የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሀአሬጽ የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ እንደዘገበው ሁለቱ አትሌቶች የማራቶን ሩጫቸውን በማቋረጥ ነው ባለፈው አርብ ፣ ማርች 1፣ 2013 የጠፉት። ሜላት መኮንን እና ማህሌት ዘለቀ የተባሉ የ24 እና 25 አመት እድሜ ያላቸው አትሌቶች የጠፉት በደቡብ ቴላቪቭ ሲሆን፤ የ እስራኤል ፖሊስ አትሌቶቹ ሆን ብለው እንደጠፉ ገልጿል። ሁለቱም አትሌቶች ፓስፖርታቸውን እና ሌሎች እቃዎቻቸውን ሁሉ በመተው በሩጫ ...
Read More »ኢህአዴግ በርካታ የመረጃ ሰዎችን በሆቴል ቤት ሰራተኝነት ስም ቀጥሮ አሰማራ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ሻሂ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ውስጥ የ ኢህአዴግ መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወጣት ሴቶችን በማሰልጠን እና አንድ ለአምስት በመጠርነፍ መረጃ እንዲያቀርቡ እያሰማራ እንደሚገኝ ታውቋል። መንግስት ከሻሂ ቤቶችና ሆቴሎች ስራ አስኪያጆች ጋር በሚስጢር በመነጋገር ደሞዝ የሚከፍላቸውን አስተናጋጆች አሰማርቶ ከህዝቡ መረጃ እየሰበሰበ ነው። ቀደም ሲል መንግስት ሰዎችን በማስረግ ብቻ ...
Read More »ታዛቢዎች የቤተክህነቱ ” ጅሀዳዊ ሀረካት” ያሉት መጽሀፍ እየተሰራጨ ነው
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደት የሚገኙነትን አራተኛው ፓትርያርክ ጨምሮ በውጪ አገር ያሉ አባቶችን ስሕተት፣ ጥፋትና ዕርቀ ሰላሙን ማፍረስ የሚያትት እንዲሁም ፓትርያርኩ ከሥልጣን የወረዱት ተገደው ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ መሆኑን የሚያትት ባለ 52 ገጽ አነስተኛ መጽሐፍ ታትሞ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ደጀሰላም ዘግቧል። ይኸው በአቡነ ማቲያስ ዕለተ ሲመት ጀምሮ መሰራጨት የጀመረው መጽሐፍ በብዙዎች አባባል የቤተ ክህነቱ “ጂሐዳዊ ሐረካት” የተሰኘ ...
Read More »ወታደሮች በኦጋዴን የውሀ ጉድጋዶችን በመያዝ ህዝቡን እያሰቃዩት ነው ተባለ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሰራዊቱ እና የሶማሊ ልዩ ምልሻ በጋራ ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የውሀ ጉድጓዶችን ተቆጣጥረው ህዝቡን ገንዘብ በማስከፈል እያሰቃዩት ነው። ድርጅቱ ለአለማቀፍ ድርጅቶች ባሰማው የድረሱልን ጥሪ ሰራዊቱ በአንድ ሰው እና በእንስሳ ቁጥር ልክ ገንዘብ እያስከፈለ ነው። አንድ ቤተሰብ ወደ ውሀ በወሰዳቸው ግመሎች፣ ፍየሎችና በጎች ልክ ለውሀው እንደሚከፍል ...
Read More »በኬንያ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ እየመሩ ነው
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ ተቀናቃኛቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን በሰፊ ልዩነት እየመሩ ነው። እስካሁን በተደረገው ቆጠራ ሚስተር ኬንያታ 53 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው 42 በመቶ አግኝተዋል። የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ሀላፊ እንደተናገሩት ውጤቱ ጊዜያዊ በመሆኑ፣ ህዝቡ በትእግስት እንዲጠብቅ መክረዋል። እስካሁን አንድ ሶስተኛው ድምጽ የተቆጠረ ሲሆን ኡሁሩ ኬንያታ በሰፊ ድምጽ እየመሩ ...
Read More »33 የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የመግባቢያ ሰነድ ፈረሙ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲዎቹ የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት ባለፈው ቅዳሜ ነው። በፊርማ ስነስርአቱ ላይ የፓርቲዎቹ ጥምረት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ ” የተፈረመው ሰነድ የመጀመሪያ የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን ገልጠው፣ የኢህአዴግ የ21 አመታት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ኢትዮጵያን ለረሀብ፣ ለድህነት፣ ለስደት፣ ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ ለኢፍትሀዊነት፣ ለሙስና ዳርጓታል ብለዋል። የአዲሱ ስብስብ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በበኩላቸው በዚህ ታሪካዊ የአድዋ ቀን ...
Read More »የሰብዓዊ መብት ሊጉ የዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው አለ።
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ሊግ በቅርቡ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ 10 የኦሮሞ ተወላጆች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ መደረጋቸውን አጥብቆ አወገዘ። የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከትምርታቸው የታገዱትን ተማሪዎች ፎቶ አስደግፎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገዱት የመጀመሪያ ሴሚስተር ፈተናቸውን አጠናቅቀው የሁለት ሳምንት እረፍት ወስደው ከተመለሱ በሁዋላ ነው። ሊጉ ከውስጥ የደረሱትን መረጃዎች ...
Read More »የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አርቲስት ታማኝ በየነ የመራው የኢሳት የአውሮፓ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ተጠናቀቀ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት ሳምንታት በአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ስለ ሰብአዊ መብቶች ቀላል፣ ግልጽ እና አስተማሪ በሆነ መንገድ እያቀረበ ለኢሳትም የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ የሰራው እውቁ አርቲስት ታማኝ በየነ የአውሮፓ ጉዞውን ቅዳሜ ማርች 2፣ 2013 በጀርመንዋ የፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ዝግጅትና ስነስርአት አጠናቋል። አርቲስት ታማኝ ጉዞውን በጄኔቫ ስዊዝርላንድ ጀምሮ በ ስዊድን ስቶክሆልም፣ በ ኖርዌይ ኦስሎ ፣በ ጀርመን ...
Read More »በጀርመን የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን ፣ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል። ”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!” ፣”የፕሬስ ነጻነት ይከበር!” ”ሃሳብን ...
Read More »117ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት በሄግ ፣ ኔዘርላንድስ ተካሄደ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ድባቅ በመምታት የኢትዮጵያን ነጻነት ያስከበሩበትን 117ኛውን የአድዋ ድል፣ የተለያዩ ምሁራን በአካል በተገኙበትና በስካይፕ በተደረገ ንግግር ታስቦ ውሎአል። የቀድሞው የህወሐት መስራች እና መሪ የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ እና ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ በአካል ፣ ፕ/ር ጌታቸው መታፈሪያ እና አቶ ኪዳኔ አለማየሁ ...
Read More »