ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ በምስል በማስደገፍ በላኩት መረጃ፣ ወረቀቶችን የበተኑት በመርካቶ ፣ በስድስት ኪሎ፣ ጊዮርጊስ ፣ ሳሪስና ፒያሳ አካባቢዎች መሆኑ ታውቋል። ፖሊስ ወረቀቶች ከተበተኑ እና ከተለጠፉ በሁዋላ የወረቆቶችን ደብዛ ለማጥፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር የድርጀቱ አባላት ገልጠዋል። በቅርቡ በታላቁ ርጫ ላይ መንግስትን የሚቃወሙ ወረቀቶችን የበተኑ ወጣቶች መታሰራቸው ይታወሳል።
Read More »Author Archives: Central
ሰማያዊ ፓርቲ፤ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂድበትን አዳራሽ በማጣቱ በጽ/ቤቱ ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከስድስት ወራት በፊት የአንድ ሺህ አምስት መቶ መስራች አባላትን የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂድበትን አዳራሽ በማጣቱ ጠቅላላ ጉባኤውን በጽ/ቤቱ ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ። ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ፤ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂድበትን አዳራሽ በማጣቱ በጽ/ቤቱ ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ ከፓርቲው አደራጆች አንዱ የሆኑት የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት አባል ...
Read More »ኤርትራ፤”ገለልተኛ አይደለም”ያለችው የተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ጉዳይ አጣሪ ቡድን እንዲቀየር ጥያቄ አቀረበች
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስብሰባ ላይ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ ሴራ ጠንስሳ ነበር” በሚል የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አጣሪ ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት እንደማትቀበለው በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል። “ኤርትራ ፤የአጣሪ ቡድኑን ሪፖርት ያልተቀበለችው፤ ፍትሃዊነት የሚጐድለውና በአድሎም የተሞላ ስለሆነ ነው” በማለት የየኤርትራ መንግስት በአጣሪ ቡድኑ ላይ ተቃውሞውን መግለጹም አይዘነጋም። በአዲስ መልክ የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ...
Read More »በእነ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በተከሰሱት ላይ የሚያቀርበውን ማስረጃ ማጠናቀቁን አቃቢ ህግ አስታወቀ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ “አኬልዳማን” በተመለከተ እስረኞች ያቀረቡትን አቤቱታም ሳይቀበለው ቀርቷል። አቃቢ ህግ ፣ የብሄራዊ የጸጥታና የደህንነት ቢሮ ህጋዊ በሆነ መንገድ የጠለፋቸው መረጃዎች ናቸው ያላቸውን 2 የኦዲዮ ማስረጃዎች በእስክንድር ነጋ ላይ አቅርቧል። የኦዲዮ ማስረጃዎቹ እስክንድር ነጋ ከ16ኛ ተከሳሽ ከሆነው አበበ በለው ጋር ሲነጋጋር እንደነበር ያረጋገጣል ብሎአል። አበበ በለው የግንቦት 7 ቃል አቀባይና የኢሳት የቦርድ አባል ነው ...
Read More »በአዲስ አበባ የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቤቶች እየተስፋፉ ነው ተባለ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው በአዲስ አበባ ከተማ አንድ እና ሁለት የነበሩት የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቦታዎች በተለያዩ ክፍለ ከተሞችም እየተስፋፉ ነው። በመርካቶ ብቻ ሶስት የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቦታዎች መኖራቸውን የዘገበው ፎርቹን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፒያሳ፣ ስድስት ኪሎና ሌሎች ቦታዎችም የጉርጫ ምግብ መሸጫ ቦታዎች መቋቋማቸውን ዘግቧል። ጉርሻ የሚባለው ከሆቴሎች የተረፈ ምግብ ወይም በተለምዶ “ቡሌ” ለአንድ ሰው ...
Read More »የአህባሽን እምነት ለመከተል ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ 10 የእስልምና እምነት ተከታዮች ታሰሩ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር በአድርቃይ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሙስሊሞች የታሰሩት ፣ የአህባሽን አስተምህሮ የሚያስፋፉት የሙስሊም አባላት ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሎ ነው። ያለምንም ጠያቂና የፍርድ ቤት ሂደት ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ሙስሊሞቹ እየተሰቃዩ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። እስረኞቹ “የድረሱልን ጥሪ” ማሰማታቸውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሙስሊሞቹ የአካባቢው ተወካይ ለኢሳት ተናግረዋል። “ፍርድ አጣን፣ በአገራችን መኖር ...
Read More »27 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራርና አባላት ታሰሩ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ልዩ ዞን በዘንጋ አዋንዴ ቀበሌ ውስጥ 27 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራርና አባላት በገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች መታሰራቸውን መኢአድ አስታወቀ፡፡ የደምባ ጎፋ ወረዳ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ማዩ ማይጠሎ በበኩላቸው፣ የተጠቀሱት የመኢአድ አባላት የታሰሩት በአካባቢው እየተከናወነ ያለውን የልማት ሥራ ለማደናቀፍ በመንቀሳቀሳቸው ነው ይላሉ። መኢአድ እንዳስታወቀው፣ ታኅሣሥ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከታሰሩት ...
Read More »የአቶ መለስ መንግስት የደህንነት ሀይሎች በኡጋንዳ የሚገኙ አምስት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንና ጋዜጠኞችን አፍነው ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተጋለጠ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በካምፓላ- በደህንነቶች የመታፈን አደጋ ተጋርጦባቸው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከሚገኙት አምስት ሰዎች መካከል፤ በቅርቡ የፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት የመኢዴፓ ሊቀመንበሩ አቶ ዘለለ ፀጋሥላሴ እና ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻው ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። በቅርቡ እዚያው ካምፓላ ውስጥ የነበረ ሩዋንዳዊ የፖለቲካ ስደተኛ በታጠቁ ሀይሎች መገደሉን ያስታወሰው የኢሳት ዘጋቢ፤ በኡጋንዳ የሚገኘው የተባበሩት ...
Read More »በዳርፉር አመጽያን መሪ ግድያ ዙሪያ የኢትዮጵያ እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር መረጃዎች አመለከቱ
ታህሳስ 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንደሚያመለክተው የዳርፉር አማጺ መሪ የነበሩት ዶ/ር ካሊል ኢብራሂም ከመገደላቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ አቶ በረከት ስምኦን ከሱዳን ከፍተኛ የደህንነት ሰዎች ጋር በካርቱም ውይይት አድርገዋል። አቶ በረከት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከ ኢትዮጵያ 10 የደህንነት አባላት ጋር ዲሰምበር 23 ቀን 11፡30 ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው ዲሰምበር 24 ቀን ከቀኑ ...
Read More »87 የአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሬት በሊዝ ድርድር እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ የአዲስ አበባ መስተዳድር ውድቅ አደረገው ፤ለቻይና ኩባንያ እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ 160 ሄክታር መሬት ተሰጠ
ታህሳስ 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-87 የአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሬት በሊዝ ድርድር እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ውድቅ ያደረገው የ አዲስ አበባ መስተዳድር፤”ሁጃን ግሩፕ” ለተባለው ግዙፍ የቻይና ኩባንያ እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ አርሶ አደሮችን በማፈናቀል 160 ሄክታር መሬት ሰጠ። የአዲስ አበባ መስተዳድር የሊዝ ቦርድ የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገበትን ምክንያት ግልጽ ባያደርግም፣ የከተማው ማኅበራዊና ሊዝ ...
Read More »