Author Archives: Central

የፕሬስ ነጻነት አስከፊ ከሆነባቸው 10 አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ናት ተባለች

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሲፒጄ  የፕሬስ ነጻነት አደጋ ውስጥ የወደቀባቸው 10 የአለም አገራት በማለት በግንባር ቀደምነት ያስቀመጣቸው አገሮች ብራዚል፣ ኢኳዶር፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ፓኪስታን፣ ራሺያ፣ ሶማሊያ ፣ ሶሪያ፣ ቱርክ እና  ቬትናም ናቸው። ኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ በማውጣት ጋዜጠኞች በእስር ቤት እንዲማቅቁ ማድረጓን በዚህ ድርጊቷም   ከኤርትራ በመቀጠል የሁለተኛነት ስፍራ መያዙዋ ተጠቅሷል። አምና 4 ጋዜጠኞች ፣ ከ2007 ጀምሮ ደግሞ በድምሩ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ነጋዴዎች ተቃውሞአቸውን እየገለጡ ነው

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳለው ምርታቸውን ወደ ውጭ አገራት የሚልኩና የሚያስገቡ ነጋዴዎች ፣ መንግስት የጣለባቸውን የአባይ ግድብ ቦንድ ግዢም ሆነ ሌሎች የመንግስት እዳዎችን ለመክፈል የተቸገሩት ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር ተያይዞ ስራቸው በመዳከሙ ነው። የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ኤልሲ ከፍተው እቃዎችን ለማስገባት በማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው ድርጅታቸውን በመዝጋት ሰራተኞቻቸውን ለማሰናበት ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ነጋዴዎች እንደሚገልጹ ...

Read More »

የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያዎች በነዋሪዎች ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ኢሳት ይፋ አደረገ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምእራባዊያን አቆጣጠር ማርች 16፣ 2012 በኢትዮጵያዋ የሶማሊ ክልል ፣ በጋሻሞ ወረዳ በክልሉ መንግስት የሚተዳዳሩት ልዩ ሚሊሺያዎች አንድ ወጣት ይገድላሉ። የወጣቱን መሞት ተከትሎ ከወረዳው ህዝብ የተውጣጡ ሰዎች ” አሁንስ በቃ ” በማለት ገዳዩን የሚሊሺያ አባል ተከታትለው  ይገድሉታል። የልዩ ሚሊሺያ ሀይሉ አባላት በተደጋጋሚ ወደ አካባቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሴቶችን ሲደፍሩና ንብረት ሲዘርፉ መቆየታቸውን የአካባቢው  ሰዎች ...

Read More »

ከዋልድባ ተሰደው በጎንደር መድሀኒዓለም ቤ/ክ የተጠለሉ 48 ባህታዊያን ታፍሰው ተወሰዱ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የጎንደር ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ እንደዘገበው  ባህታዊያኑ ከጥር 2 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ  መድሀኒአለም ቤ/ክርስቲያን ውስጥ በሚገኝ አንድ አዳራሽ ውስጥ ከሰዎች ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ በጥብቅ ቁጥጥር  ሲጠበቁ  ቆይቷል። በዛሬው እለት ባህታዊያኑ ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ በአውቶቡስ ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። የአካባቢው ወጣቶች ከባህታዊያኑ ጋር አብረን እንሄዳለን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ ...

Read More »

የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት ሊከፈል ነው

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ሁለት ቦታ ለመክፈል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በቂ ጥናት ያልተደረገበትና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ባለመሆኑ መንግሥት ዕርምጃውን  እንዲገታ እና ዳግም እንዲያጤን  በዓለማቀፍ አበዳሪዎች መጠየቁን ሪፖርተር ዘገባ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች ዓለም አቀፍ አበዳሪዎችም ኮርፖሬሽኑ የመዋቅር ለውጥ የሚደረግበት ከሆነ ብድር ላለመስጠት እያንገራገሩ ናቸው፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ ...

