የአንድነት ፓርቲ የወጣቱን ክፍል የሚመሩ፤ ሰባት ወጣቶች ተመረጡ

የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ፍኖተ-ነፃነት  ከድርጅቱ ቋሚ ኮሚቴ ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሥር የወጣቶች ንዑስ ኮሚቴ ባለፈው አርብ ተቋቁሟል።

ቋሚ ኮሚቴው እንዳለው፤በፓርቲው ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፀደቀው የተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ቋሚ ኮሚቴዎችና ንዑስ ኮሚቴዎች በአዲስ መልክ ይገኛሉ፡፡

 በዚሁ መሠረት በተለያየ ጊዜ እየተገናኙ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩት የአንድነት ወጣቶች ባደረጉት ምርጫ ሰባት አመራሮችን ሳይመዋል። በተካሄደው ምርጫ “ወጣት አማኑኤል ዮሴፍ ሰብሳቢ፤ ወጣት ኤፍሬም ሰለሞን ም/ሰብሳቢና ወጣት ስንታየሁ ቸኮል ፀሐፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን ፤ወጣት ሚሊዮን ካሳ፣ ወታት ቅዱስ ብርሃኑ፣ወጣት ይማነህ አሰፋና ወጣት ዘላለም ሰለሞን በአመራር አባልነት መመረጣቸው ተገልጿል።

ፓርቲው፤ ወጣቱ  የአንድ ሥርዓት ዋነኛ የለውጥ ኃይል ነው ብሎ  እንደሚያምን በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide