Author Archives: Central

የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 2 ነጥብ 8 ሚሊየን መደረሱ ተገለጸ። ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው በአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊየን መጨመሩንም የመንግስታቱ ድርጅት የህጻናት መርጃ ተቋም ዩኒሴፍ አስታውቋል። መፈናቀሉ የተከሰተው በአብዛኛው በኦሮሚያ፣ ሶማሌና ደቡብ ክልሎች መሆኑንም ዩኒሴፍ ባወጣው መረጃ ተገልጿል። ከክረምቱ መጠናከር ጋር ተያይዞ በሚከሰት የጎርፍ አደጋ ተጨማሪ ተፈናቃዮች እንደሚኖሩ በመግለጽ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል ብሏል ዩኒሴፍ። የመንግስታቱ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መሬቶች በአቶ አባይ ጸሀዬ ፊርማ የተፈጸሙ ናቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) ለሱዳን ተላልፈው የተሰጡ የኢትዮጵያ መሬቶች በአቶ አባይ ጸሀዬ ፊርማ የተፈጸሙ መሆናቸው ተጋለጠ። ይህንን የሚያሳየውና የአቶ አባይ ጸሀዬ ስምምነት የተገለጸበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል። ስምምነቱን የተፈራረሙት አቶ ደመቀ መኮንን እንደሆኑ ተደርጎ ለዓመታት ሲገለጽ የነበረው ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነም የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ አስታውቋል። አቶ አባይ ጸሃዬ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ የተፈራረሙት ሰነድ ላይ መሬቶቹ በአስቸኳይ ለሱዳን ተላልፈው ...

Read More »

ለሃይማኖታዊ የሃጂ ፀሎት የሚጓዙ ምእመናን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ መንገላታት ደረሰባቸው።

ለሃይማኖታዊ የሃጂ ፀሎት የሚጓዙ ምእመናን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ መንገላታት ደረሰባቸው። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በማድረግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገቢውን የበረራ መስፈርቶችን አሟልተው ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመብረር ሲጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸው በረራቸው እንዲሰረዝ በመደረጉ ለከፍተኛ እንግልትና ለተጨማሪ ወጪዎች ተጋላጭ ሆነዋል። አብዛሃኞቹ እድሜያቸው የገፋ አቅመ ደካማ አዛውንቶች፣ ...

Read More »

የዓባይ ግድብን እየሠራ የነበረው ሳሊኒ የኮንስትራክሽን ኩባንያ መንግስትን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መጠየቁ ተሰማ።

የዓባይ ግድብን እየሠራ የነበረው ሳሊኒ የኮንስትራክሽን ኩባንያ መንግስትን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መጠየቁ ተሰማ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) የዓባይ ግድብን የሜካኒካል ስራ ኃላፊነት የወሰደው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን በምህጻረ ቃሉ ሜቴክ፣ በኮንትራት የወሰደውን ሥራ በተቀመጠለት ጊዜ እና በትክክል ሰርቶ ማስረከብ ባለመቻሉ የጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ሌሎች ስራዎችን መቀጠል አልቻለም ሲሉ ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት ውሉ ያልተጠበቀለት ...

Read More »

በጅግጅጋ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ባንዲራና መገንጠልን የሚቀሰቅሱ ባነሮች በብዛት እየታተሙ መሆናቸው ተገለጸ። ኮማንድ ፖስቱ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

በጅግጅጋ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ባንዲራና መገንጠልን የሚቀሰቅሱ ባነሮች በብዛት እየታተሙ መሆናቸው ተገለጸ። ኮማንድ ፖስቱ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) በስፍራው ያሉ የኢሳት ወኪሎች ባደረሱን መረጃ መሰረት፣ ቀደም ሲል አብዲ ኢሌ ያደራጃቸው ሄጎ የእተባሉ የሚጠሩት ቡድኖች፤ ትናንትና በጅግጅጋ ከተማ የመንግስት መኪኖችን ጭምር በመጠቀም እና የኦብነግን ባንዲራ በማውለብለብ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረዋል። እነዚሁ ቡድኖች ክልሉን ለማረጋጋት ከተሰማራው የመከላከያ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን አዲስ የዋጋ ታሪፍ ጭማሪ ማስተካከያ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን አዲስ የዋጋ ታሪፍ ጭማሪ ማስተካከያ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ተጨማሪ የዋጋ ታሪፍ ሊጥል ነው። ከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ ተጠቃሚዎች በአዲሱ ተመን እስከ 350 በመቶ ጭማሪ ክፍያ ይጠየቃሉ። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት (EEU)፣ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ፓወር (EEP)፤ ከውሃ፣ መስኖ እና ኤሌትሪክ ...

Read More »

አቶ ተስፋዬ ኡርጌ እየተካሄዱ ካሉ ግጭቶች ጋር በተያያዘ ምርመራ ተጀመረባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ባለስልጣን የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ካሉ ግጭቶች ጋር በተያያዘም ምርመራ እንደተጀመረባቸው ተገለጸ። አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት በማስተባበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል። ግለሰቡ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የግዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ወህኒ ቤት ተመልሰዋል። ተጠርጣሪው አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በውጭ ሃገር ካሉ ቡድኖች ጋር አላቸው በሚል የተጀመረባቸው ምርመራም መቀጠሉ ...

Read More »

ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳና ሌሎች የፖሊስ አመራሮች ዋስትና ተፈቀደ

 (ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)በመስቀል አደባባይ ሰኔ 16 በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው ታስረው የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮችም ዋስትና ተፈቀደላቸው። አቃቤ ህግ የፖሊስ አመራሮቹ  በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ለፍርድቤቱ ገልጾ ነበር። የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል። ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ...

Read More »

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)የመብት ተሟጋቹ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ጥሪ ቀረበ ። ለዚህ ታዋቂ አትሌት የጀግና አቀባበል ለማድረግ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝግጅት ማድረጋቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል። በነሃሴ 2008 ዓም በብራዚል ሪዮ ዲጄነሮ በተካሄደው ኦሎምፒክ በማራቶን ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው  አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ  ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል። በዚሁ ወቅትም ሩጫውን ሲያጠናቅቅ በኢትዮጲያ የሚካሄዱ ግድያዎችን በአጠቃላይ የመብት ...

Read More »

ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከስደት ተመለሱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)  የአፋር መንፈሳዊ መሪ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከስደት ተመለሱ።በከሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ጋር የአፋር ሕዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር  ኮንቴ ሙሳ እንዲሁም የአፋር ሰብዓዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድም  በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በተመሳሳይ ዜና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮችም ዛሬ  ወደ  ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። ከአምስት አመታት በፊት የሱልጣን አሊ ሚራህን ማለፍ ተከትሎ፣ የሱልጣን ማዕረጉን የወረሱትና ባዕለ-ሲመታቸውን በአፋር ክልል በአሳይታ   ከተማ  ያካሄዱት ...

Read More »