(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010) የአባይ ግድብ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ። በገንዘብ እጥረት ምክንያት ስራው እየቀዘቀዘ የመጣው የአባይ ግድብ ፕሮጀክት በሰራተኞች በተነሳ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄና በሚደረስባቸው የመብት ረገጣ ምክንያት አድማ እንደተመታበት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከኢንጅነር ስመኘው በቀለ ግድያ በኋላ የአባይን ግድብ በሃላፊነት የተረከቡት አዲሱ ስራ አስኪያጅም የሰራተኛውን ጥያቄ መፍታት እንዳልቻሉ ምንጮች ጠቅሰዋል። በትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ድርጅት ኢፈርትና በህወሃት ጄነራሎች በሚመራው ሜቴክ ...
Read More »በቴፒ ከተማ 5 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010 በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ 5 ሰዎች በደቡብ ክልል ልዩ ሃይል መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጸ። በአካባቢው ብሔርን ተኮር ያደረገ ግጭት ተባብሶ መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች አረጋግጠዋል። ግጭቱን ለማብረድ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ከዚህ ቀደሞ ወደ አካባቢው አምርተው ከሕዝቡ ጋር ቢመክሩም ችግሩ አሁንም መፍትሄ አላገኘም ተብሏል በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች በመተሳሰብና በአንድነት ለበርካታ ዘመናት አብረው ኖረዋል። ባለፉት 27 ...
Read More »አቶ አብዲ ኢሌ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አቶ አብዲ ኢሌ ፍርድ ቤት ቀረቡ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚወነጀሉት አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። አቶ አብዲን ጨምሮ ወይዘሮ ራሃማ መሐመድ፣ አቶ አብድራዛቅ ሰህኒ እና አቶ ሱልጣን መሐመድ ችሎት የቀረቡ ...
Read More »በአማሮ ወረዳ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
በአማሮ ወረዳ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኮሬና በአጎራባቹ የጉጂ ብሔረሰቦች መሃከል ከ15 ወራት በላይ ያስቆጠረዉን ግጭት ለማስቆም እርምጃ በመወሰድ ላይ መሆኑን ተከትሎ፣ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል። ሰልፈኞች ብሄርን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ ይቁም፣ ለ 15 ወራት የተዘጋው ከዲላ አማሮ አዲስ አበባ መንገድ ይከፈትል፣ እየሞትንም ቢሆን ሃገራዊ ለዉጡን በመደገፍ ተደምረናል፣ያለ ሕዝብ ...
Read More »የራያ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰፋሪዎች መምጣታቸውን ተቃወሙ
የራያ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰፋሪዎች መምጣታቸውን ተቃወሙ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በትግራይ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ትዕዛዝ 600 የሚሆኑ በአድዋና አዲግራት አካባቢ የነበሩ ሰዎችን በአላመጣና አካባቢው እንዲሰፍሩ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተገቢ አይደለም። የአካባቢው ተወላጆች እንደሚሉት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች መሬት አልባ ሆነው እንዲሁም የመሬት ጥያቄ አቅርበው መልስ ባላገኙበት ሁኔታ አርሶአደሮችን አምጥቶ ማስፈር በአካባቢው ...
Read More »የአባይ ግድብ ሰራተኞች ያስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው
የአባይ ግድብ ሰራተኞች ያስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰራተኞቹ አድማውን የጀመሩት ከደሞዝ እና ከአግልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ነው። ሰራተኞቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የበረሃ አበል መስተጓጎል፣ የሚከፈላቸው ክፍያ እና የሚሰሩት ስራ አለመመጣጠን ና የደህንነት ጅግሮች አድማውን እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ይገልጻሉ። ማኔጅመንቱ ሰራተኞችን ለማወያየት እቅድ መያዙን አስታውቋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን ...
Read More »አምስት የኬንያ ወታደሮች በተጠመደ ፈንጂ ተገደሉ።
አምስት የኬንያ ወታደሮች በተጠመደ ፈንጂ ተገደሉ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ ዛሬ በወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ ሆነው ለሰብዓዊ እርዳታ ሲጓዙ የነበሩ አስር የኬንያ ወታደሮች በወደቧ ከተማ ላሙ ሲደርሱ ተሽከርካሪያቸው በተጠመደ ፈንጂ ጋይቶ አምስቱ ሞተዋል። ወራደሮቹ በኩዋንጋ ሳንኩሪ ጎዳና ለችግረኞች የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ የተመደቡ መሆናቸውን የኬንያ መከላከያ አስታውቋል። የአልሸባብ ሰርጎ ገቦች እንዳሉበት በሚነገው በተጠቀሰው የኬንያ ...
Read More »ሬክ ማቻር የሰላም ስምምነቱን የመጨረሻ ምዕራፍ አልፈርምም አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 22/2010) የደቡብ ሱዳን አማጽያኑ መሪ ሬክ ማቻር የሰላም ስምምንቱን የመጨረሻ ምዕራፍ አልፈርምም ማለታቸው ተሰማ። ይህን ተከትሎም በደቡብ ሱዳን ሰላም ለማስፈን የተጀመረው ጥረት ጥቁር ጥላ አጥልቶበታል ብሏል አፍሪካ ኒውስ በዘገባው። በሬክ ማቻር በኩል እንደ ምክንያት የቀረበው የሰላም ስምምነቱ ለተቃዋሚዎች ዋስትናን አያረጋግጥም የሚል ነው። በ2013 የተቀሰቀሰውና ከ10 ሺ በላይ ንጹሃን ዜጎች እልቂት ምክንያት ለሆነው የደቡብ ሱዳን የርስበርስ ግጭት ማብቂያ ይሆናል ...
Read More »አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ አዲስ አበባ ገባች
(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 22/2010) ታዋቂዋ አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ከ27 አመታት በኋላ አዲስ አበባ ስትገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላት። አርቲስት አለም ፀሐይ ወዳጆ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የጥበብ አፍቃሪዎችና ወዳጆቿ እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦቿ አቀባበል አድርገውላታል፡፡ ከአለም ጸሀይ ወዳጆ ጋር አርቲስት ተክሌ ደስታ እና አበበ በለውም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በተለያዩ የጥበብ ስራዎች በተለይም በትወና እና በግጥሞቿ ትታወቃልች -አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ። ...
Read More »መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 22/2010) የፌደራል መንግስቱ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ ተጠየቀ። የፌደራል መንግስቱ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገባ የጠየቀው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ነው። ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ እንዳለው በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ ህወሓት እየፈፀመ ያለው በደል ወደ ባሰ አደጋ ሊሸጋገር ይችላል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ እንደገለጸው የትግራይ መንግስት በወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት አካባቢ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ከመንግስት ግምጃ ቤት ...
Read More »