መምህራን የነገው ጉባኤ ውጤት ለቀጣይ ትግሉ ወሳኝ ነው ይላሉ

የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የመምህራን ማህበር ላቀረበው የደሞዝ ጭማሪ እስከ ጥር 30 ከመንግስት በኩል መልስ እንዲሰጠው ቢጠይቅም፣ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት መልስ ሊሰጠው ባለመቻሉ በአማራ ክልል በጎንደር እና በጎጃም እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ እስከ ማድረግ የደረሰ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወሳል።

አገራቀፉ የመምህራን ማህበር ይህን በተመለከተ ለነገ ሀሙስ የካቲት 15 ቀን 2004 ዓም አስቸኳይ ጉባኤ በራስ አምባ ሆቴል ጠርቷል።

በጉባኤው ላይ የተለያዩ ክልሎች መምህራን ተወካዮች እንደሚገኙ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ መምህራን ለኢሳት ተናግረዋል።

በዛሬው እለት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራን፣ በየትምህርት ቤቶቻቸው ስብሰባዎችን ሲያደርጉና ለመምህራን ተወካዮች ጥያቄ አላቸውን ድጋፍ ሲገልጡ እንደነበር መምህራን ገልጠዋል።

የማህበሩ ተወካዮች መንግስት ጥያቄያቸውን ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆነበትን ምክንያት በማወቅ፣ በሂደት ስለሚወዱት እርምጃ ይመክራሉ።

መምህራን እንደሚሉት ግን መንግስት የጠየቁትን የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ፣ ማህበሩ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ በራሳቸው የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት  ዝግጁ ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በደባርቅ ወረዳ ይቅርታ አልጠየቃችሁም ተብለው ከስራ የታገዱት መምህራን አሁንም እገዳው አልተነሳላቸውም።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide