ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትላንትናው እለት በ11/04/04ዓ.ም ለፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ መከላከያ ምስክር ሆኖ በመቅረብ የመሰከረላት የፍትህ አዘጋጅ ሀይለመስቅል በሸዋምየለህ ከምሽቱ 12፡30 ላይ ቢሮ በር ላይ የደህንነት ሰራተኛ ነን ያሉ 3 ግለሰቦች ሲም ካርዱን ከነጠቁ በኋላ ከባድ ማስፈራራያ እንዳደረሱበት ታወቀ በዚሁ እለት ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ የፍትህ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እና ሀይለመስቀል በሸዋምየለህ ከቢሮ ወጥተው ሲሄዱ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢሚግሬሽንና ደህንነት መስሪያቤት ሰራተኞች ፓስፖርት እና ቪዛ ጠያቂዎችን ለማስተናገድ በማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ ነው
ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው ኢትዮጵያውያኑ ፓስፖርት ለማግኘት ሲሉ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ በኢሚግሬሽን ፊት ለፊት ሰልፍ ይይዛሉ። አብዛኞቹ ፓስፖርት ጠያቂዎች ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት ለስራ ፍለጋ የሚሄዱ ናቸው። በቪዲዮ ምስል አስደግፎ በላከው መረጃ እንደገለጠው በእየለቱ የሚታየው ረጅም ሰልፍ በተሽከርካሪ ፍሰት ላይም ችግር እየፈጠረ ነው። በሱዳን ኢምባሲ አካባቢ የሚታዩት ረጃጅም ሰልፎች የአገሪቱ ህዝብ ...
Read More »የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ የኢትዮጵያ ጦር በአሁኑ ጊዜ ሶማሊያ ውስጥ አልገባም አሉ
ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ውስጥ ወታደር ለመቅጠር ተቸግረን ነበር ሲሉም ተናግረዋል። መከላከያ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከትናንት በስቲያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ውስጥ ለተሰበሰቡት የኢህአዴግ አባላት የመስሪያ ቤታቸውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት -ከብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ከአቶ ግርማ ሰይፉ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው። ከሳምንታት በፊት በ አዲስ አበባ በተካሄደውና በአቶ መለስ ዜናዊ በተመራው የኢጋድ አባል አገራት ስብሰባ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በመንግስት ላይ የሚያደርጉት ተቃውሞ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ መንግስት ስደተኞችን በማስፈራራት ድጋፍ ለማግኘት እየሞከረ ነው ተባለ
ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመንግስት ላይ የሚያደርጉት ተቃውሞ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ መንግስት ስደተኞችን በማስፈራራት ድጋፍ ለማግኘት እየሞከረ ነው ተባለ የመለስ መንግስት በፖለቲካው መስክ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ የተባሉ ስደተኞችን ሰነድ ለመንግስታት የውጭ አገር መስሪያቤቶች በመላክ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ለማድረግ አዲስ ስልት ቀይሷል። በጀርመን አገር አከን ከተማ ነዋሪ የሆነው ነብዩ አለማየሁ ላለፉት 10 አመታት በድረገጾች ላይ ...
Read More »የህወሀት ጄኔራሎች እና የህወሀት ኩባንያ የሆነው ኢፈርት በፑንትላንድ እና ጁባ ላንድ ከፍተኛ ዝርፊያ እየፈጸሙ ነው ተባለ
ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የዛሬ 20 አመት ፣ የሲያድ ባሬ መንግስት እንደተገረሰሰ የሶማሊያ የጎሳ መሪዎች አገሪቱን ለብተና የዳረገ ጦርነት አካሄዱ፣ ጦርነቱም እስከ ዛሬ ቀጥሎ ህልቆ መሳፍርት ሶማሊያውያን ተገደሉ፣ ተሰደዱ። ጦርነት ለአንዱ ሰርግ ይሆንለታል ለሌላው ደግሞ ተስካር ይሆንበታል እንደሚባለው፣ በሶማሊያ ጦርነት ከፍተኛ ትርፍ በማጋበስ ላይ የሚገኙ ጎረቤት አገሮች አሉ። በ1940ዎቹ አውሮፓ በጦርነት ትታመስ በነበረችበት ጊዜ፣ የአሜሪካ መንግስት የጦር ...
