የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መንግስት ላይ ያነጣጠረ ጠንካራ ጥናት ይፋ ሲያደርግ፤የአሁኑ የመጀመሪያ ነው ተብሏል። “ኪሊማንጃሮ ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን ሊሚትድ”ተሰኘ የታንዛኒያ ኮርፖሬሽን ነው ፤ለኮሚሽኑ ጥናቱን የሠራለት። “ሁለተኛው አገር አቀፍ የሙስና ቅኝት”በሚል መሪ ሀሳብ ኩባንያው በ 27 የኢትዮጵያ ተቋማት ዙሪያ በሰራው በዚህ ጥናት፤’6 ሺህ 500 ሰዎችና ተቋማት ቃለ-ምልልስ በመስጠትና ሀሳባቸውን በመግለጽ ተሳታፊ ሆነዋል። እንደ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት፤ በ27 ተቋማት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአንድነት ፓርቲ የወጣቱን ክፍል የሚመሩ፤ ሰባት ወጣቶች ተመረጡ
የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ-ነፃነት ከድርጅቱ ቋሚ ኮሚቴ ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሥር የወጣቶች ንዑስ ኮሚቴ ባለፈው አርብ ተቋቁሟል። ቋሚ ኮሚቴው እንዳለው፤በፓርቲው ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፀደቀው የተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ቋሚ ኮሚቴዎችና ንዑስ ኮሚቴዎች በአዲስ መልክ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ መሠረት በተለያየ ጊዜ እየተገናኙ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩት የአንድነት ወጣቶች ባደረጉት ...
Read More »ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች በሚል ወጪ ካደረገው 10 ሚሊዮን ብር መካከል 9 ሚሊዮን 989 ሺህውን ኢህአዴግ ወሰደው
የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምርጫ ቦርድ ለአስር ፓርቲዎች ለማከፋፈል በሚል ከመንግስት ካዝና ወጪ ካደረገው 10 ሚሊዮን ብር መካከል 9 ሚሊዮን 989 ሺህውን ኢህአዴግ ወሰደው። የተለመደ ህጋዊ ዘረፋ ወይም የእንቁልልጭ ጨዋታ ነው ይሉታል-አንድ የመድረክ ከፍተኛ አመራር ሰሞኑን ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ የፈፀሙትን ተግባር። በቅድሚያ ምርጫ ቦርድ 10 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለመደጎም 10 ሚሊዮን ብር ከመንግስት ካዝና ወጪ ማድረጉን አስታወቀ። ይህ ሢሰማ፤አብዛኛው ...
Read More »መምህራን የነገው ጉባኤ ውጤት ለቀጣይ ትግሉ ወሳኝ ነው ይላሉ
የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የመምህራን ማህበር ላቀረበው የደሞዝ ጭማሪ እስከ ጥር 30 ከመንግስት በኩል መልስ እንዲሰጠው ቢጠይቅም፣ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት መልስ ሊሰጠው ባለመቻሉ በአማራ ክልል በጎንደር እና በጎጃም እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ እስከ ማድረግ የደረሰ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወሳል። አገራቀፉ የመምህራን ማህበር ይህን በተመለከተ ለነገ ሀሙስ የካቲት 15 ቀን 2004 ዓም አስቸኳይ ጉባኤ በራስ ...
Read More »የፓኪስታን ኩባንያ ንብረት የሆነውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ በእሳት ጋየ
የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከመሬታቸውን በሀይል እንዲነሱ የተገደዱ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አርሶአደሮች ተቃውሞዋቸውን ለመግለጥ፣ የፓኪስታን ኩባንያ ንብረት የሆነውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ በእሳት አጋዩ ሪፖርተር እንደዘገበው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የስኳር ልማት ኮርፖሬሽንና የፓኪስታኑ ኩባንያ አል ሐበሻ ስኳር ሊያለሙ ያቀዱትን መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት ከሰው ንክኪ ነፃ ለማድረግ እየተረባረቡ ነው። ይህ በጂማና በምሥራቅ ወለጋ ዞኖች መካከል ከበደሌ ከተማ ወደ ነቀምት ...
