በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ህዳር 20 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱት የመለስ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመውን ከልክ ያለፈ ግፍ ለማውገዝ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በላይ ወንድ አፍራሽ ለጀርመን ሬዲዮ ገልጠዋል።

መለስ ወያኔ ይውደም፣ የታሰሩት ንጹሀን ዜጎች ይለቀቁ፣ የመሬት ሽንሸናው ይቁም፣ ጀርመን አምባገነኖችን አትርጂ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች በእለቱ ተስተጋብተዋል።

ኢትዮጵያኑ ከዚህ ቀደም በኑረምበርግ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ሳምንታትም በዋና ከተማዋ በርሊን ተመሳሳይ ሰልፍ ያደርጋሉ።

የመለስ መንግስት ሰለማዊ የነጻነት ታጋዮችን አንዴ በአሸባሪ ሌላ ጊዜ አገር በመክዳት ወንጀል ስም እየሰጠ ማሰሩ አለማቀፍ ውግዝት እያስከተለበት ነው።

የአለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ሲፒጄ ፣ ሂውማን ራይትስ ወች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል  የመለስ መንግስት ሀሳብን በጉልበት ለማፈን
የሚደረገውን ሙከራ መቃወማቸው ይታወሳል።