.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢህአዴግ አባልነታቸውን አነፈልግም ብለው ከለቀቁ በሁዋላ ወደ መኢአደ የገቡ 21 የቀደሞ የ ኢህአዴግ አባላት ታሰሩ

ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) እንዳለው፤ ካለፈው ጥር 8 ቀን እስከ ጥር 15 ቀን ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ብቻ፤ 38  የመኢአድ አባላት ታስረዋል። ከነዚህም መካከል 21ዱ፤ የኢህአዴግ አንድ ክንፍ ከሆነው ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር-ደኢህዴግ  አባልነት ራሳቸውን በማግለል፤ ወደ መኢአድ የገቡ ናቸው። እንደ መኢአድ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ገለፃ፤ የኢህአዴግ አባላት የነበሩት 21 ሰዎች የታሰሩት፤ በመ ...

Read More »

በሀገረማርያም አካባቢ የሚኖሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከምርጫ በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አትችሉም መባላቸው ገለጡ

ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ለኢሳት እንደገለጡት የደህንነት ሀይሎች ከምርጫ በፊት ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል እንደነገሩዋቸው ገልጠዋል። የደህንነት ሀይሎችም በተደጋጋሚ ሊያስፈራሩዋቸው እንደሚሞክሩ ተወካዩ ገልጠዋል። በመደረክ አባላት ላይ የሚደርሰው ወከባ እየጨመረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Read More »

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከ ጥር 12 ቀን ጀምሮ ሶስተኛ አመታዊ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄዱን ገለጠ

ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጠው በጉባኤው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የክልል ተወካዮችን ጨምሮ የአውሮጳ፤ የአፍሪካ፤ የኦሲኒያ፤ የመካከለኛው ምስራቅ፤ የካናዳ፤ የሰሜን አሜሪካና የአውሮጳ ተወካዮች እየተሳተፉበት ነው። በዚህ ሶስተኛ ጉባኤ ላይ በዋንኛነት መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው ከወያኔ ጋር እየተካሄደ ያለው የጸረ ዘረኝነት ትግል ይበልጥ ተጠናክሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግቡን ሊመታ የሚችልበትን ድርጅታዊ አቅም በማጎልበት ላይ ...

Read More »

ኢሳት ለማጠናከር በሚኒሶታ ታላቅ የራትና የመዝናኛ ዝግጅት እንደተደገሰ አስተባበሪዎቹ አስታወቁ

ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንን ለማጠናከር በሚኒሶታ ታላቅ የራትና የመዝናኛ ዝግጅት እንደተደገሰ አስተባበሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ በላኩት መግለጫ ላይ አስታወቁ:: በዚህ ዕለት ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነና ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ እንደሚገኙ ታውቋል:: “ሚኒሶታውያን ለኢሳት” በሚል መርህ የቴሌቭዥን ጣቢያውን በገንዘብ ለማጠናከር ማርች 18 በኪኤሊ ኢን ሆቴል በሚደረገው በዚሁ የራት ምሽት ላይ ከታማኝ በየነ እና ከድምጻዊ ...

Read More »

በአወልያ መስጊድ የተጀመረው የእስልምና እምነት ተከታዮች ተቀውሞ ዛሬም የአርብ ቀን ስግደትን ተንተርሶ መካሄዱን ዘጋቢያችን ገለጠ

ጥር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በመስጊዱ ግቢና ከመስጊዱ ውጭ በመሆን ስግደት ከሰገዱ በሁዋላ የመብት ጥያቄዎችን በመፈክር ካሰሙ በሁዋላ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ተስማምተው ተለያይተው ነበር። በዛሬው የጁማ ስግደት ካለፈው ሳምንት የበለጠ ህዝብ የተገኘ ሲሆን፣ የተለያዩ የሙስሊሙ ተወካዮች ንግግር አድርገዋል። ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በዲናችን ( በሀይማኖታችን) አንደራደርም፣ መሞት ካለብንም እንሞታለን ብለው ለተሰብሳቢው ...