Read More »መለስ ዜናዊን በመቃወም በለንደን ታላቅ ሰልፍ እንደሚካሄድ ታወቀ
የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መለስ ዜናዊን የመሰለ አምባገነንና አሸባሪ ዘረኛ መሪ የሰላምና የመረጋጋት ዋስትና ሊሆን እንደማይችል ለአለም ህዝብ እናሳያለን! በሚል መሪ መፈክር ስር በተጠራዉ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ በለንደንና አካባቢዉ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንና የሶማሊያ ተወላጆች እንደሚገኙ የሰልፉ አስተባባሪ ቡድን Net work against Repression & Injustice in Ethiopia ገልጿል። በሶማሊያ ጉዳይ የብሪታኒያ መንግሰት ሐሙስ የካቲት 23 ቀን 2012 በጠራዉ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የአቶ አንዱአለም አራጌ ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል አለ
የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ፣ አቶ አስራት ጣሴ ፣ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ እና አቶ ዳንኤል ተፈራ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው አቶ አንዱአለም አራጌ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓም ከቀኑ 8 ሰአት ገደማ ለህይወቱ የሚያሰጋ ከባድ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገልጠው፣ አቶ አንዱአለም በተፈጸመበት ድብደባ ምክንያት ከፍተኛ የአካልና የስነልቦና ጉዳት ...
Read More »በጋምቤላ ከተገደሉት ሁለት ፖሊሶች መካከል አንዱ የአመራር አባል ነው
የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ባለፈው ሳምንት ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላትና አንድ ሲቪል ሰራተኛ መገደላቸውን መዘገቡ ይታወሳል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ባወጣው ዝርዝር ዘገባ ደግሞ የካቲት 8 ቀን ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ከተገደሉት መካከል አንደኛው የጋምቤላ ልዩ ሀይል አመራር መኮንን ሲሆን ፣ ከቆሰሉት ሲቪሎች መካከል ደግሞ የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሆነው ሳዑዲ ስታር እርሻ ልማት ኩባንያ የፋይናንስ ኃላፊ ...
Read More »በኩዌት ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊ ወገንዋን አንቃ መግደሏን አመነች
የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኩዌት ሃዋሊ በተባለዉ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊ ወገንዋን በገመድ አንቃ እንደገደለች ማመኗን አረብ ታይምስ የመረጃ ምንጭ ገልጧል “የቤት ሰራተኛ እራሷን በገመድ ሰቅላ አጥፍታለች “ በማለት ማንነቱ ካልታወቀ ሰዉ በደረሳቸዉ ጥሪ መሰረት የፀጥታ ሰራተኞችና አስቸኳይ የህክምና ቡድን /ፓራሜዲክስ/ በስፍራዉ ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራዎች በሚደረጉበት ወቅት ሟች እራሷን እንዳልገደለችና ለምን እንደሆነ ...
Read More »በደቡብ የሶማሊያ ግዛቶች ጠንካራ ዉጊያዎች ተቀስቅሰዋል
የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ሶማሊያ ቤይ እና ባኩል ክልሎች ዉስጥ በፌዴራል የሽግግሩ መንግሰትና በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጥምረት እንዲሁም በሌላ በኩል የአልቃይዳ አካል በሆነዉ አልሸባብ መካከል ጠንካራ ዉጊያ በመካሄድ ላይ እንዳለ ተገለፀ። በበርዳሌ ከተማ የሚገኙ የአይን ምስክሮች ለሸበሌ ሚዲያ በስልክ እንደገለፁት የአልሸባብ ተዋጊዎች ወታደራዊ ልምምድ በማድረግና ወደ ይዞታቸዉ እየገፉ በመምጣት ላይ ያሉትን የኢትዮጵያንና የሽግግር መንግሰቱን ወታደሮች ለመግታት መከላከያቸዉን ...
Read More »