶ/ር ነጋሶ እንዳሉት አኬል ዳማ ተብሎ የተሰራው ድራማ በህዝቡም ላይ ሆነ በፓርቲያቸው ላይ የፈጠረው አንዳችም ተጽእኖ ዬለም። በሌላ ...

Read More »

ኢትዮጵያ፤ ታንዛኒያና ዛምቢያ የቀድሞዉ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽን አስረዉ ለፍርድ እንዲያቀርቡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ

ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በለንደን የሚገኘዉ አለም አቀፉ የሰብኣዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅት አምነስቲ ኢንርተርናሽናል የቀድሞዉ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ለአምስት ቀን ጉብኝት የሚጎበኟቸዉ አገሮች ኢትዮጵያ፤ ታንዛኒያና ዛምቢያ  በሰልጣን ላይ በነበሩበተ ወቅት  ለፈፀሙት አለምአቀፍ ወንጀል አስረዉ ለፍርድ እንዲያቀርቧቸዉ ጥሪ አቀረበ። ፕሬዝዳንት ቡሽ ለፈፀሟቸዉ ወንጀሎች በቂ ማስረጃዎች በህዝብ፤ በአሜሪካን መንግስት ባለስልጣኖች እና በቡሽ በእራሳቸዉ እጅ እንደሚገኝ  አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባቀረበዉ ጥሪ ...

Read More »

ኢትዮጵያ የስሎቫክን አምባሳደር በማሰሯ ይቅርታ ጠየቀች

ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ ባለፈዉ እኤአ ጥቅምት 5 2011 የስሎቫክ አምባሳደር ሚላን ዱብቼክን ማሰሯ ስህተት እንደሆነና  ወደፊት ተመሳሳይ ድርጊት እንደማትፈፅም የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት በአዲስ አበባ ለሚገኘዉ የአዉሮፓ ህብረት የልኡካን ቡድን በመግለፅ ይቅርታ መጠየቋን የስሎቫክ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። “አሁን የተሰጠንን ማብራሪያና የቀረበዉን ይቅርታ በቂ ሆኖ አግኝተነዋል”” ብለዋል ሚኒስትሩ። ቀደም ሲል በዚህ ጉዳይ ...

Read More »

ወደ እስራኤል ሲጓዙ ህይወታቸዉ ላለፈ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊያን የመታሰቢያ ሃዉልት እንዲቆም ተወሰነ

ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ እስራኤል በእግር ሲጓዙ ህይወታቸዉን ላጡ አራት ሺህ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊያን የመታሰቢያ ሃዉልት እንዲሰራ የእስራኤል የሚኒስትሮች ም/ቤት መወሰኑን ጄ ዊክሊ የተባለዉ የእየሩሳሌም ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘግቧል። በእየሩሳሌም ኸርዝል ተራራ ላይ በሚሰራዉ በዚህ የመታሰቢያ ሃዉልት ላይ የሞቱት ቤተ አስራኤላዊያን የስም ዝርዝር እንደሚቀረፅ ተመልክቷል። “የመታሰቢያዉ ሃዉልት መሰራት 130 ሺህ የሚሆን ቁጥር ያላቸዉ ወንዶች፤ ሴቶች፤ ህፃናት እና ...

Read More »

አርሶአደሩ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ 500 ብር እንዲያወጣ፣ ለህዝብ ማመላለሻ መኪና ክላውዲዮ የሚያወጡ ደግሞ 7 ሺ ብር እንዲከፍሉ መመሪያ ወጣ

ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝቅተኛው  አርሶአደር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ 500 ብር እንዲያወጣ፣ ለህዝብ ማመላለሻ መኪና ክላውዲዮ የሚያወጡ ደግሞ 7 ሺ ብር እንዲከፍሉ እንዲሁም መምሀራን የደሞዛቸውን 100 ፐርሰንት እንዲከፍሉ የሚያደርግ መመሪያ ወጣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ዝቅተኛ የተባለው ገበሬ ለግድቡ ማሰሪያ አምስት መቶ ብር እንዲያዋጣ፣ የተሻለ ገቢ አለው የተባለው ገበሬ ደግሞ ከ1 ሺ ብር ጀምሮ እንደዬደረጃው እንዲከፍል ይደረጋል። የወረዳ ...

