አንድነት ፓርቲ በፍቼ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርግ በባሌ ሮቤ አቅዶት የነበረውን ሰልፍ ደግሞ ሰረዘ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፍቼ ከተማ እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፈ ላይ የገዢው ፓርቲ አፈና በግልጽ የተነጸባረቀበት እንደነበር የፓርቲው የምክርቤት አባል አቶ አበበ አካሉ ገልጸዋል

በባሌ ሮቤ ሊካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው ሀይል የሀይል እርምጃ ለመውሰድ በማቀዱ ሳይሳካ መቅረቱን በስፍራው የተገኙት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት ገዢው ፓርቲ በተቃውሞው ላይ ለመገኘት በሚመጡ ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ በመዘጋጀቱ ተቃውሞን ለመሰረዝ መገደዳቸውን ተናግረዋል።