አንድነት ፓርቲ ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አቤቱታ አቀረበ

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲው ያወጣውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ፣ ወረቀቶችን በትነዋል የተባሉ ሰዎች በየቦታው እየታሰሩ በመሆኑ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆምና የታሰሩትም እንዲፈቱ ጠይቋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ ፣ በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ  አቶ አምደማሪያም እዝራ፣ አቶ ስማቸው ዝምቤ  በወገራ ወረዳ፣ አቶ ጀጃው ቡላዴ፣ በአልፋ ጣቁሳ ወረዳ መምህር አዋጁ ስዩም እንዲሁም በአዲስ አበባ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ መታሰራቸውን ፓርቲው ገልጿል።

አንድነት ፓርቲ ሀምሌ7 በጎንደር ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።