አምስት የኬንያ ወታደሮች በተጠመደ ፈንጂ ተገደሉ።

አምስት የኬንያ ወታደሮች በተጠመደ ፈንጂ ተገደሉ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ ዛሬ በወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ ሆነው ለሰብዓዊ እርዳታ ሲጓዙ የነበሩ አስር የኬንያ ወታደሮች በወደቧ ከተማ ላሙ ሲደርሱ ተሽከርካሪያቸው በተጠመደ ፈንጂ ጋይቶ አምስቱ ሞተዋል።
ወራደሮቹ በኩዋንጋ ሳንኩሪ ጎዳና ለችግረኞች የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ የተመደቡ መሆናቸውን የኬንያ መከላከያ አስታውቋል። የአልሸባብ ሰርጎ ገቦች እንዳሉበት በሚነገው በተጠቀሰው የኬንያ ክፍለ ሀገር ተመሣሳይ ጥቃት ሲፈፀም የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።
ናይሮቢ በሞቃዲሾ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ማድረጓን በመቃወም የአልሸባብ ሚሊሻዎች በተደጋጋሚ በኬንያ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ይታወቃል። አልሸባብን ለመዋጋት በአፍሪቃ ህብረት ጢር ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ወታደር ካሰለፉት ሀገሮች መካከል አንዷ ከፀንያ ናት።