መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታሰቢያ ፕሮጀክት ገንዘብ እያሰባሰበ ነው

መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፕሮጀክት የሚውል በሚል በአገር አቀፍ ደራጃ የሚገኙ ነጋዴዎችና ድርጅቶች የገንዘብ መዋጪ እንዲያደርጉ እየጠየቀ ነው።

ነጋዴዎቹና ድርጅቶቹ ከመንግስት ተወስኖ የሚሰጣቸውን ገንዘብ የሚከፍሉ ሲሆን ከተመኑ በላይ ለሚከፍሉት ደግሞ ማበረታቻ ይሰጣል።

አቶ መለስ የቀብር ስነስርአታቸው በሚፈጸምበት ወቅት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር የሆኑት ሀይለማርያም ደሳለኝ ለመለስ ትልቅ መታሰቢያ ሙዚየም ገንብተው አስከሬናቸውን ወደዚያው እንደሚያዛውሩት መግለጻቸው ይታወሳል።

አሁን ነጋዴዎች እንዲያዋጡ የሚጠየቁት ገንዘብ ለዚሁ ሙዚየም ማሰሪያ ይሁን አይሁን አልታወቀም።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት የተጀመሩ  ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከፍተና የገንዘብ እጥረት መከሰቱን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት መንግስት ለመሰረተልማት ግንባታዎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲገታ መጠየቁ ይታወሳል።