ቅዳሜ ታህሳስ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና፡- የሳምንታዊው ፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ፣ የጋዜጣው አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮች እና የጋዜጣው ሠራተኞች ከዛሬ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ጠንከር ወዳለ ሁለተኛ ዙር የደህንነት ሠራተኞች ክትትልና ቁጥጥር ሥር መውደቃቸውን የጋዜጣው ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ የሣምንታዊው ፖለቲካዊ ፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ከዕረቡ ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከሰሃት በኋላ ጀምሮ የጋዜጣው ቢሮ እና ቀበና አካባቢ የሚገኘው የዋና አዘጋጁ ...
Read More »Author Archives: Central
መንግስት የሚያሰለጥናቸው የአህባሽ የእስልምና አስተምህሮ ተከታዮች ወደ ሀይል እርምጃ እየገቡ ነው በወረታ አንድ ሰው ገድለዋል
ታህሳስ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመንግስት ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው እና ስልጠና ተሰጥቶአቸው የሚንቀሳቀሱት የአህባሽ የእስልምና አስተምሮ ተከታዮች የሌሎች አስተምህሮ ተከታዮችን ለማጥፋት ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ የእስልምና አስትምህሮ ተከታዮች ለኢሳት ገልጠዋል። በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ መንግስት አሰልጥኖ ያሰማራቸው የአህባሽ ተከታዮች የአልሱና እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸውን በአደባባይ ሲናገሩ መሰማቱን አንዳንድ ሙስሊሞች ለኢሳት ተናግረዋል። የአህባሽ ተከታዮች ጥቅምት 1 ቀን ...
Read More »‹‹አራት ኪሎ የፀደቀ የኢትዮጵያ ሕግ መርካቶን ማስተዳደር አይችልም፤›› ሲሉ የአቶ መለስ ዜናዊ የህግ አማካሪ የነበሩ ሰው ተናገሩ
ታህሳስ 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የህግ ስርአት ምርምር ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መንበረጸሀይ ታደሰ መቀሌ ተደርጎ በነበረው የሰብአዊ መብቶች ቀን በአል ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ “ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ የሚባል ነገር ጠፍቷል፤ ገንዘብ ያለው ሰው እውነት ባይኖረውም፣ እውነት የያዘውን ሰው እያሸነፈው” ሲሉ ገለጡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሳይቀር ያስደነገጠ ንግግር ያቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ...
Read More »ፍርድ ቤት በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በተከሰሱት የመከላከያ ምሥክሮችን ትላንት አደመጠ
ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በተከሰሱት የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚሃብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና ሂሩት ክፍሌ ላይ የመከላከያ ምሥክሮችን ትላንት አደመጠ፡፡ አርቲስት ደበበ እሸቱ የርእዮት ዓለሙ የመጀመሪያ ተከላካይ ምሥክር ሆኖ ርዮትን ከኢትየጵያን ሪቪዩ ...
Read More »የፍትህ ጋዜጣ ቢሮ እና የዋና አዘጋጁ ቤት አሁንም በደህንነት ሀይሎች እንደተከበበ ነው
ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደህንነት ሀይሎች ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 5 ሰአት ጀምሮ የፍትህን ቢሮ እና የዋና አዘጋጁን የተመስገን ደሳለኝን መኖሪያ ቤት መክበባቸው ታውቋል የአዘጋጁን የሀይለመስቀል ባሸዋምየለህን ስልክ ሲም ካርድ አውጥተው በመውሰድና ማንነቱን የሚያንቋሽሽ ስድብ ከመስደብ ውጭ ፣ የደህንነት ሰራተኞቹ ጋዜጠኞችን ለማሰርም ሆነ ለመደብደብ ሙከራ አላደረጉም። ይሁን እንጅ ጋዜጠኞቹ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና የደረሰባቸው በመሆኑ ስራቸውን ተረጋግተው ለመስራት አልቻሉም። ...
