የፕሬስ ነጻነት አስከፊ ከሆነባቸው 10 አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ናት ተባለች

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሲፒጄ  የፕሬስ ነጻነት አደጋ ውስጥ የወደቀባቸው 10 የአለም አገራት በማለት በግንባር ቀደምነት ያስቀመጣቸው አገሮች ብራዚል፣ ኢኳዶር፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ፓኪስታን፣ ራሺያ፣ ሶማሊያ ፣ ሶሪያ፣ ቱርክ እና  ቬትናም ናቸው።

ኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ በማውጣት ጋዜጠኞች በእስር ቤት እንዲማቅቁ ማድረጓን በዚህ ድርጊቷም   ከኤርትራ በመቀጠል የሁለተኛነት ስፍራ መያዙዋ ተጠቅሷል።

አምና 4 ጋዜጠኞች ፣ ከ2007 ጀምሮ ደግሞ በድምሩ 49 ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን፣ ከአለም አገራት ጋር ሲተያይ አገሪቱ በሶስተኛ ደረጃ እንድትታይ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

በአገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች የሀይለማርያም ደሳለኝ መንግስት በፕሬስ ላይ የሚታየውን አፈና ይለውጠዋል ብለው እንደማያስቡ  ሲፒጄ ገልጿል።