ሁለት የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድራቸውን አቋርጠው ጠፉ

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ሀአሬጽ የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ እንደዘገበው ሁለቱ አትሌቶች የማራቶን ሩጫቸውን በማቋረጥ ነው ባለፈው አርብ ፣ ማርች 1፣ 2013 የጠፉት።

ሜላት መኮንን እና ማህሌት ዘለቀ የተባሉ የ24 እና 25 አመት እድሜ ያላቸው አትሌቶች የጠፉት በደቡብ ቴላቪቭ ሲሆን፤ የ እስራኤል ፖሊስ አትሌቶቹ ሆን ብለው እንደጠፉ ገልጿል።

ሁለቱም አትሌቶች  ፓስፖርታቸውን  እና ሌሎች እቃዎቻቸውን ሁሉ በመተው በሩጫ ልብሳቸው መጥፋታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

አትሌቶቹ እስካሁን ለፖሊስም ሆነ ለአካባቢው ባለስልጣናት ስለሁኔታው አላመለከቱም።