አንድነት ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ ውጤት እየገመገመ ነው

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው አመራሮች በዛሬው እለት ተሰብስበው ትናንት እሁድ ፓርቲው የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ውጤት ገምግመዋል። መስቀል አደባባይ ብንሄድ ኖሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል የተናገሩት አቶ ደንኤል፣ በከፍተኛ አፈና ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ከ80 ሺ በላይ በሆነ ህዝብ መካሄዱ የተሳካና ለሚቀጥለው ሰልፍ ፍንጭ የሰጠ፣ ህዝቡ ለውጥ ፈላጊ መሆኑንና ከፓርቲያቸው ጎን የቆመ መሆኑን ለማየት ችለናል ...

Read More »

ግንቦት7 በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መስመሩን እየዘረጋ መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው። የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው  የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት ሰዎች በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ የገለጹት ...

Read More »

9.5 ሚልዮን የባለ አንድ እና የባለ አምስት ብሮች የአገልግሎት ጊዜያቸው ከመጠናቀቁ በፊት ከገበያ ውጭ ሆኑ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአውሮፓውያኑ በ2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው ፣ በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው። ብሮችን የሚቀብሩ እና አሽገው የሚያስቀምጡ እንዳሉ የገለጹት ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ በነጻነት ቅስቀሳ ለማድርግ አልቻለም

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ የፓርቲው አመራሮች ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ለሰአታት ታግተው አርፍደዋል። ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር  በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ ለፓርቲው ፈቃድ ቢሰጥም ፣ ፖሊስ በበኩሉ ፓርቲው ቅስቀሳ ለማድረግ ከፈለገ ከሚመለከተው አካል ልዩ ፈቃድ ማምጣት ...

Read More »

በቁጫ ወረዳ ታስረው የነበሩ ሰዎች ተለቀቁ

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ታስረው የነበሩ 40 ሰዎች ተፈቱ። አስተባባሪ ናቸው በሚል የታሰሩት መቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ ግን ሳይፈቱ ቀርተዋል። ሰዎቹ ከ3 ወራት በፊት ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ውሳኔ ቢያስተላልፍም ፖሊስ በራሱ ስልጣን አልፈታም ብሎ መቆየቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። ይሁን እንጅ እስረኞቹ በትናንትው እለት ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክታል። ...

Read More »

ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የተሸከሙ መኪኖች ወደ ሰሜን ማቅናታቸው ተዘገበ

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት ከ30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል። መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመነጋገር ያደረግነው ሙከራ ...

Read More »

በአዲስ አበባ በርካታ ቤቶች ሊፈርሱ ነው

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የያዘውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ወደሁለት ዓመት ካጠፈ በኋላ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ያለውን መልሶ ማልማት ሥራ በሰፊው እንደሚያከናውን አስታውቆአል፡፡ በዚህ የመልሶ ማልማት ሥራ በመሃል ከተማ የሚገኙ በርካታ ቁልፍ ቦታዎች የሚፈርሱ ሲሆን ነዋሪዎችም የመፈናቀል አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ በ2006 እና  በ2007 በጀት ዓመትም ...

Read More »

በ10 ቀናት ውስጥ አንድ ባለ አንድ ፎቅ ተገነባ

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንጻ ግንባታ እና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ከጀርመኑ ባዉሃዉስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊመር እና ከደቡብ ሱዳኑ ጁባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ ተማሪዎች አማካይነት በ10 ቀናት ውስጥ  የባለ አንድ ፎቅ ተገጣጣሚ ሕንጻ ገነባ፡፡ ይህ በዓይነቱ አዲስ የሆነውን ቴክኖሎጂ በነገው ዕለት ይፋ ለማድረግ ፕሮግራም ተይዞአል፡፡ ቴክኖሎጂው በተለይ በጀርመን አገር የሚሰራበትና ...

Read More »

የደመራ በአል ተከበረ

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው ደመራ በአል በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። በአዲስ አበባ የሀይማኖቱ አባቶች ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የውጭ አገር ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተከብሮአል።

Read More »

የመንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ከወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት አለ

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል። በቅርቡ በወልድያ ከተማ የወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች ባነሱት ...

Read More »