ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሜሪካን ኤምባሲ በተካሄደው የአምባሳደሮቹ ስብሰባ ላይ በቅርቡ የተመሰረተውንና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙበትን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ የቻለውን ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል። በተለምዶ ‘‘የኢትዮጵያ ለጋሾች ቡድን’’ የሚል መጠሪያ ያለውና የአሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በአባልነት የሚገኙበት የለጋሾች ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ የተቃዋሚ አመራሮች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የመከላከያ ሰዎች በየቀበሌው እየዞሩ ህዝቡን በማስፈራራት ላይ መሆናቸው ታውቋል
ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ልዩ ፖሊሶች በቶዮታ ፒክ አፕ መኪኖች ላይ ሆነው በየመንደሩ በመዞር ህዝቡን ሰብስበው እያነጋገሩ ነው። ወታደሮቹ ” የማንነት ጥያቄዎችን ያቀረባችሁት እናንተ ናችሁ ወይስ ጸረሰላም ሀይሎች ናቸው?” በማለት ጥያቄ ሲጠይቁ መዋላቸው ታውቋል። ድርጊቱ በሚቀጥሉት ቀናት በተማሳሳይ መንገድ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የተቃውሞ ሰልፍ ከአሁኑ ለማኮላሸት የታሰበ መሆኑን የአካባቢው ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ450 በላይ መድረሱ ታወቀ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል። ወደ አርባምንጭ እስር ቤት ከተላኩት መካከል አቶ አማኑኤል ...
Read More »አዲሱ የአዲስአበባ ም/ቤት ካቢኔ ተመሰረተ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚሆኑ አስቀድሞ ሲነገርላቸው የነበሩት የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ የአስተዳደሩን ኃላፊነታቸውን ከአቶ ኩማ እጅ ተረክበዋል፡፡ በተለይ ሪፖርተር ጋዜጣ የምክትል ከንቲባነት ሥልጣን እንደሚይዙ የተነበየላቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንደተገመተው ወደስልጣኑ ያልመጡ ሲሆን በምክትል ከንቲባነት የቀድሞ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ተሹመዋል፡፡ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በተከናወነው ...
Read More »አንድነት ፓርቲ ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አቤቱታ አቀረበ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲው ያወጣውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ፣ ወረቀቶችን በትነዋል የተባሉ ሰዎች በየቦታው እየታሰሩ በመሆኑ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆምና የታሰሩትም እንዲፈቱ ጠይቋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ ፣ በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ አቶ አምደማሪያም እዝራ፣ አቶ ስማቸው ዝምቤ በወገራ ...
Read More »አቶ አየለ ደበላ አረፉ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራጣ በማደበር ተከስሰው 25 ዓመት የተፈረደባቸው አየለ ደበላ በቅጽል ስማቸው አይ ኤም ኤፍ የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴደራል በከፍተኛ ስነስርዓት ተፈጽሙዋል፡፡ አቶ አየለ የባንክን ሥራ ተክተው በመሥራት፣ አራጣ በማበደር፣ ግብር ባለመክፈልና በሌሎችም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በ22 ዓመታት እስርና በባንክ ያላቸው 12 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ከተወሰነ በሁዋላ፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ ...
Read More »በጋሞጎፋ ዞን በተነሳው ተቃውሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታሰሩ ብዙዎችም ተደበደቡ
ሐምሌ ፩( አንድ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን 300 የሚሆኑትን ደግሞ ማሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። አንዳንድ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጹት ፖሊሶች ...
Read More »50 ኢንዱስትሪዎች በሀይል እጥረት ስራ አልጀመሩም ተባለ
ሐምሌ ፩( አንድ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ተጎራባች በሆነችው ገላን ከተማ ውስጥ 50 ኢንዱስትሪዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ምክንያት ሥራ አለመጀመራቸውን ሪፖርተር ዘገበ። የከተማው ከንቲባ አቶ ሙሉጌታ ከበደ የሀይል አቅርቦቱ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ግንባታ ጨርሰው ወደ ሥራ የገቡ ባለሀብቶች ለሞራል ውድቀት እየተዳረጉ ነው፤›› ያሉት ከንቲባው፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ሥራ ውስጥ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ በጎንደር የጠራውን ሰልፍ በመንግስት ጥያቄ ማራዘሙን ገለጸ
ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በላከው መግለጫ ቀኑ እንዲራዘም የተደረገው የከተማው ከንቲባ በእለቱ የተማሪዎች የምረቃ በአል ፣ የመንገድ ምርቃና የፖሊስ ሀይሉ በስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ ሀይል የለም በሚል ፓርቲውን በጠየቀው መሰረት ነው። ፓርቲው በከንቲባው የቀረበውን ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ...
Read More »ከእስራኤል አገር በደህንነት ሙያ ሰልጥነው ስራ ከጀመሩት መካከል የተወሰኑ ሰራተኞች መታሰራቸው ታወቀ
ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከእሰራኤል አገር በደህህነት ሙያ ሰልጥነው በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት እና በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ከተመደቡት መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የደህንነት አባሎች ታሰሩ። አባሎቹ የታሰሩት መረጃውን ለኢሳት አቀብላችሁዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። እስካሁን ምን ያክል የደህንነት ሰራተኞች ተይዘው እንደታሰሩ አልታወቀም። ኢሳት ከአስተማማኝ የደህንነት ምንጮች ባገኘው መረጃ ስልጠናውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ከተመለሱት 987 ሰዎች መካከል ሁለት ...
Read More »