.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢምሬት ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያውያን እንስቶች በእሳት አደጋ ሞቱ

ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢምሬት አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲቀጥፍ፣ ከነኚህም አንደኛዋ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ መሆኗን  “ዘ-ናሽናል” የተሰኘው ድረ ገጽ ዘገበ። “አጅማን” ከተማ አቅራቢያ “አል-ሃሚድያ” የተሰኘ አካባቢ በሚገኝ ቪላ ውስጥ በድንገት ቤታቸው ውስጥ እሳት መነሳቱን ያዩት እናት፣ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸው የስልክ ጥሪ ያደርጋሉ። ሆኖም በደቂቃዎች ልዩነት ከእሳቱ ይወጣ በነበረው ...

Read More »

ከፍተኛ የፖሊስ አዛዦች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ህገመንግስቱን ለመናድ ከሞከረ ውጤቱ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠነቀቁ

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጀመሩት ተቃውሞ አንድ አመት ሊመላው ጥቂት ወራቶች ብቻ በቀሩበት በዚህ ጊዜ፣ የፖሊስ አዛዦች ተቃውሞው የሚቀጥል ከሆነ የከፋ ጉዳት ይከተላል ብለዋል። የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ወርቅነህ ገበየሁ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርበው እንደተናገሩት  ፣  ሙስሊሞች ፍላጎታቸውን በሀይል ለመጫን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ርብርብ የማይቆም ከሆነ ውጤቱ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ...

Read More »

ወቅታዊው የዋጋ ግሸበት በ20 በመቶ አሻቀበ

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም  የተመዘገበው የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሸበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ32 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን፣ወቅታዊው የዋጋ ግሸበት ሁኔታ በተመሳሳይ መልኩ ከአምና ሐምሌ ወር ጋር ሲነጻጸር በ20 በመቶ ከፍ ማለቱን  ይፋ አደረገ፡፡ ኤጀንሲው ከትላንት በሰቲያ ይፋ ባደረገው ወርሃዊ ሪፖርቱ እንደገለጸው የ12 ወራት ተንከባላይ ...

Read More »

በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ በእገታው ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ወጣቶች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ታሰሩ በአማራ ክልል የክልሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪዎች፣ የሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ባለስልጣናትና ሌሎች የክብር እንግዶች ተሰርቶ ያልተጠናቀቀ መንገድ ተረክበዋል በማለት በአካባቢው ነዋሪዎች መታገታቸውን ሰንደቅ ዘገበ። እገታውም በድርድርና ውይይት ከተፈታ በኋላ መንገድ ዘግተዋል የተባሉ 12 ወጣቶች በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል። ...

Read More »

ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መፈረጅ ነው ተባለ

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጥቶ ያዋቀረውን ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን እንደመፈረጅ ነው” ሲሉ የጅማ ሀገረ-ስብከት  ሊቀ-ጳጳስ ተናገሩ። ብጹዕ አቡነ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ይህን ያሉት፤   የጅማ ሀገረ ስብከት ጠቅላላ ጉባኤ ሰሞኑን  የ2004 ዓ.ም. ዕቅድና ክንውንን ለመገምገም እና የ2005 ዓ.ም. ዕቅድን ይፋ ለማድግ በጠራው ስብሰባ ላይ ነው። የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ማህበረ-ቅዱሳንን በተደጋጋሚ ፦” በአክራሪነት”ሲወነጅሉ ይደመጣሉ። ጉባኤውን የመሩት ...

Read More »

ቴዲ አፍሮ ለመጪው አዲስ አመት የሙዚቃ ኮንሰርት ያቀርባል

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝነኛው ኢትዮጵያዊ አቀንቃኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለመጪው 2005 የኢትዮጽያዊያን አዲስ አመት ዋዜማ ከአዲካ ኮሚውኒኬሽን ኤንድ ኢቬንትስ ጋር በመተባበር የሙዚቃ ዝግጅቱን በግዮን ሆቴል እንደሚያቀርብ ተገለፀ፡፡ በቅርቡ የወጣውን ጥቁር ሰው የተባለውን አልበሙን አስመልክቶ በሚደረገው በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከ15 ሺ በላይ የቴዲ አድናቂዎች ይታደማሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ ጥቁር ሰው ተብሎ የሚጠራው አልበሙ ለህዝብ ከቀረበ ...

Read More »

አቶ ስዩም መስፍን የአቶ መለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እየሰሩ ነው ተባለ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትና ለ19 አመታት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት አቶ ስዩም መስፍን፤ ከቻይና ተመልሰው በአዲስ አበባ ቤተመንግስት የመሪነቱን ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ፍኖተነጻነት ዘግቧል። አቶ መለስ ከተሰወሩ ጀምሮ “እረፍት ላይ ናቸው፤ ሕክምና እየተከታተሉ ነው፤ አሁንም አመራር የሚሰጡት እሳቸው ናቸው፤ ከሳምንት በሁዋላ ይመለሳሉ” የሚሉ የተለያዩ መግለጫዎች በመንግስት የተሰጡ ሲሆን፤ ኢሳት አቶ መለስ ...

Read More »

የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ተስማሙ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አስራ አንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበረሰባት የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በመከታተል ህዝቡን ለዴሞክራሲያዊ ስርእት ግንባታ ለማብቃት እንዲቻል በጋራ የተደራጀ ትግል ለማድረግ መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ድርጅቶቹ ትናንት ነሀሴ አንድ ቀን ባወጡትና ባሰራጩት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የትብብራቸውና የጋራ ትግላቸው ዓላማ በኢትዮጵያ አንድነት ስር አስተማናኝና፤ በህዝብ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መመስረት ነው። በመግለጫው መሰረት ...

Read More »

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ይጠበቅበታል አሉ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ሊቀመንበርና የመድረክ ም/ሊ/መ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህንን የተናገሩት፤ ከፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። ኢህአዴግ የመንግስት አመራር ለሕዝብ ግልጥ በሆነ መንገድ መከናወን አንዳለበት የሕገመንግስ አንቀጽ 12 ደንግጓል። በተጨማሪም ማንኛውም የሕዝብ ተመራጭ ሀላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ተጠያቂ እንደሚሆን አስፍሯልና ኢህአዴግ ይሄንን ባለማድረጉ ሕዝብ አመኔታ ስላጣ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት ብለዋል፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ። ...

Read More »

አርቲክል 19 አዋጅ ቁጥር 761/2004ን ተቃወመ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱን በለንደን ያደፈረገውና አርቲክል 19 በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያሳለፈውን አዋጅ ቁጥር 761/2004፤ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት የሚገድብ አፋኝ ሕግ መነሆኑን ገለጸ። አርቲክል 19 ሕጉን በመተንተን በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፤ “የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ማጭበርበርን ለመከላከል” በሚል ሽፋን፤ የጸረ-ሽብር ህጉን ማጠናከሪያና፤ መንግስት በአገልግሎቱ ዘርፍ የያዘውን ሞኖፖሊ ለማስጠበቅ የወጣ ነው ሲል ተችቷል። አርቲክል 19፤ የኢትዮጵያ ...

Read More »