Read More »

መድረክ የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣውን ዓዋጅ በመቃወም ጋዜጣዊ መግለጫ በጽ/ቤቱ ውስጥ ሰጥቷል

ጥር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣውን ዓዋጅ ቁጥር 721/2004 በመቃወም ዛሬ  አርብ ረፋዱ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ በጽ/ቤቱ ውስጥ ለሀገር ቤትና ለውጭ ጋዜጠኞች ሰጥቷል፡፡ የመድረክ የአመራር አባላት ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ አቶ ገብሩ ገብረማርያም እና ሌሎችም ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች ...

Read More »

በእነ ውብሸት ታየና ርእዮት አለሙ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ተሟጋቾች እያወገዙት ነው

ጥር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት አስከባሪ ድርጅት በእንግሊዝኛው አጠራር ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ በእነ ውብሸት ታየና ርእዮት አለሙ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያን ምስል የሚያበላሽ ነው። “የኢትዮጵያን የፍትህ ስርአት መረዳት አይቻልም” ያለው ድርጅቱ ፣በ ህገመንግስቱ የተቀመጡትን መብቶች በግልጽ እንደሚጋፋ በሚነገርለት የጸረ ሽብር አዋጅ ተጠቅሞ ጋዜጠኞችን መቅጣት ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ብሎአል። ርእዮትና ውብሸት ወንጀለኞች ባለመሆናቸው በአስቸኳይ ...

Read More »

ኖርዌይ 400 የሚጠጉ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከመንግስት ጋር ስምምነት ማድረጓ ተወቀ

ጥር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኖርዌይ ጋዜጦች እንደዘገቡት ጉዳያቸው ተቀባይነት ያለገኘ ከ400 በላይ ስደተኞች፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ወደ አገራቸው ይመለሳሉ። እስከ መጪው መጋቢት ወር በፈቃደኝነት ወደ አገሩ ለመመለስ የተመዘገበ ስደተኛ ለእያንዳንዱ  40 ሺ ክሮነር ወይም ወደ 6 ሺ ዶላር እንደሚሰጠው  አንድ የፍትህ  ሚኒሰትር ሰራተኛ ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ከማርች 15 በሁዋላ እነዚህን ስደተኞች ከአገር በግዴታ ለማስወጣት እንደሚሞክሩን ተናግረዋል። ...

Read More »

የፌደራሉ ከፍተኛው ሶስተኛው ወንጀል ችሎት በእነኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በተከሰሱላይ ውሳኔ ሰጠ

ጥር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሪቪው ዌብሳይት አዘጋጅ በሆነው ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ላይ እድሜልክ፣ ሂሩት ክፍሌ 19 አመት፣ ውብሸት ታየ 14 አመትና 33 ሺ ብር ፣ ርእዮት አለሙ 14 አመት እና 36 ሺ ብር እንዲሁም ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄርን 17 አመት እስራትና እና 50 ሺ ብር ቅጣት መበየኑን ዳኛ እንዳሻው ገልጠዋል። ውሳኔው አስቀድሞ የተጠበቀ መሆኑን በፍርድ ቤቱ የተገኙት ታዳሚዎች መናገራቸውን ...

Read More »

መድረክ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 በማን አለብኝነት የዜጎችን ንብረት የማፍራት የመሸጥ የመለወጥ እና የመጠቀም መብትን የገፈፈ ነው አለ

ጥር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የዜጎች የንብረት ባለቤትነት መብት ይከበር በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ለስልጣን ማራዘሚያ ተብሎ የወጣው አዋጅ በህገ መንግስት አንቀጽ ስምንት ንኡስ አንቀጽ 3 የኢትዮጵያ ብሄሮች ፣ ብሄረሰቦችና እና ህዝቦች ሉአላዊነታቸው የሚገለጠው በዚህ ህገመንግስት መሰረት በሚመርጣቸው ተወካዮቻቸው እና በቀጥታ በሚያደርጉት ዲሞክራሲያዊ ተስፎ ይሆናል ቢልም ጉዳዩ የሚመለከተው ህዝብ በነጻነትና በግልጽነት አልተወያየበትም፤ እንዲሁም ...

Read More »