በደቡብ ክልል በማጅራት ግትር በሽታ አሁንም ሰዎች እየሞቱ ነው

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጠው በሲዳማ ዞን በሰበዲኖ ወረዳ በበሽታው ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ በአዋሳ ከተማ ደግሞ አንድ ታዳጊ ወጣት ሞቷል።  ከመንግስት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዞኑ ከ100 በላይ ሰዎች በበሽታው በመያዛቸው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። በአዋሳ በሁሉም ጤና ማእከላት ክትባት ለመስጠት እየተሞከረ ሲሆን፣ በጭኮ፣ አለታ ወንዶ፣ ይርጋለም፣ በደራ እና  በቤኔሳ ክትባቱ ባለመጀመሩ ህዝቡ መደናገጡ ታውቋል።