የዋጋ ንረቱ መንስኤ አርሶ አደሩ በአፍር ጥበቃ ላይ በመሰማራቱ ነው ተባለ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጤፍ የችርቻሮ ዋጋ የጨመረባቸው ዋነኛ ምክንያቶች በኮንትሮባንድ ከሀገር እየወጣ በመሆኑና አርሶ አደሩም በአብዛኛው በአፈር ጥበቃ ሥራ ከመሰማራቱ ጋር በተያያዘ ምርቱን ወደ ገበያ ይዞ በመውጣቱ መሆኑን የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓሊ ሲራጅ መግለጣቸውን ሰንደቅ ዘግቧል። አቶ ዓሊ የጤፍ ምርት ዋጋ እንዲቀንስ መንግስት በአካባቢና አፈር ጥበቃ ላይ የተሰማራው ገበሬ ምርቱን ወደ ገበያ ይዞ እንዲወጣ ...

Read More »

በወጣቶች እንቅስቃሴና በሰብኣዊ መብት ረገጣ የአንድ ወር ሪፖርት ቀረበ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እኤአ ከየካቲት 9 እስከ መጋቢት 9/2012 በክልሉ ዉስጥ ስለነበረዉ የወጣቶች እንቅስቃሴና በመንግስት በኩል ስለተወሰደዉ የመብት ረገጣ የሚገልፀዉን የአንድ ወር ዝርዝር ሪፖርት ያወጣዉ የኦሮሚያ ወጣቶች ንቅናቄ  የተባለዉ ድርጅት ነዉ። በመንግሰት ጥቃት የተፈፀመባቸዉን የኦሮሞ ተወላጆች በሙሉ በስም በመጥቀስ ድርጅቱ ባወጣዉ ሪፖርት፤ በኦሮሚያ  ምእራብ ሸዋ ዞን በአዳ-በርጋ ወረዳ አነስተኛ ገበሬዎችን ከመሬታቸዉ በማፈናቀል ከኢትዮጵያ መንግሰት ጋር ...

Read More »

አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኰሰ ጥይት ቆስሎ ወደ ሕክምና ተወሰደ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዝቋላ ገዳም ቃጠሎውን ለማጥፋት በተሰበሰቡ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መካከል በተቀሰቀሰው አለመግባባት አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኰሰ ጥይት እግሩ ላይ ቆስሎ ወደ ሕክምና መወሰዱን ደጀሰላም ዘገበ ወጣቶቹ ቃጠሎውን አስመልክቶ በቀጥታ ስርጭት ዘገባ ማስተላለፍ ሥራ ላይ የነበረውን ጋዜጠኛ በመቃወማቸው ጸቡ ተፈጥሯል። የዐይን እማኞችን ጠቅሶ ድረገጹ እንደዘገበው  ጋዜጠኛው እሳቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የሚገልጽ ዘገባ ...

Read More »

የዝቋላ ገዳም ደን በእሳት እየተቃጠለ ነው

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አካባቢ የሚገኘው ደን በመንደድ ላይ መሆኑን የገዳሙ አባቶች ተናገሩ። ባለፈው አርብ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተነሳው ቃጠሎ  የዝቋላ አቦ ቤተክርስቲያንን ሊያቃጥላት ይችላል ተብሎ የተፈራ ቢሆንም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ደረስ የእሳቱ መጠን የቤተክርስቲያኑንና የገዳሙን ህልውና ወደ ማይፈታተንበት ደረጃ ቀንሶአል። በካባቢው በእሳት ማጥፋት ላይ ...

Read More »

በጋምቤላ የጸጥታ ማስጠበቁ ስራ ለፌደራል ፖሊስ ተሰጠ ምክር ቤቱም ተከፍሎአል

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ የጸጥታ ማስጠበቁ ስራ ከክልሉ መንግስት ተወስዶ ለመከላከያ እና ለፌደራል  ፖሊስ ተሰጠ  ምክር ቤቱም ተከፍሎአል በጋምቤላ የሚታየው የጸጥታ መደፍረስ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቦ ቆይቷል። የኢሳት ዘጋቢዎች  በክልሉ ያለውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ሲዘግቡና ለህዝብ ይፋ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በኢትዮጵያ የምእራብ ጠረፍ የምትገኘዋ ጋምቤላ በስልጣን ላይ ያለው የህወሀት መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሰላምና መረጋጋት ርቋት ...

