ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያውን መደበኛ ስብሰባ ሰኞ እንደሚያደርግ ምክር ቤቱ አስታውቋል

መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያውን መደበኛ ስብሰባ የፊታችን ሰኞ እንደሚያደርግ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በሚታደሙበት በዚህ መድረክ፤ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሚያደርጉት ንግግር የዓመቱ ሥራ እንደሚጀመርም ተመልክቷል።

በወጣው መርሐ-ግብር መሠረት መንግሥት በዓመቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት በፕሬዚዳንቱ ንግግር ይዳሰሳሉ። በቀጣይ ቀናት በፕሬዚዳንቱ ንግግር ላይ ተመስርተው የፓርላማ አባላቱ ለሚያነሱት ጥያቄ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፓርላማው ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በሚያደርገው ስብሰባ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አዲስ የካቢኔ አባላት በፓርላማው አቅርበው እንደሚያስጸድቁ ይጠበቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide