የፓኪስታን ኩባንያ ንብረት የሆነውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ በእሳት ጋየ

የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከመሬታቸውን በሀይል እንዲነሱ የተገደዱ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አርሶአደሮች ተቃውሞዋቸውን ለመግለጥ፣ የፓኪስታን ኩባንያ ንብረት የሆነውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ  በእሳት አጋዩ

 ሪፖርተር እንደዘገበው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የስኳር ልማት ኮርፖሬሽንና የፓኪስታኑ ኩባንያ አል ሐበሻ ስኳር ሊያለሙ ያቀዱትን መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት ከሰው ንክኪ ነፃ ለማድረግ እየተረባረቡ ነው።

ይህ በጂማና በምሥራቅ ወለጋ ዞኖች መካከል ከበደሌ ከተማ ወደ ነቀምት ከተማ በሚወስደው ደዴሳ ሸለቆ የሚገኘው መሬት አካባቢ  100 ሺሕ የሚጠጉ አርሶ አደሮች የሚገኙ ሲሆን እነዚህን አርሶ አደሮች ከቦታቸው አፈናቅሎ ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ሙከራ እየተደረገ ነው።

ከቦታው ላይ መነሳታቸው ያላስደሰታቸው አርሶ አደሮች፣ ተቃውሟቸውን በተለያዩ መንገዶች እየገለጡ ሲሆን ከአንድ ሳምንት በፊት  በፓኪስታኑ ኩባንያ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ላይ እሳት ለቀውበታል። እሳቱን ለማጥፋት ሁለት ቀናት ያክል መውሰዱም ተዘግቧል።
የፓኪስታኑ ኩባንያ አል ሐበሻ ስኳር ፋብሪካ ከሦስት ዓመታት በፊት በአካባቢው 26 ሺሕ ሔክታር መሬት በመረከብ የሸንኮራ አገዳ ልማት በማካሄድ ላይ  ሲሆን ኩባንያው ከተረከበው ቦታ በተጨማሪ 26 ሺሕ ሔክታር መሬት ለማስፋፊያ ይፈልጋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide