የኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት አባላት በአዲስ አበባ በራሪ ወረቀቶችን መበተናቸውን አስታወቁ

20 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ በምስል በማስደገፍ በላኩት መረጃ፣ ወረቀቶችን የበተኑት በመርካቶ ፣ በስድስት ኪሎ፣ ጊዮርጊስ ፣ ሳሪስና ፒያሳ አካባቢዎች መሆኑ ታውቋል።

ፖሊስ ወረቀቶች ከተበተኑ እና ከተለጠፉ በሁዋላ የወረቆቶችን ደብዛ ለማጥፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር የድርጀቱ አባላት ገልጠዋል።

በቅርቡ በታላቁ ርጫ ላይ መንግስትን የሚቃወሙ ወረቀቶችን የበተኑ ወጣቶች መታሰራቸው ይታወሳል።