ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ እስራኤል በእግር ሲጓዙ ህይወታቸዉን ላጡ አራት ሺህ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊያን የመታሰቢያ ሃዉልት እንዲሰራ የእስራኤል የሚኒስትሮች ም/ቤት መወሰኑን ጄ ዊክሊ የተባለዉ የእየሩሳሌም ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘግቧል። በእየሩሳሌም ኸርዝል ተራራ ላይ በሚሰራዉ በዚህ የመታሰቢያ ሃዉልት ላይ የሞቱት ቤተ አስራኤላዊያን የስም ዝርዝር እንደሚቀረፅ ተመልክቷል። “የመታሰቢያዉ ሃዉልት መሰራት 130 ሺህ የሚሆን ቁጥር ያላቸዉ ወንዶች፤ ሴቶች፤ ህፃናት እና ...
Read More »Author Archives: Central
አርሶአደሩ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ 500 ብር እንዲያወጣ፣ ለህዝብ ማመላለሻ መኪና ክላውዲዮ የሚያወጡ ደግሞ 7 ሺ ብር እንዲከፍሉ መመሪያ ወጣ
ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝቅተኛው አርሶአደር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ 500 ብር እንዲያወጣ፣ ለህዝብ ማመላለሻ መኪና ክላውዲዮ የሚያወጡ ደግሞ 7 ሺ ብር እንዲከፍሉ እንዲሁም መምሀራን የደሞዛቸውን 100 ፐርሰንት እንዲከፍሉ የሚያደርግ መመሪያ ወጣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ዝቅተኛ የተባለው ገበሬ ለግድቡ ማሰሪያ አምስት መቶ ብር እንዲያዋጣ፣ የተሻለ ገቢ አለው የተባለው ገበሬ ደግሞ ከ1 ሺ ብር ጀምሮ እንደዬደረጃው እንዲከፍል ይደረጋል። የወረዳ ...
Read More »የኦክላንድ የምርምር ተቋም በኢትዮጵያ የሚደረገው የመሬት ሽያጭ መቆም እንዳለበት ገለጠ
ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የኦክላንድ የምርምር ተቋም በኢትዮጵያ የሚደረገው የመሬት ሽያጭ መቆም እንዳለበት ገለጠ፣ በጋምቤላ መሬት የሚወስዱትና ንግዱን የተቆጣጠሩት የአንድ ብሄር ሰዎች መሆናቸውንም አጋለጠ ተቀማጭነቱ በካሊፎርኒያ አሜሪካ የሆነው የኦክላንድ የምርምር ተቋም መስራችና የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አኑራዳ ሚታል ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ የሚቸበችበው መሬት፣ ለአገሪቱ ...
Read More »”ኦነግ ነፃ ድርጅት እንጂ የወያኔ ተለጣፊ ቡድን አይደለም” ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ገለጸ
ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “የኦነግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት፤ ዛሬ ወያኔ ከኤርትራ መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት ስለተቋረጠ የሚቋረጥ አይሆንም፤ኦነግ በሁለት እግሮቹ ራሱን ችሎ የቆመና የተመሰረተበትን ህዝባዊ አላማ በነፃነት የሚያራምድ ነፃ ድርጅት እንጂ፤የወያኔ ተለጣፊ ቡድን አይደለም”ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ገለጸ። “ኦነግ ኤርትራ ውስጥ ተመስርቶ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እስኪመስል ድረስ፤የወያኔ ቡድን ስለ ኦነግ ባነሳ ቁጥር የኤርትራን ስም ሳያነሳ ያለፈበት ጊዜ የለም” ...
Read More »የአቶ መለስ መንግሥት በ”ሽብርተኝነት‘ በወነጀላቸው ስምንት ተከሳሾች ላይ በዐቃቤ- ሕግ ተሸሻለ የተባለው የክስ ቻርጅ ዛሬ ቀረበ
ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግሥት በ”ሽብርተኝነት‘ ከወነጀላቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢያን ኢትዮጵያዊያን ውስጥ ሀገር ውስጥ በእሥር ላይ በሚገኙት ስምንት ተከሳሾች ላይ በዐቃቤ- ሕግ ተሸሻለ የተባለውን የክስ ቻርጅ ዛሬ አቀረበ፡፡ ይህ ተሸሻለ የተባለው የክስ ቻርጅ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር እና ዋና አዘጋጅ የሆኑት ዐብይ ተክለማርያምና መስፍን ነጋሽን አያካትትም ተብሏል፡፡ እነ ...
