በአምስት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ 196 ፕሬሶች ከሕትመት ውጪ ሆኑ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በኢትዮጽያ ባለፉት አምስት ዓመታት  በፖለቲካ፣በማኀበራዊ፣በኢኮኖሚ ፣በስፖርት፣በሃይማኖት፣በፍቅር፣ በኪነጥበብ እና በመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች አተኩረው ይታተሙ ከነበሩ 235 የፕሬስ ውጤቶች መካከል 196 ያህሉ በተለያየ ምክንያት ከህትመት ውጪ መሆናቸውን የብሮድካስት ባለስልጣን ሰሞኑን በድረገጹ በለቀቀው መረጃ አስታወቀ፡፡ ባለስልጣኑ ከየካቲት 2001 እስከ ጥር 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ለ91 ጋዜጦችና ለ144 ያህል መጽሔቶች በድምሩ ለ235 ያህል የፕሬስ ውጤቶች የምዝገባ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አስታውሶ ...

Read More »

የሳውዲው ም/ል የመከላከያ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ወቀሱ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ምክትል የመከላከያ ሚኒሰትሩ ካሊድ ቢን ሱልጣንን በመጥቀስ ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው፣ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ምትገነባው ፕሮጀክት ለሱዳንና ግብጽ ከፍተኛ አደጋ አለው በማለት ተናግረዋል። ግድቡ በ700 ሜትር ከፍታ ላይ የሚሰራ በመሆኑና 70 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሀ የሚይዝ በመሆኑ፣ ግደቡ ቢፈርስ ሱዳን ሙሉ በሙሉ ስትሰምጥ፣ የግብጽ አስዋን ግድብ ደግሞ አደጋ ያጋጥመዋል ብለዋል ሚኒስትሩ። ግብጽ ሌላ ...

Read More »

የአምስት አመቱን የእድገት እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት አጋጠመ

የካቲት ፩፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሶሶት አመት በፊት የነደፉት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ሊጠናቀቅ ሁለት አመታት ብቻ የቀሩት ቢሆንም፣  በቀሪዎቹ አመታት ውስጥ ዋና ዋና የሚባሉትን ፕሮጀክቶች ለፍሬ ለማብቃት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት አጋጥሟል። የአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት መንግስት በስሜት ላይ ተመስርቶ የነደፈውን እቅድ መልሶ እንዲከልሰው ግፊት በማድረግ ላይ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲህ አይነቱን እርምጃ ለመውሰድ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ውብሸትና አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር ሊፈቱ ነው

  የካቲት ፩፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ መሆኑን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ገለጸ። ተመስገን ፦<<አቃቤ ህግ ዕዳ አለብህ >>በሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ  ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና አቶ ዘሪሁን ገብረ-እግዚአብሔር  በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር  አብረው እንደሚፈቱ ምንጮች አረጋግጠውለታል። <<ይህ የሚደረገው ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም ...

Read More »

የሽግግር ምክር ቤቱ 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ

የካቲት ፩፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ከፌብርዋሪ 22 እስከ 24 ቀን 2013 በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ 2 ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ በጉባኤው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ  ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገለጠ ምክር ቤቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ ” ጉባኤው የስራ አስኪያጅ፥ የኦዲተርና የአካባቢ ምክርቤቶች ሪፖርቶችን አዳምጦና ተወያይቶ ማጽደቁን” ጠቅሷል። ጉባኤው የምክር ቤቱ ...

Read More »

የደህንነት መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ከአገር እንዳይወጡ አዘዘ

የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ 15 የትኬት እና 30 የኤርፖርት ሰራተኞችን ከስራ ካባረረ በሁዋላ ከአገር እንዳይወጡ አገደ። ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሀብታሙ ጫኔ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ኢማን ያሲን፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛ ኤፍሬም፣ ይገርማል ታደሰ፣ ሰለሞን ይብራህ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤን ጨምሮ በርካታ ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፣ አየር መንገዱ ለደህንነት እና አሚግሬሽን መስሪያ ቤት ...

Read More »

ስድስተኛ ፓትርያር ለመሾም የሚደረገውን ጥድፊያ አጥብቀው እንደሚቃወሙ በኒውዮርክና አካባቢው የሚገኙ የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን አስታወቁ

የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ምዕመናኑ ባወጡት መግለጫ  ስድስተኛ ፓትርያርክ ለማስቀመጥ በአገር ቤት እየተደረገ ያለውን ጥድፊያ እንደሚቃሙትና በውጪ የሚገኘው ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ እንደተቀበሉት ገልጸዋል። ይህን ያደረጉትም አንዱን ወገን አግልለው አንዱን ወገን ለመደገፍ ሳይሆን መጽሐፍ ፦<<እውነትን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው>>ባለው መሰረት ከሁለቱም ወገን የተባሉትን እና እየሆነ ያለውን ነገር ከሥረ-መሰረቱ በመመርመር እንደሆነ አስረድተዋል። <<በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ...

Read More »

የ6ኛው ፓትርያርክ እጩዎች ምርጫ አከራካሪ እንደሆነ ቀጥሏል

የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የ6ኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ በእጩነት ባቀረባቸው 5 ሊቃነ ጳጳሳት ዙሪያ ተወያይቶ ለማፅደቅ ባሳለፍነው ቅዳሜ የተሰበሰበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ፣ ያለ አንዳች ውሳኔ መበተኑ ታወቀ። እንደ ሃራ ተዋሕዶ ብሎግ ዘገባ የዕለቱ የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባዔ፣ በተለይም ለእጩነት በቀረቡት አባቶች መካከል ከረር ያለ የቃላት ልውውጥ የተስተናገደበት፤ ዋና ጸሐፊውን ተክቶ የኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረበውየሕዝብ ...

Read More »

በብራሰልስ የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዘግጅት ተካሄደ

የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-እውቁ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ በተገኘበት ትናንት የካቲት 17፣2005 ዓም የተካሄደው የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት በቤልጂየም የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። ከሰአት በሁዋላ የተጀመረው ስብሰባ የተከፈተው በቤልጂየም የኢሳት የገቢ አሰባሳቢ ግብረሀይል ወኪል በሆኑት በአቶ ገበየሁ ደስታ ነበር። በመቀጠልም ሌላው የኮሚቴ አባል አቶ ኤፍሬም ሻውል ኢሳት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰጠውን ግልጋሎት የተመለከተ ጥናታዊ ...

Read More »

ፓትሪያርክ ለማሾም የሚደረገ ው የምረጡኝ ዘመቻ ቀጥሏል

የካቲት ፩፮ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ የፓትሪያርክ የምርጫ ቅስቀሳ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች ገለጹ። ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገብ የቆየውን የፓትሪያርክ የምርጫ ቅስቀሳ፣ ፓትሪያርክ ይሆናሉ ተብሎ ባለፈው ሳምንት በተሰራጨው ዘገባ ላይ ስማቸው የተነሳው አቡነ ሳሙኤል አረጋግጠዋል። አቡነ ሳሙኤል ለአዲስ አድማስ በሰጡት አጭር ቃለምልልስ እንደገለጡት በምርጫው ዙሪያ የተለያዩ ቡድኖች ተፈጥረው ...

Read More »