Read More »

የኦክላንድ የምርምር ተቋም በኢትዮጵያ የሚደረገው የመሬት ሽያጭ መቆም እንዳለበት ገለጠ

ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የኦክላንድ የምርምር ተቋም በኢትዮጵያ የሚደረገው የመሬት ሽያጭ መቆም እንዳለበት ገለጠ፣ በጋምቤላ መሬት የሚወስዱትና ንግዱን የተቆጣጠሩት የአንድ ብሄር ሰዎች መሆናቸውንም አጋለጠ ተቀማጭነቱ በካሊፎርኒያ አሜሪካ የሆነው የኦክላንድ የምርምር ተቋም መስራችና የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አኑራዳ ሚታል ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ የሚቸበችበው መሬት፣ ለአገሪቱ ...

Read More »

”ኦነግ ነፃ ድርጅት እንጂ የወያኔ ተለጣፊ ቡድን አይደለም” ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ገለጸ

ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “የኦነግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት፤ ዛሬ ወያኔ ከኤርትራ መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት ስለተቋረጠ የሚቋረጥ አይሆንም፤ኦነግ በሁለት እግሮቹ ራሱን ችሎ የቆመና የተመሰረተበትን ህዝባዊ አላማ በነፃነት የሚያራምድ ነፃ ድርጅት እንጂ፤የወያኔ ተለጣፊ ቡድን አይደለም”ሲል  የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ገለጸ። “ኦነግ ኤርትራ ውስጥ ተመስርቶ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እስኪመስል ድረስ፤የወያኔ ቡድን ስለ ኦነግ ባነሳ ቁጥር የኤርትራን ስም ሳያነሳ ያለፈበት ጊዜ የለም” ...

Read More »

የአቶ መለስ መንግሥት በ”ሽብርተኝነት‘ በወነጀላቸው ስምንት ተከሳሾች ላይ በዐቃቤ- ሕግ ተሸሻለ የተባለው የክስ ቻርጅ ዛሬ ቀረበ

ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግሥት በ”ሽብርተኝነት‘ ከወነጀላቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢያን ኢትዮጵያዊያን ውስጥ ሀገር ውስጥ በእሥር ላይ በሚገኙት ስምንት ተከሳሾች ላይ በዐቃቤ- ሕግ ተሸሻለ የተባለውን የክስ ቻርጅ ዛሬ አቀረበ፡፡ ይህ ተሸሻለ የተባለው የክስ ቻርጅ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር እና ዋና አዘጋጅ የሆኑት ዐብይ ተክለማርያምና መስፍን ነጋሽን አያካትትም ተብሏል፡፡ እነ ...

Read More »

የታሪክ ምሁሩ ጆን ማርካኪስ ህወሀት ከቀድሞው የደርግና የሀይለ ስላሴ ስርአቶች ለመማር ባለመቻሉ፣ ለመውደቅ ተቃርቧል አሉ

ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ መጽሀፎችን በመጻፍ እውቅና ያተረፉት ታወቂው የፖለቲካና ታሪክ ምሁር ጆን ማርካኪስ ፣ ህወሀት መራሹ መንግስት ከቀድሞው የደርግና የሀይለስላሴ ስርአቶች ለመማር ባለመቻሉ፣ ለመውደቅ ተቃርቧል አሉ። “ኢትዮጵያ ፣ ዘ ላስት ቱ ፍሮንቲየርስ” የሚለውን አዲሱን መጽሀፋቸውን ለማስተዋወቅ በለንደን ቻትሀም ሀውስ በተገኙበት ወቅት እንደገለጡት አገዛዙ ስልጣን በበቂና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ወደ ክልሎችና ወደ ...

Read More »

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱት የመለስ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመውን ከልክ ያለፈ ግፍ ለማውገዝ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በላይ ወንድ አፍራሽ ለጀርመን ሬዲዮ ገልጠዋል። መለስ ወያኔ ይውደም፣ የታሰሩት ንጹሀን ዜጎች ይለቀቁ፣ የመሬት ሽንሸናው ይቁም፣ ጀርመን አምባገነኖችን አትርጂ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች በእለቱ ተስተጋብተዋል። ኢትዮጵያኑ ከዚህ ቀደም በኑረምበርግ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ሳምንታትም በዋና ...

Read More »