ወደ እስራኤል ሲጓዙ ህይወታቸዉ ላለፈ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊያን የመታሰቢያ ሃዉልት እንዲቆም ተወሰነ

ህዳር 22 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ወደ እስራኤል በእግር ሲጓዙ
ህይወታቸዉን ላጡ አራት ሺህ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊያን የመታሰቢያ ሃዉልት እንዲሰራ የእስራኤል የሚኒስትሮች ም/ቤት መወሰኑን ጄ ዊክሊ የተባለዉ የእየሩሳሌም ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘግቧል።

በእየሩሳሌም ኸርዝል ተራራ ላይ በሚሰራዉ በዚህ የመታሰቢያ ሃዉልት ላይ የሞቱት ቤተ አስራኤላዊያን የስም ዝርዝር እንደሚቀረፅ ተመልክቷል።

“የመታሰቢያዉ ሃዉልት መሰራት 130 ሺህ የሚሆን ቁጥር ያላቸዉ ወንዶች፤ ሴቶች፤ ህፃናት እና አረጋዊያን ወደ እስራኤል ለመምጣት በጀመሩት ረዢምና አድካሚ ጉዞ ጥቂቶቹ በምግብና በዉሃ እጥረት እንዲሁም በበሽታ በመሰቃየት የረገፉበትን ምእራፍ እንዘጋዋለን።” ይላል ከጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ነትናያሁ ጽ/ቤት ስለመታሰቢያዉ ግንባታ የወጣዉ መግለጫ።