አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ አዲስ አበባ ገባች

 (ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 22/2010) ታዋቂዋ አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ከ27 አመታት በኋላ አዲስ አበባ ስትገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላት።

አርቲስት አለም ፀሐይ ወዳጆ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የጥበብ አፍቃሪዎችና ወዳጆቿ እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦቿ አቀባበል አድርገውላታል፡፡

ከአለም ጸሀይ ወዳጆ ጋር አርቲስት ተክሌ ደስታ እና አበበ በለውም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በተለያዩ የጥበብ ስራዎች በተለይም በትወና እና በግጥሞቿ ትታወቃልች -አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ።

አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ  በአሜሪካን ጣይቱ የተሰኘ የጥበብ ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅም ናት።

በጣይቱ የባህል ማዕከል በርካታ የመድረክ ድራማዎችንና ልዩልዩ የግጥም  ስራዎችን እንዲቀርቡም ያደርገች እርቲስት ነች።

ላላፉት 27 አመታት በኢትዮጵያ ወስጥ የነበረውን አገዛዝ በመቃወም በስደት የኖረችው አርቲስት አለምጸሀይ ወዳጆ አዲስ አብበባ ስትገባ ደማቀ አቀባበል ተደርጎላታል።

አርቲስት አለም ፀሐይ ወዳጆ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የጥበብ አፍቃሪዎችና ወዳጆቿ እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦቿ አቀባበል አድርገውላታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አርቲስት አልምጸሐይ ወዳጆን ጨምሮ ከረጅም ዓመታት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሃገራቸው የተመለሱትን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን አርቲስት ዓለምፀሓይ ወዳጆ፤ አርቲስት አበበ በለው እና አርቲስት ተክሌ ደስታን በጽሕፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፥ በሀገሪቱ የተፈጠረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ በቀረበው ጥሪ መሰረት አርቲስቶቹ ወደ እናት ሃገራቸው መመለሳቸው የሚያስደስት መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ ጊዜም ለውጡን በርቀት ሳይሆን በቅርበት ተጋግዞ መደገፍ እንደሚገባም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

አርቲስቶቹ በበኩላቸው ለረጅም ጊዜ ወደ ናፈቋት እናት ሃገራቸው ለመመለስ ዕድል በመፈጠሩ እና በመንግስት በኩል በተደረገላቸው መልካም አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ወደፊትም ሙያዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል።