መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሰሞኑን ዓመታዊው የኢሬቻ በዓል በደብረ ዘይት በሚከበርበት ጊዜ በደህንነት ሀይሎች የታሰሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ደህንነት ጉዳይ እጅግ እንዳሣሰበው የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገልጿል። የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከወኪሎቹ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ባለፈው መስከረም 29 የኢሬቻ በዓል ማጠናቀቂያ ላይ በደህንነቶች ተወስደው የታሰሩት ከ200 በላይ ሲሆኑ፤ሁሉም ወጣቶች ናቸው። ወጣቶቹ በማግስቱ ...
Read More »በአዲስ አበባ የቪኦኤ ወኪል ጋዜጠኛ ማርቲ ቫን ደር ወልፍ መታሰሯን ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ኮሚቴ-ሲፒጄ አወገዘ
መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ሲፒጄ መግለጫ፤ ጋዜጠኛ ማርቲ የታሠረችው፤ የትናንት አርቡን የሙስሊሞች ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ በመገኘት የዘገባ ሽፋን እየሰጠች ባለችበት ጊዜ ነው። ሰልፈኞቹ፤’በመጪው እሁድ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫን ለማካሄድ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል’ በማለት ተቃውሟቸውን ለማሰማት የወጡ መሆናቸውን ፤ሲፒጄ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞችን በመጥቀስ በመግለጫው ጠቁሟል። በስፍራው ዘገባዋን እያጠናቀረች የነበረችውጋዜጠኛ ወልፍ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ ...
Read More »በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ተደስታችኋል የተባሉ 6 ኢትዮጵያውያን ታስረው፤ አንዱ የ7 ዓመት እስራት እንደተፈረደበት ታወቀ
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምንጮቻችን ከሥፍራው እንደገለፁት ከሆነ፣ የአቶ መለስ ሞት ይፋ በተደረገበት ሰሞን፤ በቤታቸው ውስጥ ተሰብስበው የነበሩት ወጣቶች የታሰሩት፤ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ደስታችሁን ገልጣችኋል፤ ጨፍራቸኋል፤ በሚል ሰበብ እንደሆነ ታውቋል። የታሰሩት ወጣቶች በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን፣ ከእስረኞቹ ውስጥ አህመድ የተባለው ወጣት፤ የ7 አመት እስራት እንደተፈረደበትና፤ የተቀሩት አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። ኢሳት ባለፈው ሣምንት ...
Read More »የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ ዛሬም በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በሚገኙ መስጊዶች ቀጥሎ ዋለ
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ ዛሬም በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በሚገኙ መስጊዶች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ ምርጫው ግን በተያዘለት መርሀ ግብር እሁድ መስከረም 27 ቀን እንደሚቀጥል፤ ባለቤትነቱ የኢህአዴግ የሆነው፤ ፋና ብሮድካስቲንግ፤ በመንግስት የሚደገፈውን የእስልምና ጉዳዮች የፈተዋና የደእዋ ም/ቤት ጠቅሶ ዘገበ። ከአዲስ አበባ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ የተቃውሞ እንቅስቃሴው በአዲስ አበባ በሚገኙ መስጊዶች፤ እንዲሁም በሻሸመኔና ከሚሴ፤ በሀርቡና ...
Read More »ሼክ አላሙዲን ትልልቅ የሊሙ ቡና መሬቶችን፤ በጨረታ አሸንፈው መውሰዳቸው ታወቀ
የሳኡዲ ዜግነት ያላቸው ባለሀበት፤ ሼክ አላሙዲን ትልልቅ የሊሙ ቡና መሬቶችን፤ የሕዝብ ንብረቶችን ወደግል ይዞታ ከሚያዛውረው የፕራይቬታይዜሽን ባለስልጣን በጨረታ አሸንፈው መውሰዳቸው ታወቀ። የባለስልጣኑ ቃላ አቀባይ፤ አቶ ወንድአፍራሽ አሰፋ እንደገለጹት፤ በቀድሞዋ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፤ በኦህዴዷ ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የባለስልጣኑ ቦርድ፤ የስድስቱን ለም የቡና እርሻዎች ጨረታ አሸናፊነት ብቸኛውን ዋጋ ላቀረበው የአቶ አላሙዲን ኩባንያ ሰጥቷል። ለተወሰኑት እርሻዎች ሌሎች ተጫራቾችም ዋጋ መስጠታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ...
Read More »ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያውን መደበኛ ስብሰባ ሰኞ እንደሚያደርግ ምክር ቤቱ አስታውቋል
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያውን መደበኛ ስብሰባ የፊታችን ሰኞ እንደሚያደርግ ምክር ቤቱ አስታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በሚታደሙበት በዚህ መድረክ፤ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሚያደርጉት ንግግር የዓመቱ ሥራ እንደሚጀመርም ተመልክቷል። በወጣው መርሐ-ግብር መሠረት መንግሥት በዓመቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት በፕሬዚዳንቱ ንግግር ይዳሰሳሉ። ...
Read More »በትናንትናው እለት የኢራን መንግስት ዋና ከተማዋ ቴህራን ቦታዎች ላይ አድማ በታኝ ፖሊስ እንዳሰማራ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገበ
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፖሊስ የተሰማራው በሀገሪቱ ላይ የተደረጉ ማእቀቦች በኢኮኖሚው ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ተጽእኖ መኖር ከየአቅጣጫው የህዝብ ተቃውሞ በመፈጠሩ ነው። በተለያዩ ቦታዎች በተደረገው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ግጭት የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች በእሳት መያያዘችው ተዘግቧል። በቴህራን ዋና መገበያያ ቦታ ላይ ቀደም ባሉት የስራ ቀናት ተዘግተው የቆዩት በርካታ የንግድ ቤቶች ሀሙስ እለት ቢከፈቱም፤ በሁሉም ስፍራ አለመረጋጋት እንዳለ ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ካሚል ሸምሱ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኡላማዎች ምክርቤትን ከሰሱ
መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“መንግስት የአህባሽ አስተምህሮን ለማስፋፋት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ያቁም፣ የሀይማኖት መሪዎቻችንን በነጻነት እንምረጥ፣ መሪዎቻችን ይፈቱ” የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተው ተቃውሞአቸውን ካለፈው አመት ጀምሮ በማሰማት ላይ ያሉት የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ተወካይ የሆኑትና በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ካሚል ሸምሱ ሲራጅ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤትን በጠበቃቸው አማካኝነት ከሰዋል። ከሳሹ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ልደታ ...
Read More »በአዲስ አበባ በሚኒባስ ውስጥ ፈንጅ ተጠምዷል በሚል ትርምስ ተፈጥሮ ዋለ
መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት ከቀኑ 4 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ በአዲስ አበባ መርካቶ በአንድ ሚኒባስ ታክሲ ላይ ተጠምዷል በተባለ ፈንጂ ትርምስ ተፈጥሮ ነበር። ረፋዱ ላይ ወደ አውቶቡስ ተራ አምባሰል ሙዚቃ ቤት አካባቢ የደረሰው ሚኒባስ ታክሲ በውስጡ ፈንጂ ተጠምዶበታል በመባሉ ከውስጡ ተሳፋሪ የነበሩ ሰዎች በትርምስ ሲወርዱ እና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሲሸሹ ከፍተኛ ትርምስ የተፈጠረ ሲሆን ...
Read More »መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታሰቢያ ፕሮጀክት ገንዘብ እያሰባሰበ ነው
መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፕሮጀክት የሚውል በሚል በአገር አቀፍ ደራጃ የሚገኙ ነጋዴዎችና ድርጅቶች የገንዘብ መዋጪ እንዲያደርጉ እየጠየቀ ነው። ነጋዴዎቹና ድርጅቶቹ ከመንግስት ተወስኖ የሚሰጣቸውን ገንዘብ የሚከፍሉ ሲሆን ከተመኑ በላይ ለሚከፍሉት ደግሞ ማበረታቻ ይሰጣል። አቶ መለስ የቀብር ስነስርአታቸው በሚፈጸምበት ወቅት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር የሆኑት ሀይለማርያም ደሳለኝ ለመለስ ትልቅ መታሰቢያ ...
Read More »