Read More »

በደቡብ ክልል በማጅራት ግትር በሽታ አሁንም ሰዎች እየሞቱ ነው

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጠው በሲዳማ ዞን በሰበዲኖ ወረዳ በበሽታው ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ በአዋሳ ከተማ ደግሞ አንድ ታዳጊ ወጣት ሞቷል።  ከመንግስት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዞኑ ከ100 በላይ ሰዎች በበሽታው በመያዛቸው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። በአዋሳ በሁሉም ጤና ማእከላት ክትባት ለመስጠት እየተሞከረ ሲሆን፣ በጭኮ፣ አለታ ወንዶ፣ ይርጋለም፣ በደራ እና  በቤኔሳ ክትባቱ ባለመጀመሩ ህዝቡ መደናገጡ ታውቋል።

Read More »

አንድነት ፓርቲ በአራት ወራት ውስጥ 1 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዷል

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ለመገናኛ ብዙሀን ባሰራጨው መረጃ፣ ገንዘቡን የሚያሰባስበው፣ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለው ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ የመጣውን ፍኖተ-ነጻነት ጋዜጣን ለማተም ፈቃደኛ ባለመሆኑ የራሱን ማተሚያ ቤት ለማቋቋም ነው። ፓርቲው ብቸኛ ልሳኑ የሆነውን ፍኖተ-ነጻነትን በመንግስት የአፈና ፖሊሲ የተነሳ ለማሳተም እንዳልቻለ ገልጿል። ይህንን ችግርም ለመቅረፍ ድርጅቱ በሚቀጥሉት አራት ወራት 1 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ የህግ የበላይነት ጭላንጭል እየተዳፈ ነው አለ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ  መንግስት ከሙስሊም ጥያቄ አቅራቢዎች ተወካዮች ጋር ሲወያይ ከቆየ በሁዋላ አብዛኞቹን በሽብረተኝነት ከሶ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ ማድረጉንና ክሳቸውም እየታየ ባለበት ወቅት በህገ መንግስቱ የተደነገገውን ማንም ሰው ወንጀለኛነቱ በፍርድ ቤት እስኪረጋገጥ ድረስ እንደንጹህ የመቆጠር መብትን በመታገስና ተከሳሾች ራሳቸው ጥፋተኞች መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ በሚያስገድድ ሁኔታ የዞጎችን ስእብና የሚያራክስ ዘጋቢ ማሳየቱን ገልጿል። ፓርቲው ፣ ...

Read More »

መንግስት 850 ሺ ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ እየገባ ነው አለ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 21 አመታት ኢትዮጵያን በምግብ እራሱዋን እንደሚያስችል ቃል ሲገባ የነበረው የኢህአዴግ መንግስት በቅርቡ ከውጭ የተገዛውን 850 ሺ ኩንታል ስንዴ እንደሚያስገባ የእህል ንግድ ድርጅት አስታውቋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም  5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ አስገብቶ ማከፋፈሉን የገለጠ ሲሆን፣ የስንዴው መግባትም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የእህል ዋጋ ንረት ለማለዘብ እንደረዳ ድርጅቱ አስታውቋል። መንግስት በአሁኑ ጊዜ በግብርናው ዘርፍ ...

Read More »

ከአርቲስት ታምራት ሞላ ቀብር ጋር በተያያዘ ቅሬታ ቀረበ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ እንደ ቅርስ ከሚታወቁት አንጋፋ ድምፃውያን አንዱ የሆነው አርቲስት ታምራት ሞላ የምድር ጦር ሰራዊት ኦኬስትራ ማርሽ ሊዘጋጅለት ይገባ ነበር ሲል ሌላው አንጋፋ አርቲስት ዳምጠው አየለ ቅሬታውን ገለጠ። አርቲስት ዳምጠው እርሱ በሚቀጠርበት ጊዜ የሙያ ገምጋሚው አርቲስት ታምራት እንደነበር ገልጾ፣ ለ30 አመታት ያክል ሳይለያዩ በምድር ጦር አገልግሎት መስጠታቸውን አውስቷል። እኛ የምንሰራው ለአገር፣ ለሙያ ...

Read More »