ግንቦት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት ተማሪዎችን አስሮ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የኦሮምያ ፖሊስና የጸረ ሽብር ግብረሃይል በጋራ አስታውቀዋል። በአለማያ ከደረሰው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘም እጃቸው አለበት ብሎ የጠረጠራቸውን ሰዎች መያዙን መንግስት ገልጿል። አጠቃላይ ግጭቱን የቀሰቀሱትን ሃይሎች ለመያዝም ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ከፖሊስ እና ጸረ ሽብር ግብረ ሃይሉ የተሰጠው መግለጫ፣ ...
Read More »Author Archives: Central
በወለጋ ዩኒቨርስቲ ፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መገደላቸው ተሰማ
ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ በተማሪዎቹ ላይ በወሰደው ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ 3 ተማሪዎች መገደላቸውን የኢሳት የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና የፌደራል ፖሊሶች ተማሪዎቹ የመጀመሪያ እርዳታ እንዳያገኙ መከልከላቸውን ተከትሎ በሃኪሞችና በፖሊስ አዛዦች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደበር ምንጮች አክለው ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ሰራተኞች በአቋማቸው በመጽናታቸው ተማሪዎች ህክምና ለማግኘት መቻላቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ...
Read More »መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ
ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የኢህአዴግመንግስትሰላማዊየተቃውሞእንቅስቃሴዎችን በኃይልለማፈንየሚወስዳቸውየኃይልእርምጃዎችእናተፅዕኖዎችበአስቸኳይቆመውየሀገራችንወቅታዊእናመሰረታዊችግሮችበሰላማዊእናዴሞክራሲያዊአግባብእንዲፈቱመንግስትንለመጠየቅ” ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ምየሚካሄድሰላማዊሰልፍመጥራቱን አስታውቋል። የአዲስአበባእናየአከባቢዋነዋሪዎችከጧቱ 3 ሰአት ላይ ከግንፍሌወንዝድልድይተነስቶበየካክ/ከተማወረዳ 8 ኳስሜዳ ወይም ታቦትማደሪያበሚባለውየመሰብሰቢያቦታ ላይ ፍጻሜውን በሚያደርገው የሰላማዊሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞዋቸውን እንዲያሰሙ መድረክ ጠይቋል። “ሰላማዊናዲሞክራሲያዊየመቃወምመብታችንንበኃይልማፈንይቁም፣ ሰላማዊተቃዋሚዎችንማሰር፣መግደልእናማሰቃየትይቁም፣ በመሰብሰብ፣በመደራጀት፣ሰላማዊሰልፎችንበማድረግ፣ሀሳብንበነፃነትበመግለጽእናመረጃማግኘትህገመንግስታዊመብታችንላይየሚፈፀሙትተፅዕኖዎችይቁሙ “በሚሉእናበመሳሰሉትአላማዎች የ ግንቦት 10 የተቃውሞ ሰልፍ መዘጋጀቱን መድረክ አስታውቋል።
Read More »የጸረሙስናኮምሽን 204 ሚሊየንብርግምትያለውመሬትበግለሰቦች እጅ መያዙን አስታወቀ፡፡
ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኮምሽኑ የአስርወራትሪፖርትእንደሚያስረዳውየሐሰተኛየመሬትባለይዞታነት ሰነድበማዘጋጀትናሕጋዊቅድመሁኔታላላሟሉሰዎችየመንግስትመሬትአለአግባብበመስጠትበሶስትምርመራዎች በ12 ተጠርጣሪዎችላይምርመራአካሂዶለአቃቤሕግውሳኔአቅርቦአል፡፡ በዚህየምርመራስራበተሰበሰበውመረጃ መሰረትግምቱ ብር 203 ሚሊየን 549 ሺ144 የሆነ 155 ሺ 208 ካሬሜትርየመንግስትመሬትበግለሰቦች አለአግባብመያዙንጠቁሟል፡፡ ሆኖምይህመሬትበየትኛውክልልወይምቦታእንደሚገኝሪፖርቱአልጠቆመም፡፡ በተጨማሪምበእያንዳንዱጉዳይከብር 45 ሺእስከ 350 ሺድረስጉቦበመስጠትናበመቀበልበሃሰተኛየፍርድቤትትዕዛዝፍርደኞችንበለቀቁየፌዴራልማረሚያቤቶችመካከለኛአመራሮችእናይህንኑሐሰተኛየፍርድቤትውሳኔበገንዘብበማሰራትከማረሚያቤትአለአግባብበወጡታራሚዎችናተባባሪዎቻቸውላይምርመራተጣርቶክስእንደተመሰረተባቸውምሪፖርቱያስታውሳል፡፡ በሙሰኞችየተመዘበረንሐብትለማስመለስይቻልዘንድባለፉትአስርወራት 72 ሺ 673 ካሬሜትርመሬት፣152ተሸከርካሪዎች፣137 መኖሪያቤቶች፣3 ህንጻዎች፣ 1 ፋብሪካ፣ 320 ሚሊየንብርበጥሬገንዘብ፣ 19 ነጥብ 3ሚሊየንየሚያወጣአክስዮን፣ 18 ሚሊየንብርየሚያወጣቦንድ፣ 5 የንግድመደብሮች፣ 12 የነዳጅመጫኛቦቴዎችበፍ/ቤትትዕዛዝእንዲታገዱመደረጉንሪፖርቱጠቁሟል። ኮሚሽኑየሚወርሳቸውንንብረቶችከማስተዳደርአቅምማነስጋርበተያያዘበተለይተሸከርካሪዎችበየቦታውበስብሰውናሳርበቅሎባቸውየሚገኙመሆኑይታወቃል፡፡
Read More »በአዲስ አበባ ከትናንት ጀምሮ ህገወጥ የተባሉ ቤቶች እየፈረሱ ነው
ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስአበባዓለም ባንክተብሎበሚታወቅአካባቢወደታጠቅጦርሰፈርአቅራቢያሕገወጥቤቶችናቸውበሚልበርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎች አብዛኛዎቹቤቶችከተገነቡከ10 ዓመታት በላይእንደሆናቸውየገለጹሲሆንበአሁኑወቅትበፖሊስሃይልቤታቸውበላያቸውላይእየፈረሰመሆኑን ተናግረዋል፡፡ በፖሊስና በነዋሪዎች መካካል በተፈጠረ አለመግባባትም እስካሁን ከ40 ያላነሱ ሰዎች መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አንዳንድ ነዋሪዎች ፖሊስ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ጭካኔ የተሞላበት ነበር ሲሉ ገልጸዋል
Read More »የሴሌንዳዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተዘጋ
ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድሬዳዋ ከተማ ከ 2 ዓመታት በፊት የተቋቋመው ሰሌንደዋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከ 1 ሺ ያላነሱ ሰራተኞችን በትኖ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፋብሪካውን ዘግቶ ወደ ሀገሩ ቱርክ መመለሱ ታውቋል። በመንግሥት 48 % እና በሚ/ር ሱሌይማን 52 % ኢንቨስትመንት ድርሻ የተቋቋመ ቢሆንም ባለሀብቱ ከመንግስት ብድር አልተሰጠኝም በሚል ሰበብ ብቻ ፋብሪካውን ዘግቶ ሊሄድ ችሏል፡፡ የተበተነው ሰራተኛ ለከፍተኛ ...
Read More »የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ
ግንቦት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ጓደኞቻቸው እንዲፈቱላቸው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ የነበሩ የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ወደ ግቢው ዘልቀው በገቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሲደበደቡ መዋላቸውን ተማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። የግቢው ተማሪዎች ጥያቄያቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማቅረብ ላይ ሳሉ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ውስጥ ሰብረው በመግባትና የጪስ ቦንብ በመወርወር ተማሪውን በሰደፍና በዱላ መደብደባቸውን ተማሪዎች ...
