በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዊ እና አልሙ የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች እንዲሁም በአማራ ክልል ቻግኒ እና አካባቢው መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤

ነዋሪዎች ለኢሳት ባደረሱት መረጃ እንዳሉት በመብራት እጦት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተናል ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዩጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሺ ከአቅም በላይ ሁኖብኛል ሲል ተናግሮዋል፡፡ ድሃ አስፈጭቶ ለመብላት በየቀኑ ገዝተው ፤ ሸምተው ጠላ እና አረቂ ጠምቀው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ችግራቸውን ለመቋቋም ሰፊ ፈተና ሁኖብናል ብለዋል፡፡ አሁንም እንደ ጥንቱ የድንጋይ መጅ ተሸክመው በእጃቸው የሚፈጩ እናቶች ሰርተው ለመብላት ተችግረዋል የገቢ ምንጫቸው ቆሟል፡፡

የገቢ ምንጫቸው የቆመባቸው ዝቅተኛ ነዋሪዎች በየቀኑ ሸምተው እና አስፈጭተው ለመመገብ መቸገራቸውንም ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እዳለ ከአዲስ አበባ ቻግኒ፤ ጉባ የህዳሴው ግድብ አንደኛ ደረጃ የጠጠረ መንገድ በመፈራረሱ የህዝብ አውቶቡሶች እና ከባድ የጭነት መኪናዎች በጭቃ ተውጠው መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ አሺከርካሪዎች ተናግረዋል፡፡ከቻግኒ ወደ እንጅባራ የሚደረገው ጉዞም በጣም አስቸጋሪ መሆኑንን ጠቁመዋል፡፡