ከዋልድባ ተሰደው በጎንደር መድሀኒዓለም ቤ/ክ የተጠለሉ 48 ባህታዊያን ታፍሰው ተወሰዱ

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የጎንደር ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ እንደዘገበው  ባህታዊያኑ ከጥር 2 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ  መድሀኒአለም ቤ/ክርስቲያን ውስጥ በሚገኝ አንድ አዳራሽ ውስጥ ከሰዎች ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ በጥብቅ ቁጥጥር  ሲጠበቁ  ቆይቷል።

በዛሬው እለት ባህታዊያኑ ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ በአውቶቡስ ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። የአካባቢው ወጣቶች ከባህታዊያኑ ጋር አብረን እንሄዳለን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።

መነኮሳቱ ገዳሙን ለቀው የተሰደዱት የጸለምት አስተዳዳሪ የትግራይ ተወላጅ እስካልሆናችሁና የክልሉን መታወቂያ እስካላወጣችሁ ድረስ በገዳሙ አትኖሩም በሚል ስላባረራቸው መሆኑን 31 ባህታዊያን በጋራ

የዚህን ዘገባ ሙሉ ዝርዝር በነገው እለት እናቀርባለን።