Read More »

ህወሀት የመለስና የሚስቱ ፓርቲ እየሆነ ነው ተባለ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት የአመራር አባል ይህን የተናገሩት አትላንታ ተዘጋጅቶ በነበረው ዝግጅት ላይ ነው። አቶ ስየ ከተሰብሳቢው ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜ ”  በአጠቃላይ ህወሃት የመስራች ወይም የአባላቱ ፓርቲ አይደለም። እባካችሁ የትግራይም ነው አትበሉ። የቤተሰብ ፓርቲ  እየሆነ ነው። ከዚያም እየቀጠነ የመለስ እና የሚስቱ የአዜብ ፓርቲ እየሆነ ነው ያለው።” በማለት ተናግረዋል። ኦህዴድ ወይም ብአዴን የሚለው ነገር ምርጫ ለመስረቅ ካልሆነ ...

Read More »

የሙስሊሙን ሠላማዊ ትግል ሊያጨናግፍ የሚችል አቻ ኮሚቴዎች ተዋቀሩ

  መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ሕዝበ ሙስሊሙ እያካሄደ ያለውን ሠላማዊ ትግል ሊያጨናግፍ የሚችል አቻ ኮሚቴዎችን አዋቅሮ የግብረ ኃይል የሥራ ተዋረድ እንደሰጣቸውና የመንግሥት ተወካዮች በእጅ አዙር ድጋፋቸውን እንደገለጹለት የመጅሊስ ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ.ም ጦር ኃይሎች አካባቢ ከሆላንድ ኤንባሲ አቅራቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ቅጥር ጊቢ ከሁለት ሺህ ...

Read More »

ዕውቁ ፎቶግራፍ አንሽ የሊባኖስ መንግስት ያበረከተላቸውን የክብር ኒሻን መልሶ እንዲረከባቸው ጠየቁ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዕውቁ ፎቶግራፍ አንሽ አቶ ሽመልስ ደስታ፤ የሊባኖስ መንግስት 50 ዓመታት በፊት ያበረከተላቸውን የክብር ኒሻን መልሶ እንዲረከባቸው ጠየቁ። አቶ ሽመልስ ደስታ በዓፄ ሀይለሥላሴ ጊዜ ከሊባኖስ ያገኙትን የክብር ሽልማታቸውን ለመመለስ የወሰኑት፤ ሊባኖስ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እየተፈፀመ  ያለውን ግፍና በደል በመቃወም ነው። አቶ ሽመልስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1966 ዓመተ- ምህረት ከቀዳማዊ ሀይለሥላሴ ጋር ወደ ቤሩት ...

Read More »

ኖርዌይ 450 ህጻናትን ልታስወጣ ተዘጋጅታለች ተባለ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘ ፎሬነር እንደዘገበው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔውን በተመለከተ ለፓርላማ አባላት ንግግር አድርገዋል። እንደርሳቸው አባባል ውሳኔው ስደተኝነትን የሚገታ እርምጃ ነው። እርሳቸው ይህን ቢሉም የአገሪቱ ፖለቲከኞችና ጸሀፊዎች ውሳኔውን እያወገዙ ነው። ፖለቲከኞች ውሳኔው ህጻናትን እንዳይጨምር እየጠየቁ ነው። ለመለስ መንግስት የሚሰጠውን እርዳታ የጨመረው የጠ/ሚኒሰትር ጂንስ ስቶልተርበርግ መንግስት ፣ በአለማቀፍ ደረጃ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለሚታወቅ መንግስት እርዳታ መጨመሩ ...

Read More »

ሰበር ዜና :- የጋምቤላ መንግስት የምክር ቤት አባላት ለሁለት ተከፈሉ

መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጋምቤላ መንግስት የምክር ቤት አባላት ለሁለት ተከፈሉ ፤ አንደኛው ወገን ህገ መንግስቱንና የፌደራሉን መንግስት አንቀበልም እንደ ጁባ ራሳችንን እናስተዳድር የሚል አቋም ይዟል የክልሉ  መንግስት ጸጥታ የማስጠበቁን ስራ ለመከላከያ አስረክቧል በቅርቡ በተገደሉት 19ኙ ሰዎች ላይ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት ተረጋግጧል ፕሬዚዳንቱ ካልወረደ  ግድያው  እንደሚቀጥል የምክር ቤቱ አባላት አስጠንቅቀዋል

Read More »