ኖርዌይ 400 የሚጠጉ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከመንግስት ጋር ስምምነት ማድረጓ ተወቀ

ጥር 19 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኖርዌይ ጋዜጦች እንደዘገቡት ጉዳያቸው ተቀባይነት ያለገኘ ከ400 በላይ ስደተኞች፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ወደ አገራቸው ይመለሳሉ።

እስከ መጪው መጋቢት ወር በፈቃደኝነት ወደ አገሩ ለመመለስ የተመዘገበ ስደተኛ ለእያንዳንዱ  40 ሺ ክሮነር ወይም ወደ 6 ሺ ዶላር እንደሚሰጠው  አንድ የፍትህ  ሚኒሰትር ሰራተኛ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ ከማርች 15 በሁዋላ እነዚህን ስደተኞች ከአገር በግዴታ ለማስወጣት እንደሚሞክሩን ተናግረዋል። ውሳኔው የብዙ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል። ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት የመለስ መንግስት በውጭ አገር የሚደርስበትን ተቃውሞ ለማዳከም ወሰደው እርምጃ ነው።

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ግን ውሳኔውን እየተቃወሙት ነው። የመለስን መንግስት ላለፉት 20 አመታት ሲቃወሙ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ቢመለሱ ሊደርስባቸው የሚችለው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችለ የሰብአዊ መብቶች ድርጅትቶች ማሳሰብ ጀምረዋል።