በቁጫ ወረዳ የመከላከያ ሰዎች በየቀበሌው እየዞሩ ህዝቡን በማስፈራራት ላይ መሆናቸው ታውቋል

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ልዩ ፖሊሶች በቶዮታ ፒክ አፕ መኪኖች ላይ ሆነው በየመንደሩ በመዞር ህዝቡን ሰብስበው እያነጋገሩ ነው። ወታደሮቹ ” የማንነት ጥያቄዎችን ያቀረባችሁት እናንተ ናችሁ ወይስ ጸረሰላም ሀይሎች ናቸው?” በማለት ጥያቄ ሲጠይቁ መዋላቸው ታውቋል። ድርጊቱ በሚቀጥሉት ቀናት በተማሳሳይ መንገድ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የተቃውሞ ሰልፍ ከአሁኑ ለማኮላሸት የታሰበ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የወረዳው ባለስልጣናት በዛሬው እለት ከ100 ያላነሱ ሰዎችን እያስፈረሙ መልቀቃቸው ታውቋል።