Author Archives: Central

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በተከሰሱ ዜጎች ላይ 35 ሰዎችን የዐቃቤ- ሕግ ምስክር አድርጎ ማቅረብ ጀመረ

 ታህሳስ 07 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግሥት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ (112546) በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ 35 ሰዎችን የዐቃቤ- ሕግ ምሥክር አድርጎ ማቅረብ ጀመረ። መንግሥት የምስክሮቹን የቀን ውሎ አበል፣ የቁርስ፣ ምሳ ፣ እራት የምግብ ፍጆታ በመሸፈን ሌሎች ጥቅማ- ጥቅሞችን እንደሚያስብ የፍርድ ቤት ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ...

Read More »

በስልጢ ዞን አስተዳዳሪዎች አመራር ሰጪነት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ሙስሊሞች በስልጢ ዞን- በኮቶ ባሰሎ የምትገኝን አንዲት ቤተ-ክርስቲያን በእሳት አቃጠሉ

ታህሳስ 07 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ክርስቲያኖች እያለቀሱ ሲናገሩ እንደተደመጡት፤ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ጣራ  ቀደም ሲል ያፈረሱት  የመንግስት ፖሊሶች ነበሩ። ሰሞኑን ደግሞ በመስተዳድሩ እና በፖሊሶች አስተባባሪነት በቀጠለ ሁለተኛ ዙር የጥቃት ዘመቻ ቤተ-ክርስቲያኒቱ ሙሉ በሙሉ  በእሳት ተቃጥላለች። ክርስቲያንና ሙስሊም ለዘመናት ተከባብረው የሚኖሩባት ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ  ተደጋጋሚ ሀይማኖታዊ ግጭቶችን ስታስተናግድ መስተዋሏ ብዙዎችን ማነጋገር ከጀመረ ውሎ አድሯል። ግጭቱ፤በህዝብ እየተጠላ የመጣው ገዥው ...

Read More »

በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኔሰው ገብሬን ለመዘከር የሻማ ማብራት ስነስርአት ያደርጋሉ

ታህሳስ 07 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያኑ እሁድ ዲሰምበር 18 በአምስተርዳም ከተማ በሚያካሂዱት የሻማ ማብራት ስነስርአት ፣ የኔሰው ገብሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ የከፈለውን መስዋትነት በመዘከር፣ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ ላይ ስለሚኖረው ሀላፊነት ምክክር እንደሚደረግ የአምስተርዳም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ወንድወሰን ገብረህይወት ለኢሳት ገልጠዋል። በአሪቢሞንድ ስትራት ከሰአት በሁዋላ 5 ፒኤም በሚደረገው ስነስርአት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙሀን ወኪሎችና የሲቪክ ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ውስጥ በጸረ ሽብርተኝነት ሰበብ የሚካሄደው እስር የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን ተብሎ የተደረገ ነው አለ

ታህሳስ 06 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ 108 የተቃዋሚ አባላትና 8 ጋዜጠኞች ታስረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት፣  ተቃዋሚዎችንና ተችዎችን በጸረ ሽብር ትግል ስም ዘብጥያ እያወረደ ነው ሲል የሰብአዊ መብት ተቋሙ በሪፖርቱ አመልክቷል። አብዛኞቹ  አሸባሪ ተብለው የታሰሩት በሙሉ መንግስትን በመተቸት የሚታወቁ ናቸው የሚለው አምነስቲ፣ የታሰሩበት ምክንያትም መንግስት የፖለቲካ ለውጥ እንዲያካሂድ ያሳሰቡ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲፈቀድላቸው ...

Read More »

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ ላይ የቀረቡት የህግ ምስክሮች በናዝሬት ለሌላ ‘አካልዳማ’ የችሎት ተዉኔት የቃል አሰጣጥ ስልጠና መዉሰዳቸዉ ታወቀ

ታህሳስ 06 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከመንግሥት ጋር በመደራደር እና በግዴታ “አኪልዳማ‘ በተሰኘው የኢቲቪ የፕሮፓጋንዳ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን፣ ሌሎች ሰዎችን እና ፓርቲዎችን በመውቀስ ለመንግሥት የድጋፍ ቃላቸውን የሰጡ  ሰዎች ይገኙበታል የተባሉት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የሚጠሩት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እነማን እንደሆኑ በዝርዝር አልታወቁም። ለምስክሮች ደኅንነት ሲባል ስማቸዉ እንዳይገለፅ የተደረገው ቁጥራቸዉ ከ30 በላይ የሆኑት የአቃቤ ህግ ምስክሮች በናዝሬት ከተማ አንድ ...

Read More »

በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ይሰጣል የተባለው ብይን የኢትዮጵያና የስዊድን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ያበላሸዋል ተባለ

ታህሳስ 05 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ  በሚቀጥለው ሳምንት  ረቡዕ ይሰጣል የተባለው ብይን ለወትሮው በቋፍ ላይ የሚገኘውን  የኢትዮጵያና የስዊድን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መውጫ ይበልጥ ያበላሸዋል የሚል ስጋት እንዳላቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ገለጹ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ለኢሳት ዘጋቢ እንዳሉት፤ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሁለቱ አገሮች መካከል እየተፈጠረ ያለው መቃቃር በጋዜጠኞቹ ላይ በሚሰጠው ብይንም ሆነ የመጨረሻ ...

Read More »

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፤ ከፓርቲ አመራርነት እራሳቸውን አገለሉ

 ታህሳስ 05 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢንጂነር ግዛቸው ይህን ያስታወቁት፤ ባለፈው እሁድ በዲ.አፍሪክ ሆቴል ብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ እና አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ  ፓርቲዎች በይፋ ውህደት በፈፀሙበት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው። ኢንጂነር ግዛቸው በዕለቱ ለውህዱ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም፦ ‘‘እኔ የፖለቲካ ኃይሌ ከውስጤ ተሟጥጦ ስላለቀ፤ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልም ሆነ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆኜ መቀጠል አልችልም’’ ማለታቸው ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ የአፍሪካን የአካባቢ ጉባኤ ለመምራት የሞራል ብቃት የላቸውም ሲሉ አንድ ደቡብ አፍሪካዊት ጸሀፊ ገለጡ

 ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጃኒስ ዊንተር የተባሉት ጸሀፊ ደይሊ መቨሪክ በሚባለው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ባወጡት ጽሁፍ ፣ በደርባን የተካሄደው ኮፕ 17 የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ፣ ድንቅ የተባለ  ስምምነት አድርጓል። የስምምነቱ ዋና ድል ተ ብሎ የተቆጠረው ደግሞ፣ የአካባቢ ጥበቃ ለማካሄድ የተፈቀደው ገንዘብ ነው። መለስ ዜናዊ በጉባኤው ላይ ለአካባቢ ጥበቃ ተብሎ የተመደበው ገንዘብ አዲስ ገንዘብ አለመሆኑን ይልቁንም ከዚህ ቀደም ለእርዳታ ተብሎ ...

Read More »

ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ እነ አንዷለም አራጌ ከቀጠሯቸው በፊት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዘ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ከተመሰረተባቸው 24 ተከሳሾች መካከል አቶ አንዷለም አራጌን ጨምሮ 8 ተከሳሾች ለታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም፤ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለታህሳስ 5 ቀን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3 ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንደደረሳቸው የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮ የተከሳሾቹን የ እምነት ክህደት ቃል ከሰማ በሁዋላ ...

Read More »

የመለስ መንግስት ልዩ ሀይል በአኝዋክ ህዝብ ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ 8 ኛ አመት ታስቦ ዋለ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አኝዋክ ጀስቲስ ካውንስልና ጥምረት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በጋራ ባወጡት መግለጫ የመለስ መንግሰት ልዩ ሀይል ከዲሰምበር 13እስከ 15 ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ 424 አኝዋኮችን ገድሏል። ከዚያ በሁዋላ በነበሩት ተከታታይ አመታት በድምሩ 1500 አኝዋኮች መገደላቸውን መግለጫው አመልክቷል። ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው የመለስ መንግስት በጊዜው በአኝዋኮች ላይ የወሰደው እርምጃ ምንክንያቱ የአካባቢውን መሬት፣ ውሀ፣ የተፈጥሮ ጋዝና ማእድናት ለመቆጣጠር ነው። ...

Read More »