ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-” የኢህአዴግ አባላትን ፖለቲካዊና ርእዮተ-ዓለማዊ ብቃት ለማሳደግ ለአርሶ አደሩና ዝቅተኛ የትምህርት ዝግጅት ላላቸው አባላት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣንና ከፍ ያለ የትምህርት ዝግጅት ላላቸው ደግሞ አዲስ ራእይ መጽሄትን እና አብዮታዊ ዲሞክራሲ መጽሄትን የይዘት እና የስርጭት ለውጥ በማድረግ ” ለማሰራጨት ቢሞከርም ፣ አመራሩም አባላቱም ለማንበብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለኪሳራ ተዳርገናል በማለት ድርጅቱ አስታውቋል። ይህ የተገለጸው ብአዴን ...
Read More »በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የፖሊሶችና እና የደህንነት ሀይሎች እጅ አለበት ተባለ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ዞን በከምሴ ከተማ ባለፈው ሳምንት በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ወደ የመን እና እና ሳውድ ኣረቢያ በህገ ወጥ ዝውውር ከሚጓዙ ወጣቶች ጀርባ ደህንነቶችና የፖሊስ ሃይሎች መኖራቸው ተመልክቷል። የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት እንድሪያስ አሊ ሸቱ ለኢሳት እንደተናገሩት የህገወጥ ዝውውሩ ችግር አገራዊ ይዘት ያለው ቢሆንም በህገወጥ ዝውውሩ ላይ እየተሳተፉ በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች ላይ ...
Read More »አትሌት ቀነኒሳ በ10 ሺ ሜትር አሸናፊ ሆነ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካ ውስጥ በኢዩጂን በተደረገው የዳይመንድ ሊግ አትሌቲክስ ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺህ ሜትር ውድድር በማሸነፍ ወደ ቀድሞ ክብሩ መመለሱ ታወቀ። በ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት፣ እንዲሁም የኦሎምፒክ ሶስት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ የሆነው ቀነኒሳ በደረሰበት ጉዳት ለረጅም ጊዜ ከውድድር ርቆ መቆየቱ ይታወሳል። ምንም እንኳን ቀነኒሳ ከጉዳቱ በደንብ ሳያገግም ባለፈው የለንደን ኦሎምፒክ ...
Read More »184 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወድቆ ያገኘው ኢትዮጵያዊ ገንዘቡን መለሰ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፅዳት ሰራተኛ የሆነው ወጣት ብርሃኑ ጀምበሬ አይሮፕላን ሲያፀዳ በካኪ ወረቀት ተጠቅልሎ ወድቆ ያገኘውን 184 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለባለቤቱ እንዲመለስ ማድረጉ ታወቋል። ወጣት ብርሃኑ በወቅቱ የተሰማውን ስሜት ሲገልፅ “በመጀመሪያ ገንዘቡን ሳገኝ ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ አይቼ ስለማላውቅ በጣም ደነገጥኩ። በዚህም የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ተጋብቼ ጥቂት ደቂቃዎች ...
Read More »የተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ኑሮ እንዳማረራቸው ገልጹ
ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ፣ በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች በመዘዋወር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማነጋገር እንደዘገቡት ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል በ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ እየተሰቃየ እንደሚገኝ አመለክተዋል። በጎዲዮ ዞን የሚገኙ አንድ በሽመና ስራ ላይ የሚሰሩ አዛውንት ” ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ እንደሆነባቸው ተናግረው፣ ጊዜው አስቸጋሪ መሆኑን” ገልጸዋል። ( ጌዲዮ 00070) ባለቤታቸውም እንዲሁ ” እሱ የፈጠረን ...
Read More »ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ድጋፋቸውን እየገለፁ ነው
ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል። <<ሰማያዊ ፓርቲ በሰልፉ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የኛም ጥያቄዎች ናቸው>> ያለው አንድነት ፓርቲ፤ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ሰልፉ በመውጣት ድምጻቸውን ያሰሙ ዘንድ መልእክት አስተላልፏል። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ፤ ፓርቲያቸው -የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ከልብ የሚደግፍ ...
Read More »በአንድ አመት ውስጥ 19 የዳንግላ ከተማ ፖሊሶች መሳሪያቸውን እንደያዙ የገቡበት አልታወቀም
ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል ፖሊስ በ9 ወሩ የግምገማ ሪፖርት ላይ እንደገለጸው 19 የዳንጋላ ፖሊሶች እስከነ መሳሪያቸው ተሰውረዋል። ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደገለጹት ፖሊሶቹ ራሱን ይፋ ያላደረገውን እና በ አዊ ዞን በጃዊ በረሀ በስፋት የሚንቀሳቀሰውን አዲስ ወታደራዊ ሀይል ተቀላቅለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደሮቹ እንቅስቃሴያቸውን በማስፋት አንዳንድ መጠነኛ የሚባሉ ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው። የፖሊስ የጸጥታ ሃይሎችን መጥፋት ተከትሎ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ድህረ ገጾችን ለማፈን 26 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለቻይና መንግስት ፈጸመ
ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአስተማማኝ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ የደህንነት ሰራተኛ ባገኘው መረጃ መንግስት ለስርአቱ አደጋ ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን የመገናኝ ብዙሀን ወደ አገር ቤት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ወደ 26 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መክፈሉን ለማወቅ ተችሎአል። በቁጥር አንድ እንዲታፈን ትእዛዝ የተላለፈበት ኢሳት ሲሆን ድህረገጹ ራዲዮው እና ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ እንዲታፈን ስምምነት ላይ ተደርሷል። ...
Read More »የብአዴን ወጣቶች ሊግ አባላት ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈን ለመታገል እምነትም ጽናትም የለንም አሉ
ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ይህን የተናገሩት በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የብአዴን ወጣቶች 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ በክልሉ ካለው 20 ሚልዮን ህዝብ መካከል 429 ሺ 520 የሚሆኑ ወጣቶችን አባል አለኝ የሚለው ብአዴን ከአደገኛ ቦዘኔነት እስከ ልማት አርበኛ ስም የሚነግድበት ወጣት ከገዥው ፓርቲ ያተረፈው ኪሳራ መሆኑን ተሰብሳቢዎች በአስተያየት አመልከተዋል፡፡ ከመላው የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ3000 በላይ ወጣቶች ...
Read More »መንግስት በጉምሩክ ባለስልጣናት ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደ ሌሎች ባለስልጣናት ማዞር ፈርቷል ተባለ
ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደሌሎች በሙስና የሚጠረጠሩ ባለስልጣናት ለማስፋት ፍርሃት እየታየበት መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ከኢትዮምህዳር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልለስ ገልጸዋል፡፡ ዶክተሩ ግንቦት 20 ለወጣው ኢትዮምህዳር ጋዜጣ እንደተናገሩት “በሙስና ተከስሰው ወደወህኒ የወረዱት የአንድ መ/ቤት ሠራተኞችና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሐብታሞች ...
Read More »