Read More »አዲስ አበባ በአንበጣ መንጋ መወረሩዋን ነዋሪዎች ገለጹ
ግንቦት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የአንበጣ መንጋ አዲስ አበባን መውረሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ኮተቤ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸው በአምበጣ መንጋ እንደተወረረ ገልጸዋል። በቅርቡም እንዲሁ በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ተመሳሳይ የአምበጣ መንጋ ወረርሽኝ ታይቶ ነበር። የአንበጣ መንጋው ከየት አካባቢ እንደመጣ ለማወቅ አልተቻለም። በአዲስ አበባ የአምበጣ ወረርሽኝ የተለመደ ነገር አለመሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
Read More »የሥነምግባርናፀረሙስናኮሚሽንኮሚሽነርአቶአሊሱለይማን፦‹ዛቻናማስፈራራትይገጥሙናል›› አሉ።
ግንቦት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኮሚሽነሩይህንያሉትየመስሪያቤታቸውንየአስርወራትየሥራአፈገፃፀምሪፖርትሰሞኑንለህዝብተወካዮችምክርቤትባቀረቡበትወቅትመሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል። አቶዓሊሱሌይማንበሪፖርታቸውኮሚሽኑንእያጋጠሙስላሉዋናዋናችግሮችአብራርተዋል፡፡የመፈጸምናየማስፈጸምአቅምውስንነት፣የሰውኃይልፍልሰት፣አንዳንድየመንግሥትተቋማትኮሚሽኑለሚያቀርባቸውየማሻሻያሐሳቦችተባባሪአለመሆንናየመስክተሽከርካሪዎችእጥረትኮሚሽኑንካጋጠሙችግሮችመካከልዋነኞቹመሆናቸውንተናግረዋል፡፡ የኮሚሽነሩንሪፖርትተከትሎከተሰነዘሩአስተያዬቶቸናጥያቄዎችመካከልበቀድሞውየትምህርትሚኒስትርዲኤታበዶክተርአድሃኖምየተሰነዘረውጥያቄ አዘልአስተያዬትአንዱነው።በኮሚሽነሩችግሮችተብለውየተዘረዘሩትክብደትየሌላቸውሆኖእንደተሰማቸውየገለጹትዶ/ርአድሃኖ፤ የኮሚሽኑችግሮችእነዚህብቻከሆኑየሚያስደስትነው” ብለዋል። ዶ/ርአድሃኖለሰጡትጥያቄአዘልአስተያየትየጸረ-ሙስናኮሚሽንኮሚሽነሩበሰጡትምላሽ፦‹ለምክርቤቱመቅረብየሚገባነውብለንስላላመንእንጂዛቻናማስፈራራትየመሳሰሉትችግሮችምአሉ፤›› ብለዋል፡፡ይሁንእንጂየትኞቹየመንግስትአስፈጻሚአካላትዛቻናማስፈራራትንእንደሰነዘሩባቸውበዝርዝርአልገለጹም። ከምስረታውጀምሮእስካሁንድረስየቁኝጮባለስልጣናትየፖለቲካመሳሪያሆኖየዘለቀውየጸረ-ሙስናኮሚሽንበብዙዎችዘንድ “ጥርስየሌለውአንበሳ” በሚልቅጽልስም ይታወቃል።
Read More »የጅቡቲ መንግስት 30 ስደተኞችን ለኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፎ ሰጠ
ግንቦት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገሪቱ መንግስት ከኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር ያሰራቸውን ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ ወደ ሚፈጸምበት ጅጅጋ እስር ቤት መውሰዱን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር አስታውቋል። ግንባሩ እንዳለው እርምጃው የተወሰደው የኦጋዴን ተወላጅ የዳያስፖራ አባላት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ካወገዙ በሁዋላ ነው። ጅቡቲ በኦጋዴን አካባቢ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደምትደግፍ ግንባሩ አስታውቆ፣ ጅቡቲ የኦጋዴን ...
Read More »