ኢሳት ለማጠናከር በሚኒሶታ ታላቅ የራትና የመዝናኛ ዝግጅት እንደተደገሰ አስተባበሪዎቹ አስታወቁ

ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንን ለማጠናከር በሚኒሶታ ታላቅ የራትና የመዝናኛ ዝግጅት እንደተደገሰ አስተባበሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ በላኩት መግለጫ ላይ አስታወቁ::

በዚህ ዕለት ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነና ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ እንደሚገኙ ታውቋል::

“ሚኒሶታውያን ለኢሳት” በሚል መርህ የቴሌቭዥን ጣቢያውን በገንዘብ ለማጠናከር ማርች 18 በኪኤሊ ኢን ሆቴል በሚደረገው በዚሁ የራት ምሽት ላይ ከታማኝ በየነ እና ከድምጻዊ ተሾመ አሰግድ ሌላ የቶምቦላና ሌሎች የመዝናኛ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሏል::

ማርች 18 በኬሊ ኢን ሆቴል ከ4 ፒኤም ጀምሮ ይደረጋል ለተባለው የራት ምሽት የቶምቦላ እና የመግቢያ ትኬት ሽያጮች ከወዲሁ እንደሚጀመርና ሕዝቡም ትኬቶቹን በመግዛት እንዲተባበር አዘጋጆቹ ጠቁመው በኢሳት ስም የተዘጋጁ ኮፍያዎችና ቲሸርቶችንም በመግዛት የቴሌቭዥን ጣቢያውን እንዲረዱ ጠይቀዋል::

በዚሁ የራት ምሽት ላይ ለኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስለሚደረግ በምሽቱ ላይ የሚገኙ ሰዎች ተዘጋጀው እንዲመጡ አስተባባሪዎቹ ጠይቀዋል::

ታማኝ በየነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየስቴቱና በየሃገራቱ ለኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅቶች ካለምንም ክፍያ በበጎ ፈቃድ እየተገኘ ለሚያደርገው ግልጋሎት ክብር ይገባዋል ያሉት የዚህ ዝግጅት አስተባባሪዎች ፣ ከዚህ ቀደም የሚኒሶታ ወጣቶች በአድዋ ድል በአል ላይ በክብር እንግድነት በተገኘበት ወቅት አርቲስቱን መሸለማቸውን ጠቅሰው የሚኒሶታ ሕዝብ ለታማኝ ክብር እንዳለው ጠቁመዋል::

የራት ምሽቱ እሁድ ማርች 18 ሲደረግ

ዝግጅቱ የሚደረግበት አድራሻም የሚከተለው ነው

161 Saint Anthony Avenue, Saint Paul, Minnesota, 55103