የሴሌንዳዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተዘጋ

ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድሬዳዋ ከተማ ከ 2 ዓመታት በፊት   የተቋቋመው ሰሌንደዋ ጨርቃ ጨርቅ  ፋብሪካ  ከ 1 ሺ ያላነሱ  ሰራተኞችን በትኖ  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፋብሪካውን ዘግቶ ወደ ሀገሩ ቱርክ መመለሱ ታውቋል።

በመንግሥት 48 %  እና በሚ/ር ሱሌይማን 52 % ኢንቨስትመንት ድርሻ የተቋቋመ ቢሆንም  ባለሀብቱ ከመንግስት ብድር አልተሰጠኝም በሚል ሰበብ ብቻ ፋብሪካውን ዘግቶ  ሊሄድ ችሏል፡፡

የተበተነው ሰራተኛ ለከፍተኛ ችግር መደራጉን ለኢሳት የደረሰው ዜና ያመለክታል።

በ200 ዓ.ም እንዲሁ መንግስት የድሬዳዋን ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን ለቱርካዊው ባለሃበት ለሚ/ር  አቴላ በለዝ ሸጦ የነበረ ቢሆንም ባለሃብቱ ሰራተኞች የሠሩበትን የሁለት ወር ደመወዝ ሳይከፍል ፋብሪካውን ዘግቶ ወደ አገሩ መመለሱ ይታወቃል፡፡