መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 12 እና መስከረም 19 ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች በተከታታይ የጠሩዋቸው ሰልፎች በመስቀል አደባባይ እንደማይካሄዱ የአዲስ አበባ መስተዳድር ህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ክፍል አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ይህን ያስታወቀው ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት ካደረገ በሁዋላ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ” ህዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ለዜጎች ሁሉ መብት የሆነውን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ...
Read More »የደቡብ ነዋሪዎች በኑሮዋቸው መጎሳቆላቸውን ገለጹ
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቆላማና ከፊል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶአደሮች ባለፉት 20 ዓመታት በአካባቢው በተደጋጋሚ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለከፍተኛ ጉስቁልና መዳረጋቸው ታውቋል። በቦረና ዞን ብቻ በ2005 ዓ.ም 30 ሺህ 216 እንስሳት በድርቅ ሲያልቁ፣ በ2004 ዓ.ም ደግሞ 10 ሺህ 609 እንስሳት አልቀዋል፡፡ በማኅበራዊ ጥናት መድረክ የአካባቢ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት አቶ አለባቸው አደም ከመልካም አስተዳደርና ከአየር ጸባይ ...
Read More »ግብጽ ወደ አደገኛ የግጭት ቀጣና ውስጥ እየገባች ነው
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣናቸውን በሀይል ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ግብጽ ሰላም ማግኘት አልቻለችም። የአገሪቱ መንግስት የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊዎች ለማደን በሚያደርጉት ጥረት አንድ የፖሊስ ጀኔራል ተገድለዋል። መንግስት በርካታ የፕሬዚዳንቱን ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲያስታውቅ፣ ደጋፊዎቹ ግን ራሳቸውን መሰራያ በማስታጠቅ መንግስት ለመፋለም ቆርጠው መነሳታቸው ይነገርላቸዋል። መንግስት በያዘው አቋሙ ከገፋበት ግብጽ ዳግም ሶሪያ ልትሆን እንደምትችል ምሁራን ይናገራሉ። ከሁለት አመት ...
Read More »4 የአየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል። በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ...
Read More »ኢህአዴግ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሩን በመያዝ እየገመገመና እያሰለጠ ነው
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦህአዴድ፣ ብአዴን፣ ኢህዴንና ህወሀት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ካለፈው እሁድ ጀምሮ በየክልሎቻቸው ተሰባስበው ግምገማ እያደረጉና ስልጠናም እየወሰዱ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ለ10 ቀናት በሚቆየው ስልጠና አመራሮቹ እርስ በርስ ከመገማገም ባለፈ ስለ ልማት ሰራዊት አደረጃጀት፣ ስለ አንድ ለአምስት አተገባበር ፣ አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም በመጪው አመት ስለሚካሄደው አገራቀፍ ምርጫ ስልጠናዎች እና ውይይቶች ይካሄዳሉ። ተመሳሳይ ስልጠናዎችና ...
Read More »ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ መንግስት የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን መበተን ጀመረ
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሁለቱ ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው መንግስት በዛሬው እለት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ሊስትሮዎችን፣ በጎዳናዎች ላይ እቃዎችን የሚሸጡትን በጸጥታ ሀይሎቹ አማካኝነት እንዲሰበሰቡና ወደ አልታወቀ ስፍራ እየወሰዱዋቸው ነው። የሚታፈሱት ሰዎች ወዴት እንደሚወስዱ ባይታወቅም ከአንዳንድ ሰዎች ባገኘነው መረጃ ሰዎቹ ፓርቲዎቹ ያዘጋጁት ሰልፍ እሲከጠናቀቅ ታግተው ይቆያሉ። ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ የሚያደርገው ...
Read More »መንግስት ለተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ጥበቃ እንዲያደርግ ተጠየቀ
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-33ቱ ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ባወጡት መግለጫ ፣ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግላቸውን ለማስፋት በተጠናከረ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ መንግስት የህግ ጥበቃ ሊያደርግ ባለመቻሉ ከፍ ያለ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በወላይታ፣ በአርባ ምንጭ፣ በፍቼና፣ በጎባ ከተሞች በተንቀሳቀሰባቸው ወቅቶች አባሎቻቸው መደብደባቸውን፣ መታሰራቸውን፣ የሥራ መሣሪያዎቻቸውን መነጠቃቸውን፣ ለመኝታ ገንዘብ የከፈሉበት ሆቴል በር እንዲዘጋባቸውና ደጅ እንዲያድሩ ...
Read More »ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሻካሮቭ ሽልማት የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ።
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች የአውሮፓ ህብረት ለነፃነት ታጋዮች በየአመቱ ለሚያዘጋጀው የ “ሻካሮቭ ሽልማት” የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ። የአውሮፓህብረት የሻካሮቭ ሽልማት ኮሜቴ-ከህብረቱ የውጪ ጉዳይና ልማት ኮሚቴ እና ከሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ጋር በመሆን ትናንት ሰኞ ይፋ እንዳደረጉት ማላላ ዩሳፍዛይ ከፓኪስታን፣ ኤድዋርድ ስኖውደን ከ አሜሪካ፣ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ ...
Read More »በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በከተማ መልሶ ማልማት ይፈናቀላሉ፡፡
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ8 ሺ 800 በላይ ሰዎች በመልሶ ማልማት የተነሳ እንደሚፈናቀሉ ከክልሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ተፈናቃዮች እንደሚሆኑ ያወቁ ነዋሪዎች በከፍተኛ የኑሮ ችግር ውስጥ ወድቀናል ሲሉ አማረዋል።በአማራ ክልል በሚገኙ በሶስቱ የክልሉ ሜትሮፖሊታን ከተሞች ማለትም በባህርዳር፣ደሴና ጎንደር በመልሶ ልማት የሚፈናቀሉ 5 ሳይቶች ተለይተው ተከልለዋል፡፡ በባህርዳር በመጀመሪያው ዙር 431 የቀበሌ ቤት ተከራዮች ፣ 2 ሺ 155 ቤት ተጋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ...
Read More »በኬንያው ም/ል ፕሬዚዳንት ላይ የመጀመሪያዋ መስካሪ ቀረቡ
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከስድስት አመታት በፊት በኬንያ ከተደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ ለተገደሉት ሰዎች ተጠያቂ የተደረጉት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ዘ ሄግ በሚገኘው አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በአካል ቀርበው የመጀመሪያዋን የጉዳቱ ሰለባን ቃል አዳምጠዋል። ማንነቷ በውል ያላታወቀችው መስካሪ በረብሻው ጊዜ የደረሰውን ግፍ በዝርዝር አስረድታለች፡፤ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው ታውቋል። ሌሎች 22 ምስክሮችም በተከታታይ ቀርበው እንደሚመሰክሩ ታውቋል። ...
Read More »