Read More »የኢህአዴግ መንግሥት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው ዜጎች ላይ 30ኛውን ምስክር አቀረበ
ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢህአዴግ መንግሥት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው በሀገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚኖሩ 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትና ጋዜጠኞች ላይ 30ኛውን ምሥክር ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ አቀረበ፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዐቃቤ- ሕግ የድምጽ፣ የምሥል እና የሠነድ ማስረጃዎችን እንዲያቀርብ ለሃሙስ ከሰሃት ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ.ም አዟል፡፡ አርቲስት ደበበ እሸቱ ...
Read More »ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች በአቶ መለስ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈባቸው
ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፐርሰን በሶማሌ ክልል ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው የስዊድን ነዳጅ ፈላጊ ኩባንያ፤ እነሱ እንዳሉት ፦በአካባቢው ነዋሪዎችና በሰራተኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸምና አለመፈፀሙን ለማጣራት” ፤ ከኦጋዴ ነፃ አውጭ ግንባር ተዋጊዎች ጋር በመሆን ድንበር አሳሰብረው ወደ ክልሉ ለመግባት ሲሞክሩ በኢትዮጵያ ወታደሮች ቆስለው የተያዙት፤ ከስድስት ወር በፊት ነው። ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ስር በዋሉ ማግስት ...
Read More »የሰሜን ኮሪያዉ መሪ መሞትን ተከትሎ በዓለም ላይ በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነን መሪዎች ቁጥራቸዉ ወደ 8 መዉረዱን ኢንተርኔሽናል ቢዝነስ ታይምስ ገለፀ
ታህሳስ 09 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሰሜን ኮሪያዉ መሪ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ፤ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በዓለም ላይ በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነን መሪዎች ቁጥራቸዉ ወደ 8 መዉረዱን ኢንተርኔሽናል ቢዝነስ ታይምስ ገለፀ ኢንተርኔሽናል ቢዝነስ ታይምስ የተባለዉ የመረጃ ምንጭ የሰሜን ኮሪያዉ ኪም ጆንግ 2ኛና የሊቢያዉ ሙአመር ጋዳፊ በ2011 በተወገደላት አለማችን ዉስጥ ቁጥራቸዉ ስምንት የሆኑ አምባገነኖች ዛሬም የመንግሰት ስልጣን ጨብጠዉ ሰብኣዊ ...
Read More »የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ 42 ኢትዮጵያዊያን በሳኡዲ አረቢያ ተደብድበው ታሰሩ
ታህሳስ 09 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ቤተ ክርስቲያን በሚገለገሉበት የመኖሪያ ቤት ዉስጥ የምሽት ፀሎትና የሃይማኖት ትምህርት በመከታተል ላይ የነበሩ 42 የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አሰሳ ባደረጉ የሳኡዲ አረቢያ የፀጥታ ሃይሎች ተይዘዉ መደብደባቸዉንና መታሰራቸዉን አለም አቀፍ የክርስቲያን ኮንሰርን ገልጧል። የመረጃ ምንጩ እንደገለፀዉ ቁጥራቸዉ አናሳ የሆኑት የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እምነታቸዉን በነፃነት እንዳይከታተሉ በሳኡዲ አረቢያ ከፍተኛ ተፅእኖ አለባቸዉ። በደቡብ ሳኡዲ አረቢያ ...
Read More »አዲሱ ሊዝ አዋጅ ከንግድ ማህበረሰቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
ታህሳስ 08 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የንግዱን ማህበረሰብና ተቃውሞ አስመልክቶ ምላሽ ይሰጣሉ ተብለው በስብሰባው የተጋበዙት የመንግስት ባለስልጣን ሳይገኙ ቀሩ። በሁኔታው ቅር የተሰኙት የንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ በበኩላቸው፦”ጥያቄዎችማ አሉን፤ የሚመልስልን አጣን እንጂ” በማለት መንግስት የንግድ ማህበረሰቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ሊፈታ እንዳልቻለ ጠቁመዋል። ባለፈው ዓርብ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው ሁለተኛው አዲስ ቻምበር ቢዝነስ ፎረም አጀንዳ ሆነው ...
Read More »