Read More »የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት በመሆን በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን የሚመሩ የካቢኔ አባላት እንደሚያቀርቡ አስታወቁ
ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ፕሬዝዳንት በመሆን በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን የሚመሩ አስር አባላት ያሉትን የካቢኔ አባላት ቅዳሜ እንደሚያቀርቡ አስታወቁ። ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፤አዲሱ ፕሬዚዳንት ነገ ታህሳስ 14 ቀን በሚካሄደው የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፓርቲውን የሚመሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት (ካቢኔ) መርጠው በመለየት ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ያቀርባሉ። ከዚህ ጎን ...
Read More »በጋሞጎፋ ዞን በጨንቻ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች መሬታቸው ያለ አግባብ በመነጠቁ ከመንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ
ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንቻ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች መሬታቸው ያለ አግባብ በመነጠቁ ሳቢያ ከመንግስት ሹመኞችና ፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ። አርሶ አደሮቹ ወደ ግጭት ለመግባት የተገደዱት፤”የጨንቻ ከተማን ለማስፋት” በሚል ሰበብ እየተካሄደ ባለው የከተማ ማካለል ስራ፤ ከይዞታቸው አላግባብ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ በመገንዘባቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ሰንደቅ እንደዘገበው፤በከተማዋ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶአደሮች የከተማዋን መስፋፋት ...
Read More »ለርዮት አለሙ መከላከያ ምስክር ሆኖ በመቅረብ የመሰከረላት ሀይለ መስቅል በሸዋምየለህ ላይ የደህንነት ሰራተኛ ነን ያሉ 3 ግለሰቦች ከባድ ማስፈራራያ አደረሱበት
ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትላንትናው እለት በ11/04/04ዓ.ም ለፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ መከላከያ ምስክር ሆኖ በመቅረብ የመሰከረላት የፍትህ አዘጋጅ ሀይለመስቅል በሸዋምየለህ ከምሽቱ 12፡30 ላይ ቢሮ በር ላይ የደህንነት ሰራተኛ ነን ያሉ 3 ግለሰቦች ሲም ካርዱን ከነጠቁ በኋላ ከባድ ማስፈራራያ እንዳደረሱበት ታወቀ በዚሁ እለት ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ የፍትህ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እና ሀይለመስቀል በሸዋምየለህ ከቢሮ ወጥተው ሲሄዱ ...
Read More »የኢሚግሬሽንና ደህንነት መስሪያቤት ሰራተኞች ፓስፖርት እና ቪዛ ጠያቂዎችን ለማስተናገድ በማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ ነው
ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው ኢትዮጵያውያኑ ፓስፖርት ለማግኘት ሲሉ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ በኢሚግሬሽን ፊት ለፊት ሰልፍ ይይዛሉ። አብዛኞቹ ፓስፖርት ጠያቂዎች ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት ለስራ ፍለጋ የሚሄዱ ናቸው። በቪዲዮ ምስል አስደግፎ በላከው መረጃ እንደገለጠው በእየለቱ የሚታየው ረጅም ሰልፍ በተሽከርካሪ ፍሰት ላይም ችግር እየፈጠረ ነው። በሱዳን ኢምባሲ አካባቢ የሚታዩት ረጃጅም ሰልፎች የአገሪቱ ህዝብ ...
Read More »የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ የኢትዮጵያ ጦር በአሁኑ ጊዜ ሶማሊያ ውስጥ አልገባም አሉ
ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ውስጥ ወታደር ለመቅጠር ተቸግረን ነበር ሲሉም ተናግረዋል። መከላከያ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከትናንት በስቲያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ውስጥ ለተሰበሰቡት የኢህአዴግ አባላት የመስሪያ ቤታቸውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት -ከብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ከአቶ ግርማ ሰይፉ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው። ከሳምንታት በፊት በ አዲስ አበባ በተካሄደውና በአቶ መለስ ዜናዊ በተመራው የኢጋድ አባል አገራት ስብሰባ ...
Read More »