አዲስ አበባ በአንበጣ መንጋ መወረሩዋን ነዋሪዎች ገለጹ

ግንቦት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የአንበጣ መንጋ አዲስ አበባን መውረሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ኮተቤ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸው በአምበጣ መንጋ እንደተወረረ ገልጸዋል።

በቅርቡም እንዲሁ በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ተመሳሳይ የአምበጣ መንጋ ወረርሽኝ ታይቶ ነበር።

የአንበጣ መንጋው ከየት አካባቢ እንደመጣ ለማወቅ አልተቻለም።

በአዲስ አበባ የአምበጣ ወረርሽኝ የተለመደ ነገር አለመሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።