Author Archives: Central

የአፍሪቃን መሬት የሚቀራመቱት የእርሻ ልምድና ዕዉቀት የሌላቸው ናቸው ተባለ

ጥር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለአፍሪቃዉያን ጥቅም የሚሰጥ ሳይሆን ይልቁንም ድሃ አነስተኛ ገበሬዎች የምግብ ዋስትና እንዲያጡና ከመኖሪያቸዉ እንዲፈናቀሉ የሚያደርገዉን የመሬት ቅርምትና ድርድር ከጀርባ ሆነዉ የሚያስፈፅሙት የአሜሪካን የልማት ድርጅት( USAID) ፣  የአለም ባንክና ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸዉን የገለፁት አሳሳቢ የፖሊሲ ጉዳዮችን በጥልቀት በማጥናት ለህዝብ በመቆም የሚሟገተዉ የኦክላንድ ኢንስቲትዩት መስራችና ዳይሬክተር አኑራ-ድሃ ሚታል ናቸዉ። ዳይሬክተሯ ይህን የገለፁት ከታዋቂዉ የቺካጎ ህዝብ ሬድዮ  ወርልድ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ወታደሮች ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል ያሏቸዉን በቁጥጥር ስር አዋሉ

ጥር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች  ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል ያሏቸዉን አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋሉ በሶማሊያ ሂራን ክልል በበለደ-ወይን ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች  ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉና በወታደራዊ ካምፖች ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ ነበር ያላቸዉን አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ነዋሪዎች ገለጸዋል። ባለፈዉ እሁድ ጥዋት በከተማዉ ዉስጥ በተወሰደዉ እርምጃ በቁጥጥር ስር የዋሉት አምስት ግለሰቦች በቅርቡ በከተማዉ ዉስጥ ...

Read More »

ኢትዮጵያዊቷ በአቡ ዳቢ ሆስፒታል ለተሰጣት የማዋለድ አገልግሎት ሂሳብ መክፈል ባለመቻሏ ታገተች

ጥር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቤት ሰራተኛነት የስራ ኮንትራት ፈፅማ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ አቡ-ዳቢ ከገባች ከሁለት ቀን በሁዋላ በተሰማት ህመም ወደ ሆስፒታል ስትወሰድ የ9 ወር ነፍሰ ጡር ሆና በመገኘቷ የወሊድ አገልግሎት የተሰጣት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ የሆስፒታሉን እዳ እስካልከፈለች ድረስ እንደማትለቀቅ ገልፍ ኒዉስ የዜና ምንጭ ገለፀ። ስፖንሰር አድራጊዋና አስቀጣሪ ድርጅቷ ስለ እርግዝናዋ ምንም እንደማያዉቁና ተሰማኝ ባለችዉ የሆድ ህመም ምክንያት በስፖንሰርዋ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አሁንም ከአረብ ሳት እንደወረደ ነው

ጥር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ኢሳትን ለማፈን ሙከራ አድርጎ  ከአረብ ሳት እንዲወርድ ካደረገው በሁዋላ በተመሳሳይ እርምጃ የኤርትራን ቴሌቪዥን ለማፈን ባደረገው ሙከራ በአረብ ሳት የሚተላለፈው ዝግጀቱ እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወቃል። አረብ ሳት ለኢትዮጵያ መንግስት ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ቢቆይም፣ በማፈን ተግባሩ የቀጠለው መንግስት በአረብ ሳት የሚተላለፈው ዝግጀቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል። የኤርትራ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈው ስርጭቱ እስከ ዛሬ ሳይታፈን  ቆይቶ አሁን ለመታፈን ...

