በመላ አገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች በነደፉት መርሐግብር መሰረት በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆን፣ መንግስት የሙስሊሙ ጥያቄ ከእጁ እየወጣ መውጣቱን የሚያመለክት ሆኗል። በመቀሌ፣ በመቱ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር፣ በጅማ ፣ ወልቂጤ፣ ጎንደር ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ” መሪዎቻችን ይፈቱ ድምጻችን ይሰማ በቤታችን ሰላም ስጡን” የሚሉ ...

Read More »

በፓትርያርኩ ምርጫ መንግስት ሙሉ በሙሉ እጁን አስግብቶ ነበር ተባለ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ መንግስት እጁን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ እንደነበርና ምርጫው ነጻ፣አሳታፊና ገለልተኛነት በሆነ መልኩ እንዳልተካሄደ ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ የቀድሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ለሶስት ዓመታት ያህል በውጪ አገር ካለው ስደተኛው ሲኖዶስ ጋር ሰላም ለመፍጠር ቀጥሎ የነበረው ጥረት እንዲከሽፍና የፓትርያርክ ምርጫው በተፋጠነ ሁኔታ እንዲካሄድ ...

Read More »

ጉምሩክና ግብር ከፋዮች እየተወዛገቡ ነው

ካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በተከማቸ የአክስዮን ድርሻ ላይ 10 በመቶ ክፍያ እንዲፈጸም ያወጣው መመሪያ አሁንም ከከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ጋር እያወዛገበው ይገኛል፡፡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 መሰረት አክስዮን ማኀበራት ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን የትርፍ ድርሻ 10 በመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ቢሆንም ላለፉት ዓመታት በህግ አስፈጻሚው ችግር አዋጁ ...

Read More »

የመቀሌ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጡ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች በውሀ እና በመብራት እጦት ለ ዓመታት እየተንገላታን እንገኛለን ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች ለኢሳት ዘጋቢ  እንደገለፁት ማዘጋጃ ቤቱ በሰጣቸው ቦታ ቤት ሠርተው ከገቡ ሁለት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፤እስካሁን ድረስ ውሀ እና መብራት ሊገባላቸው አልቻለም። ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለሚለከተው የመንግስት አስተዳደር ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት መፍትሔ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ ...

Read More »

በኢትዮጵያ “የጥበብን ስራ እንኳ በነጻነት ማካሄድ አይቻልም” ሲሉ አንድ የጀርመን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ተናገሩ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከኢትዮጵያ ለቅቆ የወጣው የጀርመን ሄንሪክ ቦል ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ፓትሪክ በርግ ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ስለለቀቀበት ምክንያት ለብሉበርጉ  ዊሊያምስ ዳቪሰን ሲናገሩ “በኢትዮጵያ  የጥበብ ስራ እንኳን በአሁኑ ጊዜ በጥርጣሬ የሚታይ ነው፣  ከመብት ጋር የተያያዘውን ስራችሁን አቁሙ በመባላችን ስራችንን ለቀን ወጥተናል” ብለዋል። የሲቪክ ሶሳይቲና ቻርቲ ህግ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውርስ መሆኑን ...

Read More »

ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው    ስት ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸው በትግራይ አጋሜ አውራጅ በስቡህ ወረዳ የተወለዱት ብፁዕ አቡነ ማትያስ   6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የፊታችን እሁድ ይሾማሉ። በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ማትያስ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ እጁን የከተተው የሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት ምርጫም እንደሆኑ አስቀድሞም ሲነገር የነበር ሲሆን፣ እርሳቸውን ...

Read More »

በጅጅጋ የአማራ ተወላጆች ቤታቸው እየተነጠቁ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸውን ገለጡ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በክልሉ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት ፣ ካለፉት 40 አመታት ጀምሮ በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ቤቶቻቸውን እያስረከቡ ለጎዳና ህይወት ተዳርገዋል። እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች የነበሩዋቸው የአማራ ተወላጆች፣ ለሶማሊ ተወላጆች እንዲያስረክቡ በመዳረጋቸው ብዙዎች ድርጅቶቻቸውን አስረክበው ወደ መሀል አገር ሄደዋል። ተወልደው ያደጉበትን ቦታ አንለቅም በማለት እስካሁን ...

Read More »

የኩማ አስተዳደር ህዝቡን ማፈናቀሉን በዘመቻ መልክ ጀመረ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ከስልጣኑ ለመልቀቅ የሁለት ወራት ጊዜያት የቀሩት የኩማ አስተዳደር“ፈጣን ለውጥ አምጪ” በሚለው ፕሮግራሙ በተለያዩ አካባቢዎች በልማት ስም የአዲስአበባን ነዋሪ የማፈናቀል ስራውን በዘመቻ መልክ እያከናወነ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ከባቡር፣ከመንገድ እና በኢንቨስትመንት ስም በተለይ በቦሌ፣በቂርቆስ፣በልደታ፣በኮልፌ ቀራኒዮ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተሞች ካለፉት ሁለት ሳምንት ወዲህ ዜጎችን ከሕግና ስርዓት ውጪ የማፈናቀሉን ሥራ ተፋፍሞ መቀጠሉን ከየአካባቢው ያገኘናቸው መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ ...

Read More »

በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ አዲስ የሚሾሙትን ፓትሪያርክ ህዝቡ እንዳይቀበል ጥሪ አቀረበ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ሲኖዶሱ ለኢሳት በላከው መግለጫ አገሪቱን እስር ቤት አድርጎ ህዝቡን በባርነት ለመግዛት የተነሳው ሀይል የቤተ ክርስቲያንን ሀዋርያዊና የነጻነት አንደበት ለመዝጋት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች ተቀዳሚውና ዋነኛው ለህገ ቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ ፈቃድ ተገዢ የሆነ ሰው በፓትሪያርክ ስም በቤተ ክርስቲያን መንበር ላይ በማስቀመጥ ቤተክርስቲያንን መድፈር ነው ብሎአል። ሲነዶሱ ” ላለፉት 21 አመታት በመንግስት አስተባባሪነትና ደጋፊነት በህገ ወጥ መንገድ ...

Read More »

ተከራካሪውን በማህበራዊ ፍርድ ቤት ውስጥ በሽጉጥ የገደለው ፖሊስ አልተያዘም

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ድርጊቱ የተፈጸመው ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት በአስኮሪ ከተማ  ነበር። ወ/ሮ ወርቅነሽ ኢፋ የተባሉ አርሶአደር በ2002 ዓም የልማት ጀግና ተብለው ተሸልመዋል። ወ/ሮ ወርቅነሽ ሳጂን ኣካለወልድ ተክለማርያም የተባለ የእንጀራ ልጅ አላቸው። ግለሰቡ የእንጀራ እናቴ በአደራ የሰጠሁዋትን  መሬት ክዳለች በሚል በፍርድ ቤት ክስ መሰረተ። ከፍተኛው ፍርድ ቤትም ለሳጅን አካለወርድ መፍረዱን ተከትሎ ወ/ሮ ወርቅነሽ ስድስት ኪሎ ...

Read More »