ዩኒስኮ የላሊበላ አብያተ-ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው አለ

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የባህል እና የሳይንስ ድርጅት ስር በአለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር እና ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ ናቸው ሲል አለም አቀፉ ድርጅት አስታውቋል፡፡

ዩኔስኮ  ባቀረበው ጥናት ቅርሶቹ ባለፉት አርባ አመታት በተለያየ መልኩ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሺ ችግሮች ተጋርጦባቸዋል ብሎአል፡፡

የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ አብያተ ክርስቲያናቱ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በላሊበላ ከተማ በተካሄው ሰፊ ውይይት ላይ እንደተገለጸው የተሰሩት ጊዚያዊ ዳሶች በዘላቂነት ቅርሶችን ከጽሐይ እና ከዝናብ ለመታደግ አቅም የላቸውም ተብሎዋል፡፡ በዩኒስኮ ድጋፍ ለቅርሶቹ ገንዘብ ወጭ ያደረገው በሚሊዩን የሚቆጠር ዶላር ለመጠለያ ብቻ ግንባታ ውሎዋል፡፡

ዩኔስኮ አብያተ ክርስቲያናቱ አሁንም አገልግሎት የሚሰጡ  ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ አደጋው እስከውድመት ሊደርስ እንደሚችል ለኢትዩጵያ መንግስት መግለጹን ተናግሯል።