የፌደራሉ ከፍተኛው ሶስተኛው ወንጀል ችሎት በእነኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በተከሰሱላይ ውሳኔ ሰጠ

ጥር 18 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሪቪው ዌብሳይት አዘጋጅ በሆነው ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ላይ እድሜልክ፣ ሂሩት ክፍሌ 19 አመት፣ ውብሸት ታየ 14 አመትና 33 ሺ ብር ፣ ርእዮት አለሙ 14 አመት እና 36 ሺ ብር እንዲሁም ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄርን 17 አመት እስራትና እና 50 ሺ ብር ቅጣት መበየኑን ዳኛ እንዳሻው ገልጠዋል።

ውሳኔው አስቀድሞ የተጠበቀ መሆኑን በፍርድ ቤቱ የተገኙት ታዳሚዎች መናገራቸውን ዘጋቢያችን ገልጧል። ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄር  “ወንጀለኛ አይደለሁም ታሪክ አንድ ቀን ንጽህናየን ያረጋገጥልኛል ብሎአል።

የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በጋዜጠኞች፣ በፖለቲካኞችና በነጻ አሳቢ ዜጎች ላይ የተመሰረተውን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ሲፒጄ ክሱ ነጻ ሀሳብን ለማፈን ተብሎ የቀረበ መሆኑን ገልጧል። ሂውማን ራይትስ ወችም እንዲሁ በሽብረተኝነት ስም የተቃውሞ ድምጾችን ለማፈን የተደረገ ሙከራ ነው ብሎአል።