Author Archives: Central

በሙኒክ የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ የሰብአዊ መብቶች ተማጓች አርቲስት ታማኝ በየነ እና ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በተገኙበት የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢ ዝግጅት ከተጠበቀው ሰው በላይ በመምጣቱ ቦታ መጥበቡን አዘጋጆች ለኢሳት ገልጸዋል። የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው አቶ አበበ መለሰ እንደተናገረው በጀርመን የኢትዮጵያውያን ዝግጅት ታሪክ ይህን ያክል ህዝብ ሲሳተፍ ማየቱ የመጀመሪያው ነው። ነገ እሁድ ፌብሩዋሪ 17 ደግሞ አርቲስት ታማኝ በየነ በኢሳት መቀመጫ ...

Read More »

በዳውሮ ዞን የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት የእና አቶ ዱባል ገበየሁን እስር ተከትሎ የዩኒቨርስቲ መምህራን እና የመንግስት ሰራተኖች እየታሰሩ ነው። ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አቶ አባተ ኡካ፣ ከጅማ ዩኒቨርስቲ  አቶ አብረሀም ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል። በክልሉ የሚታየው ውጥረት መንግስትን በእጅጉ እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሎአል። የአቶ ዱባለ ገበየሁ ዘመዶችና ወዳጆችም እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣  ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በአሸባሪነት ክስ እንደሚቀርብባቸው ...

Read More »

አዲስ አበባ ውስጥ መስማትና መናገር የማትችል ወጣት በፖሊስ ተደፈረች

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደብረ ብርሀን ብሎግ ስፖት በድምጽ በማስደገፍ ይፋ እንዳደረገው ዜና በአዲስ አበባ ጎዳና  ላይ መስማት የተሳናትና ዝግመት ያለባት ታዳጊ ወጣት ብቻዋን መንገድ ላይ ስትጓዝና መሄጃ ጥፍቷት ስትደናገር አንድ ግለሰብ ያገኛታል። ግለሰቡም፦ ይቺ ልጅ ትንሽ ከመሸ ጥቃት ይደርስባታል ብሎ በማሰብ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በመሆን  በ አቅራቢያው ወደሚገኝ  ፖሊስ ጣቢያ ይወስዳታል። በአደራ የተረከበው  ፖሊስ “ነገ ቤተሰቦቿ ...

Read More »

ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀው መንግስት ሞባይል ኔትወርክ አቋርጦ እንደነበር ታወቀ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው ዕለት ከተካሄደው ጁምአ ጸሎት ስርዓት ጋር ረብሻና ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት በተያያዘ በአዲስአበባ ዛሬ ማለዳ ላይ የሞይባል አገልግሎት ከአምስት ሰዓታት በላይ ተቋርጦ እንደነበር ተሰማ፡፡ በዛሬው ዕለት ሙስሊሙ ህብረተሰብ በመደበኛ የጁምአ ፕሮግራሙ እርስ በእርስ በመጠራራት እና አጫጭር የስልክ መልዕክቶችን በመለዋወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊያደርግ ይችላል በሚል ግምት ሐሙስ ለዓርብ አጥቢያ በግምት ከለሊቱ ...

Read More »

የአማራ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ተከሰሰ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል የሚሰሩ የተለያዩ የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኞች እና የኢህአዴግ አባላት ለኢሳት እንደገለጡት ከመሬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ በክልሉ የሚታየው ከፍተኛ ሙስና ሊገታ ያልቻለው የክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሙስናው ዋና ተዋናይ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ሰራተኞቹ ከወራት በፊት ከፍተኛ የዜና ሽፋን ተሰጥቶት የነበረውን የሙስና ጉዳይ በማንሳት እንደገለጡት ፣ የክልሉ ባለስልጣናት ከባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ...

Read More »

የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ይግባኝ ተራዘመ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፌደራሉ አቃቤ ህግ በሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም 6 ኪሎ ለሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛ በጠየቁት መሰረት ...

Read More »

በሳውዲ አረብያ የታሰሩ 43 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አሁንም እንደታሰሩ ነው

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት በሳውዲ አረብያ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ከዋሉት 43 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አለመፈታታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ኢትዮጵያውያኑ ሳምንታዊ የአምልኮ ጉባኤያቸውን ለማካሄድ በተሰባሰቡበት ወቅት ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት። ምንም እንኳ ፖሊስ ቃላቸውን ቢቀበልም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊመራው እንዳልቻለ ታውቋል። አንድ የእምነቱ ተከታይ እንደገለጠው፣ ኢትዮጵያውኑ ነገ  ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ  ሊሰጣቸው ይችላል ሲል ...

Read More »

በሩሲያ አንድ ጅራታም ኮከብ ወደቀ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ጅራታም ኮከብ ወይም ሜትዮሩ የወደቀው በሩሲያ የኡራል ተራራ ላይ ሲሆን፣ 950 የሚሆኑ ሰዎች ተጎድተዋል። አብዛኞቹ በተለያዩ መጠኖች ቁስለት የደረሰባቸው ሲሆን፣ 46 ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ፑቲን ሜትዮሩ በመኖሪያ ሰፈር ላይ ባለመውደቁ እግዚአብሄርን አመስገንዋል። ሜትዮሩ ከመሬት ጋር በሚላተምበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ፍንዳታ መሰማቱ ታውቋል። አንዳንድ ፖለቲከኞች በበኩላቸው የወደቀው ሜትዮር ሳይሆን የአሜሪካ አዲስ የጦር ...

Read More »

በጎንደር መድሀኒዓለም ቤ/ክ የተጠለሉ 48 ባህታዊያንን ወደ መጡበት ዋልድባ መወሰዳቸው ታወቀ

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባህታዊያኑ ከጥር 2 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ በጎንደር ከተማ በሚገኝ መድሀኒአለም ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገላቸው ተጠልለው ቆይተዋል። ትናንት ባህታዊያኑ ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ በአውቶቡስ ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የዘገብን ሲሆን፣ ወኪላችን ሂደቱን ተከታትሎ እንደዘገበው ባህታዊያኑ የተወሰዱት ፣ ከተለያዩ የአማራ ክልል የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ችግሩን በሽምግልና እንፈታዋለን የሚል ሀሳብ ካቀረቡ በሁዋላ ነው። ...

Read More »

33ት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጂሀዳዊ ሀረካትን ተብሎ በኢቲቪ የቀረበውን ፊልም አወገዙ

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው  የአዲስ አበባ እና የአካባቢ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑ 33ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ” መንግስት ጅሀዳዊ ሃረካት በሚል ርእስ በኢቲቪ ያስተላለፈው ፊልም ዋና አላማ የህዝብን የዘመናት አብሮነት በመሸርሸርና የመብት ጥያቄ የሚያነሳን ከሽብረተኝነትና ጦርነት ጋር በማያያዝ ህዝብን ለማሸማቀቅ ሆኖ በውጤቱም ህዝብ በአገሩ ላይ ያለውን የባለቤትነትና ሃላፊነት ስሜት በመናድ አንገት ማስደፋትና መብት ጠያቂዎችን በመነጣጠልና መከፋፈል ጥያቄዎችን ማደፈንና ...

Read More »