ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ በእስር ቤት ውስጥ ህይወቱ አለፈ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኦሮሞ ህዝብ መብት በመታገል ላይ የነበረው የ37 ዓመቱ ወጣት ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ እንዳለ መሞቱ ታውቋል። ኢ/ሩ በምን ምክንያት እንደሞተ ግን አልታወቀም።  ከጓደኞቹ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢ/ር ተስፋሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ከነበረበት ጌዜ ጀምሮ ገዢውን ፓርቲ ይቃወም ነበር። ኢ/ር ተስፋሁን ኬንያ በነበረበት ወቅት ምንም እንኳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ...

Read More »

መንግስት በቫንኩቨር ካናዳ ሊያደርግ የነበረው የቦንድ ሽያጭ ተቃውሞ ገጠመው

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአባይ በፊት ዘረኝነት የወገድ በማለት መቃወማቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ወኪሎች ተቃውሞውን በመፍራት ሊሰበሰቡበት ተከራይተውት የነበረውን አዳራሽ በመተው በሰዎች ቤት ስብሰባውን በግለሰቦች ቤት ለማድረግ ተገደዋል። በስፍራው ለተገኙት አንዳንድ አረጋውያን ለአባይ ቦንድ የሚገዙ ከሆነ የቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጠቻው በስበሰባው መሪዎች ተነግሮአቸዋል። መንግስት በውጭ አገራት የሚያደርገው የቦንድ ሽያጭ ቅስቀሳ በተደጋጋሚ ተቃውሞ ...

Read More »

ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ በርካታ ሰዎች ሞቱ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ ወደ ወልድያ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ አውቶቡስ ደሴ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ የ21 ሰዎች ህይወት ጠፋ፣ የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 66 ደርሶአል። የአደጋው  መንስኤ ጥራት የሌለው የአስፓልት መንገድ በጎርፍ በመቆረጡ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የወልድያ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለኢሳት እንደገለጸው ደግሞ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ባሙያዎች ከደሴ በመላካቸው መረጃው ...

Read More »

በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላት ይሰግዱ የነበሩ ሴት ሙስሊሞቸ ተደበደቡ፡፡

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላታቸውን በመስገድ ላይ የነበሩ ሙስሊም ሴቶች በፖሊስ መደብደባቸውን የ ኢሳት ወኪል ከስፍራው ዘግቧል። በጁምአ ሰላት ላይ የነበሩት ሙስሊም ሴቶች የተደበደቡት፤ “ሶላት መስገድ የምትችሉት በግቢ ውስጥ እንጂ ከግቢ ውጪ አንጥፋችሁ አትሰግዱም” ተብለው በውጪ እንዳይሰግዱ በፖሊሶች መከልከላቸውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ሙስሊም ሴቶቹ ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት ከውጪ አንጥፈው መስገድ መጀመራቸውን የጠቆመው ...

Read More »

በባህርዳር የኢህአዴግ አባል ያልሆነና በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ያልተደራጀ ስኳዐር አያገኘም ተባለ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህርዳር የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ ለከተማው ነዋሪዎች አዲስ የአባልነትና አንድ ለአምስት አባልነት መለያ ወረቀት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንን ወረቀት ያላሳየ ሰው በመንግስት የሚከፋፈለውን ስኳር አያገኝም። አንዳንድ ነዋሪዎች ችግራቸውን በኤፍ ኤም ራዲዮ ላይ ቢናገሩም ምንም መፍትሄ እንደሌለው እንዳወቁ ለኢሳት ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ህዝብ ግንኙነት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ...

Read More »

በሱዳን ከ300 ሺ ህዝብ በላይ በጎርፍ ተጠቃ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በያዝነው ወር በጣለው ዝናብ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተው፣ ከ300 ሺ ያላነሱት ደግሞ ተፈናቅለዋል። በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም ላለፉት 25 አመታት ያልታየ ጎርፍ መታየቱን ድርጅቱ አስታውቋል። በአገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች መካከል በ14 ላይ ከፍተኛ የንብረት መውደምም ተከስታል።

Read More »

የቁጫ የአገር ሽማግሌዎች በጠቅላይ ሚ/ሩ ጽህፈት ቤት ተገኙ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 60 የሚጠጉ የወረዳዋ ሽማግሌዎች በዛሬው እለት ለ7ኛ ጊዜ በጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽሀፈት ቤት ቢገኙም ጠ/ሚኒስትሩን ሊያገኙዋቸው እንዳልቻሉና በተወካያቸው በአቶ ወርቁ በኩል መንግስት ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳውቃል የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል። በመንግስት መልስ ደስተኞች ያለሆኑት የአገር ሽማግሌዎች፣ እንደገና ተመልሰው ወደ ክልሉ ዋና ከተማ አዋሳ ማቅናታቸው ታውቋል። ሽማግሌዎቹ ለጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ተወካይ ፣ ...

Read More »

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን ቤት ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ እንደሚፈጅ አንድ ሰነድ አመለከተ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ረቂቅ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የኮንዶሚየም ቤት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ጠቆሟል። አስተዳደሩ ለኮንዶሚየም ቤቶች ብቻ ከ800ሺ በላይ ዜጎችን ቢመዘግብም በቀጣይ አምስት ዓመት ለመስራት ያቀደው 178 ሺ ቤቶችን ብቻ ነው፡፡ አስተዳደሩ ከ2006 እስከ 2010 ዓ.ም ሥራ ላይ ...

Read More »

ሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች -ሰማያዊ ፓርቲን ከፓርቲዎች የትብብር መድረክ አሰናበቱ።

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ33ቱ ፓርቲዎች የትብብር መድረክ -ሰማያዊ ፓርቲን ያሰናበተው፤የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ለ ሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ቃለምልልስ የሌሎች ፓርቲዎችን ክብር የነፈገ ነው በሚል ነው። በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ እንዲወጣ መወሰናቸውን የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው እሁድ በተካሄደ አስቸኳይ ስብሰባ ...

Read More »

በአማራ ክልል በአንድ ሰምንት ጊዜ ውስጥ በጎርፍ ከ45 ሰዎች በላይ ሞቱ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። በክልሉ ...

Read More »