Read More »

በጋምቤላ ክልል ያለው ውጥረት በሳምንቱ መጨረሻም አይሎ ነበር ተባለ

ጥር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጠው  በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ሢሰሩ  የነበሩት   አቶ ጌታቸው አንኮሬ  ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ  ጋምቤላ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ዙሪያዋን ታጥራለች። ትናንት የፌደራል ሰራዊት አባላት በየአቅጣጫው ውጠራ አድረገው አላፊ አግዳሚውን ሲፈትሹ እንደነበር የገለጠው ዘጋቢያችን፣ በከተማው ነዋሪ ላይም ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት ይታያል። የአካባቢው ባለስልጣናት በከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ ...

Read More »

መንግስት ጥቃት ለማድረስ ሲዘጋጅ የነበረ የአልቃይዳ ህዋስ መያዟን አስታወቀች

ጥር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል እንዳለው ከምሥራቅ አፍሪካ አልቃይዳ ጋር ጥብቅ ግንኙነት በመመስረት በአገር ውስጥ በማደራጀት፣ ሥልጠናና ትምህርት በመስጠት ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአልቃይዳ አባላቱ በአገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመታየት ላይ ያለውን የአክራሪነት ዝንባሌ እንደምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ጉዳት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው ብሎአል ግብረሀይሉ። ተጠርጠሪዎቹ በሶማሊያ ...

Read More »

ኢሳት በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አደረገ

ጥር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢ ኤም ኤፍ ድረገጽ ስራአስኪያጅ የሆነው ዳዊት ከበደ  እንደዘገበው  በአትላንታ በተዘጋጀው ታላቅ ምሽት ላይ ቁጥሩ በብዙ መቶ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ተገኝቶ ነበር። ገና ከጅምሩ በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስት ታማኝ በየነ፣ አርቲስት ሻምበል በላይነህ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ልጅ ተክሌ በክብር እንግድነት ተገኘተዋል። አርቲስት ታማኝ በየነ፣ አርቲስት ሻምበል በላይነህ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ተክለሚካኤል አበበ በእንግድነት ...

Read More »

1486ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል መውሊድ ተከበረ

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዓሉ በታላቁ አንዋር መስጊድ ሲከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬ ዚዳንት ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ ሙስሊሙ በተለያየ መንገድ የሙስሊሙን አንድነት ለማደፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን እንዲከላከል አሳስበዋል፡፡ ከ50 ዓመታት በላይ የቆየውን የአወልያ ተቋም በአዲስ አደረጃጀት በመለወጥ ተቋሙን ወደ ሃይማኖታዊ ዩኒቨርስቲ ለመቀየር እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በርካታየኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአወልያ ኮሌጅ እንዲከፈት፣ የአህባሽ አስተምህሮ እንዲቋረጥና መጅሊሱ በአዲስ ...

Read More »

ጋምቤላ አሁንም በውጥረት ውስጥ ናት

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ክልል በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ሢሰሩ  የነበሩት   አቶ ጌታቸው አንኮሬ  ባልታወቁ ሰዎች በድንገት ተገደሉ። የ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ  እንደገለፀው፤ የደህንነቱ አባል መገደላቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል በክልሉ የነበረው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ የተባባሰ ሲሆን፤የክልሉ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችም ስጋት ላይ ወድቀዋል። የህወሃት አባል በመሆን በክልሉ ለረዥም ዓመታት በምስጢር የደኅንነት ሠራተኛነታቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ...

Read More »

አቶ መለስ በሳልቫኪር አቋም መበሳጨታቸው ተሰማ

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳንን ለመሸምገል ያቀረቡት የሰላም ሀሳብ በደቡብ ሱዳናዊያን ውድቅ በመደረጉ መበሳጨታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚያዉቁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለኢሳት ገልጡ። በቅርቡ ነጻ የወጣችው ደቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ወደ ሰሜኑ የሚሄደውን የነዳጅ ዘይት አቋርጧለች። የደቡብ ሱዳን ውሳኔ በሰሜን ሱዳን ህዝብ ህልውና ላይ የተቃጣ በመሆኑ አገራቸው ደቡብ ሱዳንን ለመውረር እንደምትገደድ ...

Read More »