Read More »የታሪክ ምሁሩ ጆን ማርካኪስ ህወሀት ከቀድሞው የደርግና የሀይለ ስላሴ ስርአቶች ለመማር ባለመቻሉ፣ ለመውደቅ ተቃርቧል አሉ
ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ መጽሀፎችን በመጻፍ እውቅና ያተረፉት ታወቂው የፖለቲካና ታሪክ ምሁር ጆን ማርካኪስ ፣ ህወሀት መራሹ መንግስት ከቀድሞው የደርግና የሀይለስላሴ ስርአቶች ለመማር ባለመቻሉ፣ ለመውደቅ ተቃርቧል አሉ። “ኢትዮጵያ ፣ ዘ ላስት ቱ ፍሮንቲየርስ” የሚለውን አዲሱን መጽሀፋቸውን ለማስተዋወቅ በለንደን ቻትሀም ሀውስ በተገኙበት ወቅት እንደገለጡት አገዛዙ ስልጣን በበቂና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ወደ ክልሎችና ወደ ...
Read More »በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱት የመለስ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመውን ከልክ ያለፈ ግፍ ለማውገዝ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በላይ ወንድ አፍራሽ ለጀርመን ሬዲዮ ገልጠዋል። መለስ ወያኔ ይውደም፣ የታሰሩት ንጹሀን ዜጎች ይለቀቁ፣ የመሬት ሽንሸናው ይቁም፣ ጀርመን አምባገነኖችን አትርጂ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች በእለቱ ተስተጋብተዋል። ኢትዮጵያኑ ከዚህ ቀደም በኑረምበርግ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ሳምንታትም በዋና ...
Read More »በዴንቨር የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የጠሩት ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ
ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዴንቨር ኮለራዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመንግስት ባለስልጣናት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ለመሸጥና አዲሱን የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማስተዋወቅ የጠሩት ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ በአምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራው የልኡካን ቡድን ያቀደውን ሳይፈጽም፣ በአካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እንዲመለስ መደረጉን በኮለራዶ ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች የላኩት ዜና ያመለክታል። አምባሳደሩ ስበሰባው የህዝብ ስብሰባ እንዳልሆነ በማስታወቅ በስፍራው የነበሩት ተቃዋሚዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ...
Read More »አንድ የፖሊስ ሆስፒታል ምግብ አቅራቢ በ3 የፌደራል ፖሊሶች ተደፈረች
ህዳር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፖሊስ ሆስፒታል ምግብ አብሳይ የሆነችው ማርታ ጉልላት የተባለችው የ23 አመት ወጣት ፣ ህዳር 11 ቀን ሌሊት ላይ በሶስት የፌደራል ፖሊሶች ተደፍራ ህይወቱዋ አስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የደረሰን ዜና አመልክቷል። የማርታ ጉልላት ቤተሰቦች ፖሊሶቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ መንግስትን ቢጠይቁም፣ መንግስት ግን ጉዳዩን ሆን ብሎ እያጉዋተተው ለማወቅ ተችሎአል። የፌደራል ፖሊሶቹ ወጣቷ የተለመደ ምግብ የማቅረብ ስራዋን ስትሰራ በነበረበት ...
Read More »በጎንደር ሆስፒታል በደረሰ የምግብ መመረዝ በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለበሽታ ተዳረጉ
ህዳር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሆስፒታል ምንጮች የደረሰን ዘገባ እንደሚያሳየው የምግብ መመረዙ የተከሰተው ማራኪና ቴዎድሮስ በሚባሉ ሁለት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች ውስጥ ነው። በአንደኛው ግቢ ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች በመጣበባቸው ተማሪዎች በዬመኝታ ክፍላቸው ተኝተው እንዲታከሙ ተደርጓል። መንግስት መረጃው ወደ ውጭ እንዳይወጣ ለሀኪሞቹ ትእዛዝ መሰጠቱንም ለማወቅ ተችሎአል። ከዩኒቨርስቲው አስተዳደር ሰራተኞች እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ችግሩ የተፈጠረው የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ ለተማሪዎች የሚቀርበው ምግብ ጥራት የጎደለው ...
Read More »