በሀይማኖት ጉዳይ የመጣው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን ይህን የተናገሩት በመካሄድ ላይ ባለው የሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው ላይ የተገኙት አንዳንድ የሀይማኖት አባቶች መንግስት “ትእግስቱን አብዝቶታል፣ እርምጃ ይውሰድልን” እያሉ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ አቶ በረከት ” መንግስት ሀይሉ እንዳለውና መታገሱ ጠቃሚ መሆኑን” ተናግረዋል።  “ይሁን እንጅ” ይላሉ አቶ በረከት “የተፈጠረው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም”። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰልፍ የሚያደርግ ከሆነ፤ሰልፉ ህገወጥ ነው አለ።

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል። ይህንን ተከትሎ ...

Read More »

ዩኒስኮ የላሊበላ አብያተ-ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው አለ

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የባህል እና የሳይንስ ድርጅት ስር በአለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር እና ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ ናቸው ሲል አለም አቀፉ ድርጅት አስታውቋል፡፡ ዩኔስኮ  ባቀረበው ጥናት ቅርሶቹ ባለፉት አርባ አመታት በተለያየ መልኩ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሺ ችግሮች ተጋርጦባቸዋል ብሎአል፡፡ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ...

Read More »

ምእራባዊያን በሶሪያ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ እየተዘጋጁ ነው

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የበሽር አላሳድ መንግስት በሲቪሎች ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተጠቅሟል በሚል ሰበብ ምእራባዊያን ሀይል እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው። እንግሊዝ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አንድ ህግ ረቂቅ ያዘጋጀች ሲሆን ረቂቁም አገሮች በሶሪያ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መብት ይሰጣል። የአየር ላይ ጥቃታቸውን ለመሰንዘር እየተዘጋጁ ያሉት አሜሪካ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ከቻይናና ከሩሲያ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ...

Read More »

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎችን በድጋሜ አስጠነቀቁ

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባዘጋጀው በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ” የአገሪቱ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአክራሪዎችንና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴዎች ከመደገፍ ካልተቆጠቡ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። ማንኛውም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በሚያደርጉትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጡት አቶ ሐይለማርያም፣ የጥፋት ሀይሎችን ለማምከን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። አዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ ...

Read More »

በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ እና ኢህአዴግ በየፊናቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ አዝማሚያው ወደ ውጥረት እያመራ መሆኑን ታዛቢዎች ገለጹ።

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን  በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል። በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ  የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና  ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ እንዲወጡ መታዘዛቸው፤ ሁኔታውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ...

Read More »

የግንቦት7 አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተያዙ የተባሉ 10 ሰዎች ዛሬ በአቃቂ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ዘመኑ ካሴ ከተባለው ሰው በስተቀር ሌሎች 9ኙ ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ለህዳር 2 ቀን፣2006 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶአቸዋል። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የባህርዳር ከተማና ዙሪያዋ ነዋሪዎች የሆኑት አሸናፊ አካሉ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ለማ፣ አንሙት የኔዋስ፣ ሳለኝ አሰፋ ፣ የክልሉ ...

Read More »

በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዊ እና አልሙ የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች እንዲሁም በአማራ ክልል ቻግኒ እና አካባቢው መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤ ነዋሪዎች ለኢሳት ባደረሱት መረጃ እንዳሉት በመብራት እጦት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተናል ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዩጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሺ ከአቅም በላይ ሁኖብኛል ሲል ተናግሮዋል፡፡ ድሃ አስፈጭቶ ለመብላት በየቀኑ ገዝተው ፤ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በፍቼ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርግ በባሌ ሮቤ አቅዶት የነበረውን ሰልፍ ደግሞ ሰረዘ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፍቼ ከተማ እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፈ ላይ የገዢው ፓርቲ አፈና በግልጽ የተነጸባረቀበት እንደነበር የፓርቲው የምክርቤት አባል አቶ አበበ አካሉ ገልጸዋል በባሌ ሮቤ ሊካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው ሀይል የሀይል እርምጃ ለመውሰድ በማቀዱ ሳይሳካ መቅረቱን በስፍራው የተገኙት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት ገዢው ፓርቲ በተቃውሞው ላይ ለመገኘት በሚመጡ ሰዎች ላይ እርምጃ ...

Read More »

ኢህዴግ ነሐሴ 26 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አደረገ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጽያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባዔ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ በአ/አ አምባሳደር ቲያትር አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አክራሪነትን ለመቃወም የፊታችን እሁድ ነሃሴ 26 ቀን በመስቀል አደባባይ ሰልፍ መጥራቱን አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ለማድረግ በይፋ ለአስተዳደሩ አሳውቆ ምላሽ እየተጠባበቀ የሚገኝ ሲሆን ምናልባት የሃይማኖት ተቋማቱ ሰልፍ ለማካሄድ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ሰልፍ ...

Read More »